ለኢትዮጵያዊቷ እህቴ አስቴር በdhaኔ ጥሪሽን ለማሳካት እውነቱን ላግዝሽ (ሰርፀ ደስታ)

በመጀመሪያ የግዕዝ ሶፈት ዌር ሰርተናል ለምትሉ ሥማችንን እንኳን በአግባቡ መጻፍ እንዳላስቻለን እንድታስተውሉ ነው የአስቴርን ሥም ከእነ አባቷ ለመጻፍ ጉራማይሌ መጠቀም ግድ የሆነብኝ፡፡ ከዚህ በፊት ዶ/ር አበራ ሞላ የግዕዝ ሶፍትዌር ኦሮምኛን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ቋንቋዎች ሊያስጽፍ በሚችል አዘጋጅቻለሁ ሲሉ የሰማሁ መስሎኝ ነበር ሆኖም ፊደል ተቀርጾላቸው የነበሩ ሆሄያትን እንኳን  አሟልቶ ያለ የግዕዝ ሶፍት ዌር እስካሁን አላየሁም፡፡ dhe የተባለ ፊደል ከነ ርቢው በደርግ ጊዜ ተቀርጾ  አገልግሎት ላይ እንደዋለ አስታውሳለሁ፡፡ ፊደሌ እንደ ጸ ሆኖ አናቷ ላይ ያለው ክፍተት ውስጥ  እንደ ፀ ሰረዝ ያለው ነበር፡፡ እንግዲህ ይሄ ፊደል ለምን በግዕዝ ሶፍት ዌር እንዳልተካተተ አላውቅም፡፡ ይሄን ጉዳይ ከዚህ በፊትም አንስቼ ነበር፡፡ አሁንም አስቡበት፡፡ ኦሮምኛን በላቲን የሚጽፉ ምርጫቸው ነው፡፡ ኦሮምኛን ግን በአማርኛ ለሚጽፉ ፊደሎቹ ተሟልተው እንዲቀርቡ እንፈልጋለን፡፡ ከ dhe ይልቅ ዛሬ መቐለ የሚጻፍበት ቐ እንደነበር ትዝ አይለኝም፡፡ የለም ማለቴ አደለም ደግሞ እን ከማውቀው አካባቢ አንጻር እንጂ፡፡

በዚሁ ወደ ጉዳዬ የእህቴ አስቴር ጥሪ ልመልሳቸሁ፡፡ አስቴርን እሰካሁን በኢትዮጵያዊነቷ እናውቃታለን፡፡ ሌላው ያልሆነ አለ ወይ የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ አጥቼው አደለም፡፡ መልሴ አዎ ነው፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ እገልጸላለሁ አሁን ግን በቀጥታ ወደ አስቴር፡፡

