ጉድ ነው ….ማዴቦ ኢሳትን ለዘመዶቹ አስረክቦታል

ኤፍሬም ማዴቦ

የኢሳት 5ቱ ብቸኛ ባለቤቶች ታወቁ። እነዚህ በኢትዮጵያ ብሮድካት የተመዘገቡ የኢሳት ብቸኛ አክሲዮን ባለቤቶች የግንቦት ሰባት አመራር የሆኑት ዶክተር አዲሱ (ገድሉ)
አቶ ኤፍሬም ማዴቦና የኢሳት ዋና ስራ አስኪያጅ የሆነችው ወይዘሮ ሳባ አታሮ የስጋ ዘመድና ወዳጆች መሆናቸው ታውቋል።

ጋዜጠኛ አበበ ገላው እና መሳይ መኮንን ስም ዝርዝራቸውን ይፋ ለማድረግ ቃል ቢገቡም ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በቀረበለት የገንዘብ ድለላና የስራ ዋስትና ለጊዜው ከመናገር ተቆጥቧል።

ጋዜጠኛ አበበ የኢሳት ባለቤቶች አምስቱ መሆናቸውን በፌስቡኩ የገለፀ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ስም ዝርዝሩን ይዞ እንደሚወጣ ለማወቅ ተችሏል።

የኢሳት ቦርድ አባላት ይፋ ባልሆኑበት ሁኔታ የኢሳት ባለቤቶች 5ት ሰዎች መሆናቸው ግርምትን ፈጥሯል። የግንቦት ሰባት አመራሮች ተቋሙን ወደ ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው አዙረውት እያለ ” ለህዝብ አስተላልፈናል” ማለታቸው ከድሮው ማታለላቸው እንዳልወጡ የሚያሳይ ነው። አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ሰሞኑን ይህንን ጉድ ያፍረጠርጠዋል ተብሎ ይጠበቃል።

1 COMMENT

  1. ይህ ወሬ መሆኑ ነው? Satenae ምነው ምነው ማልማት ሳትችሉ ማጥፋት ቻላችሁ! በዘመቻ መውደድ በዘመቻ መጥላት ቢቀርስ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.