አስቴር እህቴ አንቺ እንዳልሺ ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ እኔ ግን አንቺ እንዳልሺ  አይነት ከአለም በጣት የሚቆጠር ነው እላለሁ፡፡ በኦሮሞ ስም ፌስቡክ አካውንት ከፍተው ኦሮሞን እንዲጠላ እያደረጉ ያሉ ሌሎች እንዳሉ ግን አላጣሁትም፡፡ እነዚህ ሲጀምር በቀላሉ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ለእኔ ማለት ነው፡፡ ሌላው ይሸወድ እንደሆን አላውቅም፡፡ አንዳንዶቹም በይፋ ኦሮሞ እንዳልሆኑ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጂጂ ኪያ የምትባል፡፡ ሌሎቹ ቀሪዎቹ ከእውነተኞቹ ኦሮሞ ከሆኑት አንጻር እዚህ ግባ ይማይባሉ ናቸው፡፡ ምንም ማስተባባል አያስፈልግም፡፡ የጥላቻና ዘረኝነትን በዋናነት በኦሮሞ ሥም ፌስቡክ ኖሯቸው የሚነዙት በአብዛኛው ኦሮሞ ለመሆናቸው አልጠራጠርም፡፡ እሱም ብቻ አደለም፡፡ በኦሮሞ ሥም ፌስቡክ ከፍቶ በተለይ አማራን የሚጠላ ዘመቻ መልዕክት የሚያዛምቱትን ኦሮሞ እንዳልሆኑ በግልጽ እየታወቁ እንኳን  አሁንም በዋናነት ደጋፊዎቻቸው ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ካላይ የጠቀስኩልሽ ጂጂ፡፡ ይቺ ሴት በአውሮፓ የቄሮ ወኪል ነኝ እስከማለት የደረሰች ነች፡፡ ኦሮሞ እንዳልሆነች ግን ኦሮሞም ሌላውም ያውቀዋል፡፡ በአትላንታ የኦሮሞ ቻርተር እንነድፋለን ብለወ በተሰበሰቡ ጊዜ በክብር እንግድነት ተጋብዛ የተለመደ የጥላቻ ምልዕክቷን እንድታስተላልፍ በኦኤም ኤን ቃለ መጠይቅ ተደርጎላን ነበር፡፡ በተሰብሳቢዎቹም ከፍተኛ አድናቆት ሲቸራት ነበር፡፡ ሌላው ተስፋዬ ገብረአብን አስተውይ፡፡ ኦሮሞ እንዳልሆነ ይታወቃል ግን ጥሩ የጥላቻና ዘረኝነት መጽሀፍ ስለጻፈ ዛሬ ብዙ  ኦሮሞ ይቀበለዋል ብቻ ሳይሆን ያመልከዋል፡፡ በቅረቡ አዲሱ አረጋ አምቦ ላይ የተስፋዬ ገብረአብን መጻፍ  እንዴት እንደተጻፈ ሳይቸግረው ተናግሮ የገጠመውን አስተውለሻል፡፡ አዲሱ  የተናገረው ትክክል እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ያላወቀው የተስፋዬ ገ/አብ ልብወለድ ለብዙ ኦሮሞ እንደመጻፈቅዱስ ወይም ቁራን ሌላኛው የሐይማኖት መጻፍ እንደሆነ ባለማስተዋሉ በተናገረው በገጠመው ተቃውሞ ምክነያት ይቅርታ እኔ ሐይማኖትን ለመተቸት ሞክሬ አደለም የሚል የሚመስል ይቅርታን ተገድዶ ጠይቋል፡፡ እነዚህ እንግዲህ ሁሉም እንዲገነዘብ ትልልቅ ምልክቶችን እንደምሳሌ  ለማንሳት ነው፡፡

እኔ ግን ብዙ ጉድ አውቃለሁ፡፡ እንዳልሽውም አንዳንዴ ፌስቡክ ላይ ይሄ ኦሮሞ ላይሆን ይችላል ብዬ ብዙ ሰው ቼክ አደርጋለሁ፡፡ በጣም አነስተኛ የሚባሉ ከአልሆኑ በአብዛኛው በትክክልም ኦሮሞ የሆኑት ናቸው የጥላቻውንና ዘረኝነቱን መልዕክት የሚያስተላልፉት፡፡ አሁን ኦሮሞ አቃፊ ነው! አይሰራም፡፡ ኦሮሞም ሆነ ሌላው አሁን ወደ አውሬነት እየተቀየረ ነው፡፡ በአላስፈላጊ የድለላ ቃል እየተሞከሻሹ ከእነጭርሱ የቀሩትም ሰዎች ከማጣት እውነቱ ላይ ቆመን መድሀኒት ብንፈልግ ይሻላል፡፡ እንግዲህ ኦሮሞ ሁሉ ዘረኛ ነው የሚል ምልከታ የለኝም፡፡ በእርግጥም ኦሮሞ ሆነው በኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ ፖለቲካ እጅግ የተማረቱና የሚበሳጩ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ዛሬ ላይ ግን ድምጻቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰማው የጥላቻና ዘኝነቱን አራማጆች ናቸው፡፡ እኔ እስከማውቅሽ አንቺ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ነሽ፡፡ ልሳሳት እችላለሁ፡፡ ከምትናገሪያቸው ነገሮች እንጂ በውል አንቺን አላውቅሽምና፡፡ በአካል የማውቃቸው ብዙ ኦሮሞ ጓደኞች ነበሩኝ አሁንም አሉኝ፡፡ እያደርግ አምናቸዋለሁ በምለው ሳይቀር ተቀብሮ የኖረ የጥላቻና ዘረኝነት ማንነት ሲፈነዳ አያለሁ፡፡ አዝናለሁ፡፡ እኔ እውነቱ ልንገርሽ ኦሮሞ ጓደኛዬን ኦሮሞ ስለሆነ ብዬ በኦሮሞነት ደስ እንዲለው በሚል አንድም እድል አልሰጠውም፡፡ ጓደኝነት ከሆነ ጓደኝነት ነው፡፡ በቃ እንደልብ ማውራት እችላለሁ፡፡ ይሄ ማለት ግን ጋጠወጥ አይነቱን ሁሉ አደለም፡፡ በእርግጥም እንደ ኢትዮጵያዊ (ኢትዮጵያዊም ባይሆን ለምሳሌ ኤርትራዊያን) የምንጋራቸው መሠረታዊ እሴቶች ስላሉን ሁሉንም ሳንሸማቀቅ እርስ በእርስ እናወራለን፡፡ የሚገርምሽ እስከ ወያኔ ተቀይሮ አብይ መምጣት ጊዜ ጓደኝነታችንን የጠበቅን ሰዎች የአብይ መምጣት ብዙዎችን የውስጥ ማንነታቸውን መቆጣጠር በማይችሉበት ደረጃ ሆኖ ጓደኝነታችን ሊቀጥል ያልቻሉ አሉ፡፡ ይሄን ስል ደግሞ የሚገርመው እንደዛሬው አብይን በምተችበት ወቅት አደለም፡፡ ይልቁንም አብይን በመደገፌ እንጂ፡፡  የአብይ መጀመሪያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት ለብዙ ኦሮሞ ነበር ጓደኞቼ የሞት ያህል እንደነበር አስተውያለሁ፡፡ ኢትዮጵያን እንዴት እንደሚጠሉ አይቻለሁ፡፡ ይሄ እውነት ነው፡፡ እጅግም አዝኛለሁ፡፡ ዛሬ ላይ አብይ በተናገረው ቃል ሳይሆን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለቱ ስልታዊ የኦነጋውያነን ሴራ ለማስፈጸም ይረዳ ዘንድ እንደሆነ ሲረዱ ዋና የአብይ ደጋፊ ሆነዋል፡፡ በእርግጥ ነው አብይን አፈልጉትም፡፡ ግን መሸጋገሪያ እንዲሆናቸው አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ ስለሆነላቸው ነው፡፡ የተረፉት ደግሞ አሁን አብይ በሚሰራው ሥራ ልክ እንደወያኔ ደጋፊ በጭፍኑ እየደገፉ አሁን ኢትዮጵያዊነት የሚሉ አሉ፡፡ አዝናለሁ፡፡ ይሄን ጉዳይ አናባብለው፡፡ ኦሮሞ በብዙ በዘረኝነትና ጥላቻ ተበክሏል፡፡ በዩኒቨርሲት ያለፈ ኦሮሞ ለምልክት ከልብ ኢትዮጵያዊነት የሚቆጨው ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው፡፡ ለ50 ዓመት የጥላቻና ዘረኝነት አስተሳሰብ ሲሞላ ከቆየው ይልቅ በኦሮሞ ሥም ሌላው ፌስቡክም ቢኖረው ሊናገረው አይችልም፡፡   ኦሮሞ (ኦሮሞ የሚለው አውቃለሁ የሚለውን ነው፡ ሚስኪኑን ሕዝብ ድሮስ ማን ቦታ ሰጥቶት) ዛሬ ለደረሰበት የጥላቻና ዘረኝነት አስተሳሰብ 50 ዓመት ፈጅቶበታል፡፡ አሁን ላይ በአማራው ላይ የሚታየው የጥላቻና ዘረኝነት ወረርሽኝ ለሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ኦሮሞን ይተካከላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኦሮሞ ከደቂቅ እስከ ከፍተኛ ምሁር ነኝ የሚለው የተማረውና ብዙ ወጣቱ ከኢትዮጵያዊነት ከጠፋ ቆየ፡፡

በግሌም የደረሰብኝ አለ፡፡ ይሄን የማነሰው ለማስረጃነት እንጂ ደረሰብኝ ለማለት አደለም፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን! እኔ ከአንዴም ሁለቴ ማንነቴን እንኳን በውል ሳያውቁ በሥሜ ብቻ ለመቼም የማልረሳውን የኦሮሞ ዘረኝነትና ጥላቻ ልክን ማይት ችያለሁ (ከእነዚህ ውጭ ሌሎች ገጠመኞች አሉኝ ግን ተራ ናቸው ብዬ ስለማልፋቸው ነው)፡፡  አንዴ ሥራ ልቀጠር ሌላ ጊዜ ደግሞ በጣም ጓደኛዬ ከሆነ እሱ በሥም ለኦሮሞነት የሚቀርብ ጋር አንድ የጋራ ቢዝነስ ማስታወቂያ አይተን ልንመዘገብ ሄደን፡፡ የሥራ ቅጥሩ አሳዛኝ ነበር፡፡ እኔ ከተወዳደሩት በትምህርት ነጥብ ከፍተኛውን የነበረኝ ነበር፡፡ ቦታው የትምህርት ነጥብን የሚጠይቅ ነበርና፡፡ ገብቼ የተጠየኩት ጥያቄ ከሙያው ጋር የተገናኘ ሳይሆን ዘሬን ነበር፡፡ በኋላ ውጤት ሲወጣ የእኔ ሥም ከሁሉም የመጨረሻ ነበር፡፡ሁኔታው የሚጀምረው ገና ስሜ የሚጠራው ሰው መጥቶ ሥሜን ሲጠራ በትክክል መጥራት አልቻለምና ኩን ኢሞ አሳ ኑቲ dhuፌ (ይሄ ደግሞ ከየት ነው የመጣብን) አለ፡፡ ገብቼም ዋና ማጣራት የተደረገው ዘሬን ነበር፡፡ ውጤቱም ከላይ አንደጠቆምኩት መጨረሻ ነው፡፡ የሚገርመው የዚህ ሥራ ውጤት በመዘግየት እኔ ውጤቱ ሲመጣ ሌላ የተሻለ ቦታ ተቀጥሬ ሥራ ጅምሬ ነበር፡፡ ያዬት ጓደኞቼ በቁጭት ሂድና ንገራቸው ብለውን ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው፡፡ መናገሩስ፡፡ ሁለተኛው የቢዝነሱ ማስታወቂያም እንደዛው ነው፡፡ እዛ እንደደረስን መታወቂያ ተጠየቅን እኔም ጓደኛዬም ፓስፖረት ስለነበረን አውጥተን አሳየን፡፡ አስተናጋጇ የጓደኛዬን ተቀበለችው፡፡ እኔን ገና ሥሜን ስታይን ያንተ የቀበሌ መታወቂያ ያስፈልገዋል አለች፡፡ በኋላ ጓደኛዬ ሊናገር ሞከረ፡፡ እኔ ስለገባኝ ተወው አልኩት፡፡ እሷም እንመደንገጥ ብላ ስለተነገረን ነው እኔ ብዘግብህ ደስ ይለኝ ነበር አይነት ልታጽናናኝ ሞከረች፡፡ የሚገርምሽ ጓደኛዬ በጣም ተሰማው እኔን ግን ምንም አልመሰለኝም፡፡ በብዙ ኦሮሞዎች ዘንድ ምን አስተሳሰብ እንዳለ አውቃለሁና፡፡ እነዚህ ወሳኝ የሆኑ ምን አልባትም አማራጭ ባይኖረኝ ሕወትንም ሊጎዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ በሌላ ትንንሽ መድልኦዎች ጠግቤዋለሁ፡፡ እንግዲህ አስቴር ሆይ አንቺ ኦሮሞዎች አደሉም ኦሮሞዎች እንዲህ ያለ ጥላቻ የለባቸውም ብለሽ ስትናገሪ እውነቱን እንዲህ የሚያውቁ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ይሄ የእኔ ብቻ ገጠመኝ አይምሰልሽ፡፡ በተመሳሳይ አንዲሁ የገጠማቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊነትን ካልሽ እውነቱን እንጋፈጥ፡፡ ትውልድ ይዳን ከተባለ አቃፊ ነው ምናም እያሉ እጅግ ዘረኛውነና በጥላቻ የነወረውን እያሞካሹ ሳይሆን አርግጡን እንናገረው፡፡ እዚህ ላይ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዳይወሰድ፡፡ ኦሮሞ እንደ ሕዝብ አደለም፡፡ ወደድንም ጠላንም ነገሮችን የሚዘውረው የተማረውና ኤሊት የተባለው ነው፡፡

እንግዲህ ታች ያለ ሕዝብ ለኑሮው ራሱ መከራውን የሚያይ፡፡ እሱንም የመጠቀሚያ እቃ እየሆነ ያለው በኦሮሞነት እያጨቁ ማምታት ይቅር፡፡ የምናወራው በዋናነት ኤሊት በተባሉትና ዛሬ ዛሬ ደግሞ ብዙ ወጣት ስላፈሩት ዘረኛና በጥላቻ የመረቀዙ ሰዎች ነው፡፡ ኦሮሞ በኢትዮጵያ የመንግስት መዋቅሮች ሁሉ የሚገለጸው ደግሞ በእነዚህ እንጂ በሚስኪን ገበሬ አደለም፡፡ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ  በጥላቻና ዘረኝነት የመረቀዘ ኦሮሞ ሊነግረኝ አይችልም፡፡ ከመሠረቱ አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ እኔ የታሪክ ምሁር አደለሁም፡፡ አደለም ከተራ ሰው የታሪክ አዋቂ ነን ከሚሉት ያላነሰ ከልጅነቴ ከአበቴ ጀምሮ እየተማርኩ አድጌ ሌላውን አነባለሁ፡፡ አባቴ ገበሬ እንጂ ደግሞ ምሁር አደለም፡፡ እኔ ኢትየጵያን ከሰሜን እስከደቡብ ለማየት እድሉ ገጥሞኛል፡፡ አውቃለሁ ሁሉም ቦታ ኢትዮጵያዊ ኑሮው ያው ነው፡፡ የወያኔ ዘረኞች አገር እየዘረፉ ለተወሰኑ ኤሊት ትግሬዎች ሲፈነጩ የትግራይ ሕዝብ እንዴት እንደሚኖር አውቃለሁ፡፡ እስክ ጉራንጉሩ ቀበሌ ድረስ፡፡ እንደተባለው ትግራይ ቢለማ እንዴት ደስ ባለኝ፡፡ በአንደ ወቅት በአንድ የትግራይ ቀበሌ (ቦታውን አልናገርም አሁን ላይ ጥያቄ እያነሳ ያለ ነው) እርከን ሲሰሩ ያገነኋቸው ሰዎችን አስታውሳለሁ፡፡ እርከን የሚያሰራውን የቀበሌውን ተመራጭ እኔ ለማወቅ ብዬ የጠየኩትን ይሄን እርክን አሁን ምን ልትሰሩበት ነው ስለው (ጥያቄዬ ምን ሊያለሙበት እንዳሰቡ ነበር) እሱ የሠጠኝ መልስ ልብ የሚነካ ነበር፡፡  መልሱ እኔ ከጠየኩት ጋር ሳይሆን ስለሆነው ነገር በቁጭት ነበር፡፡ መሬቱ ድንጋያማና ኮረብታ ነው፡፡ እንዲህ “እንግዲህ ለእኛ ከዚህች መሬታችን ውጭ ምን እድል አለን ብለህ ነው፡፡ በደርግ ጊዜ 17 ዓመት ስንዋጋ ኖርን፡፡ ያልፍላችኋል ብለው ሲያዋጉን የነበሩት ይሄው እነሱ አልፎላቸው እኛ ከዚችው መሬታችን ነን፡፡ እስካሁንም አርፈን መሬታችንን ብንንከባከብ የተሻለ ሕይወት ይኖርን ነበር፡፡ አሁንም ዝናቡን ካልከለን የችን ድንጋያማ መሬታችንን ያለቻትን አፈር በእርከን ደግፈን የእለን ጉርሳችንን እናመርትባታለን”፡፡ ይሄ ነው እውነታው፡፡  ይሄ እውነት ከሰሜን እስከ ደቡብ ያው ነው፡፡ የኦሮሞም ገበሬ ሆነ ሌላው ሚስኪን ነዋሪ ከዚህ የተለየ ነገር የለውም፡፡ እንወክለሀለን ያሉት ግን የንግድ እቃ አድርገውት ይሄው መቼም እንዳያልፍለት መደበቂያ ዋሻቸው ሆኖ እንዲቀጥል ሙጥኝ ብለውታል፡፡ እንጂማ ለኦሮሞ በይው አማራ ትግሬ ሌላም ገበሬ ዛሬ ጀምሮ የብሔር ፖለቲካ አቁመናል ቢባል ተገላገለ ነበር፡፡

አስቴር ሆይ እውነቱን እንጋፈጥ ካልሽ መልካም፡፡ አለበለዚያ ለኦሮሞነት ጠበቃ አትሁኚ፡፡ ይዞሽ ይጠፋል፡፡ ማንም ማንነቱን ፈቅዶ አልተወለደም፡፡ ኦሮሞ አቃፊ ነው የሚለውን ዲስኩር ለጊዜው እናቆየው፡፡ በትክክል ሕዝብ እንደልቡ አስቦ የሚፈልገውን ምመረጥ ሲችል ያኔ ሕዝቡ እንደማሕበረሰብ በኖረበት ባሕሉ በተግባር የሚያሳየን ነው እንጂ አቃፊ ነው አደለም በሚል አደለም፡፡ ሕዝብ እንደሕዝብነቱ አቃፊ አደለህም ያለው ማን ነው፡፡ ሕዝብ አደለም አገር የሚመራው አኮ፡፡ የመንግስትን መዋቅር የያዘውና ወደፊትም አገርን ሊረከብ የሚችለው ብዙው ወጣት ነው እኮ ችግሩ፡፡ የምናወራውም ስለዚህ እንጂ ሚስኪን ገበሬ ወይም ነዋሪ አደለም፡፡ እርግጥ ነው ሕዝቡንም እየበከሉት ነው፡፡ አብሮ ለመኖር የሚያስችሉት እሴቶቹን በሙሉ እያጠፉበት፡፡ እንግዲህ ፌስቡክም በይው በተለያዩ ቦታዎች የሚሰሙት የጥላቻና ዘረኝነት መልዕክቶች እየተሰራጩ ያሉት በሚስኪኑ ሳይሆን አቃፊ መሆኑን ቀርቶ በገጀራና ሜጫ የሚዝቱ እንደሆኑ እያየን የኦሮሞ ሕዝብ አቃፊ ነው በሚል መደለያ ተጨማሪ ጥፋት መጋበዝ ያለብን አይመስለኝም፡፡ እስኪ አስተውይ እንደልባቸው ሕዝብን ከሕዝብ እያጋጩ ያሉትን አደል እንዴ የኦሮሞ መንግስት ነኝ ባዩ በፖልስ እያጀበ በሕዝብ ላይ የሚያስጨፍረው? ስለዚህ አስቴር ሆይ ተማጽኖሽን ከቅንነት እንደሆነ አስቤ እንድታስተውይው ያህል መለዕክቴ ይሄው ነው፡፡ ይሄ በኦሮሞ ብቻ አደለም፡፡ አሁን ሁሉም አንድ እየሆነ ነው፡፡ መሪው ግን አሁንም ኦሮሞ ነው፡፡ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ በኦሮሞ ፖለቲከኞች ዘንድ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ እንጂ አማራጭ እንኳን አደለም፡፡ የግድ የጥላቻና ዘረኝነቱ ፖለቲካ መቀጠል አለበት እነሱ በወነጀል እንዳይጠየቁ፡፡

እዚህ ላይ ለሚዲያ የማይመቹ ሌሎች ጉዳዮች አሉኝ፡፡ አንዳንድ ጉዳዮችን ከእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ከሆነ ኦሮሞ ጋር በተለይ ብነጋገራቸውና ያለውን እውነት የበለጠ ለማስረዳት ብችል ደስ ይለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ እኔ እጅላለሁ ካልሽ በሳተናው በኩል በውስጥ አድራሻ መነጋገር እንችላለን፡፡ እንደተረዳሁሽ ለቅን ኢትዮጵያዊነትሽ ግን አመሰግንሻለሁ! ትውልድ ይዳን ብለሽ የጸረ-ዘረኝነት ዘመቻ ብትከፍቺ በወሳኝ መረጃዎች ላግዝሽ እፈልጋለሁ፡፡

ልዑል አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! ከክፉ ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

 

 

4 COMMENTS

 1. ለሰርፀ ደስታ “ዻ” ይባላል ይሄ ፊደል ሳታውቅ ለመተቸት አትሩጥ አቶ ፀሐፊው ።

 2. ዹዺዻዼዽዾ ግእዝ ሶፍትዌር አለ ለምን dha ብለህ ታበላሻለህ?

  አስቴር በዻኔ
  ዘውዴ በዻዻ

  ሺመልስ አብዲሳ
  መረራ ጉዲና

 3. የኦሮሞው ተወላጅ የቋንቋ ሊቀ ሊቃውንት አናሲሞስ ናሲብ(አባ ገመቺስ) እና አስቴር ጋኖ የተባሉት ከዛሬ 230 አመታት በፊት ከዚህ በታች ያሉትን ፊደላት ፈጥረው
  ዸ ዹ ዺ ዻ ዼ ዽ ዾ ዿ
  ተጨማሪ አክለው የፊደል ገበታ አሟልተዋል።
  ቶኣንድኣንድ የኦሮሞ ምሁራን ግዕዝ የኦሮሚፋ ቃላትን ኣይጽፍም በማለቱ በኣለማወቅ በስሕተቱ ገፍተውበታል። ጎዸቱ፣ ቶኮፋዸ፣ ዹፌ፣ ዹጉማ፣ ጀዺ፣ ዻባ፣ ዻራርቱ፣ ባዻዻ፣ ዻዻ፣ ጄዼ፣ ዼራ፣ ዽባፍ፣ ዽባ፣ ነንዾከዼስ ምሳሌዎች ናቸው።
  ይሄንን የተደራጀ ምልአትና ብቃት ያለው የኢትዮይያዊያን በአፍሪካ ብቸኛ የሆነ ፊደላችንን የሰንዳፋው ተወላጅ ሳይንቲስት
  ዶክተር አበራ ሞላ ለ21ደኛው የቴክኖሎጂና
  የኮምፒተር የረቀቀ ዘመን ተራቆ በተጓዳኝ እንዲችል ከዛሬ 30አመታት በፊት ጀምሮ በዩኒብቨርሳል ኮድ/ዩኒ ኮድ አስገብተውታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.