ሻለቃ ዳዊት ከችኩል አስተያየት ወደ ተጨማሪ ስተቶች አዘገመ። (ጋሻው ገብሬ)

ከዚህ ቀደም ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ በተጨበጠ መረጃ፤”የከሸፈ መንግስት” ማለት ያለውን መለኪያ አብራርቶ ካገራችን ሁኔታ ጋር ሳያገናዝብ ኢትዮጵያ ያላት የከሸፈ መንግስት ነው በማለት ባደባባይ መናገሩ ግራ ቀኙ እንዲቃወመው እንዳደረገ እናስታውሳለን። እንደሟርትም ተቆጥሮበት ነበር።በዚህ ሰሞን ደግሞ ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ ሌላ ስተት ሲደግም ለመስማት በቅተናል።

ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ

ሻለቃ ዳዊት በዋሽንግቶን ዲ ሲ “ኢትዮጵያ ወዴት?” በሚል የውይይት መድረክ ብዙ ተናግሮ ግን ያሳየው አዲስ አቅጣጫ የለም። አለመታደል ነው።ከዚህ ቀደም “ኢትዮጵያ ያላት የከሸፈ መንግስት ነው” በማለቱ መተቸቱ በጣም የቆጨው ይመስላል።”እኔ አደለሁም መረጃው ከሌላ የጥናት ተቋም የተገኘ ነው” በማለት ሊከላከል ሞክሯል። አንድ ተቋም አንድን ነገር አለው ማለት ያንን ይዞ ያለማስተዋል ወደ አደባባይ መሮጡ ችግር እንደሆነ ለሻለቃ ግልጽ የሆነለት አይመስልም።

መጀመሪያ ሻለቃ ዳዊት በሰፊው ስለቀድሞው ሰራዊት ሲናገር በጥቅሉ ያለው ወታደር ነበርኩ።የቀድሞ ሰራዊት ጀግና ነበር።ላገሩ ሞተ።ተሰዋ።ሰንደቁ እና የአገሩ አንድነት፤ኢትዮጵያዊነቱ እምነቱ ነበር።ብሏል።ሁሉም እውነት ነው።ሻለቃ ዳዊት ባይልውም ይህ አኩሪ ታሪክ ህያው ሆኖ የሚኖር ነው።ይህ ታሪክ ዛሬ በሚቋቋሙት ዘመናይ የጦር ማሰልጠኞች ለሚገቡ የኢትዮጵያ ልጆች ስንቃቸው የሚሆን ነው።የምነታቸውም መሰረት ነው።አዲሱ ትውልድን የሚያንጽ ነው።የወታደሮቹን ጀግንነት መናገር ብቻ ሳይሆን ሰራዊቱ ላይ የተሰራውን ደባም ጨምሮ መናገርም ተገቢ ነው።አላፊነትም መውሰድ ነው።ደግነቱ ደስ የሚያሰኘውም ታሪኩን እንድናውቅ የሚረዱን መጽሀፎች በብዛት መውጣታቸው ነው። ይህን ብለን አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ብናተኩር ተገቢ ነው።

ሻለቃ ዳዊት ስለ አንዷለም አራጌ የኢዜማ ም/ሊቀ መንበር ሲናገር “[አንዱ ዓለም]የፓርቲያቸውን ዓላማ ሲናገር ጠ/ሚኒስትሩን ማገዝ እና የህግ የበላይነት ሰፍኗል” ማለቱን ጠቅሷአል። በመቀጠልም ይህ ከሆነ “[እነ አንዱ ዓለም]ታዲያ ለምን ኦዴፓ አይገቡም?” በማለትም ሻለቃ ዳዊት ለማጣጣል ሞክሯል። ሻለቃ ዳዊት እንዲያው አንዷለም አራጌን ማኳሰስ የሚችል ነው?ማን ለመጣው ለውጥ የሚችለው ሁሉ ያደረገ?ማን ጽናቱን አሳይቷል?ከኢትዮጵያው ውጭ በምቾት ኖሮ ማውራት እና በሳት ተፈትኖ መውጣት በጣም ሩቅ ለእሩቅ አይደሉምን?

ሻለቃ ዳዊት አሁን ያሉት ተቃዋሚዎች ለዓይኑ ካልሞሉ ለምን ኢትዮጵያ ገብቶ አደራጅቶ መንግስትን የሚገዳደር ሪፑብሊካዊ ሆነ ዴሞክራት ወይ ደርጋዊ ፓርቲ አይመሰርትም? ጥያቄው የዶ/ር አቢይ ሆነ ማንም መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ተደራጅቶ ለመታገል ያሉትን መንገዶች ክፍት አድርጓል ወይ ነው? ከዚህ በኋላ ደግሞ ምን ይደረግ ነው? ወሬ ቢበዛ ባአህያ አይጫንም ብሎ ያገራችን ሰው የጨረሰው ነው።የሚዲያ ነጻነት፤(ለማስታወስ ሻለቃ ዳዊት አልሰማ ከሆነ ኢሳት አዲስ አበባ ገብቷል)፤የመሰብሰብ፤የመጻፍ የመደራጀት፤መብቶች በተግባር ተከብረዋል።ኢንተርኔት ልክ እንደ ህወሃት ዘመን ተሸብቦ ዛሬ አልተያዘም። አቶ አንዱ ዓለም ሆነ ኢዜማ ዛሬ ያለውን እድል እንጠቀምና ህዝብን እናስተምር፤ከህዝብም እንማር፤እናደራጅ ቢሉ ለምን ይወቀሳሉ? ሻለቃ ዳዊት ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በሚያቀርቡት የክርክር ደረጀ እያወረደው አይደለም ወይ? ሻለቃ ዳዊት ያልተረዳው ነገር ያለው መንግስት ተቀጥላ ሳይሆኑ ወይም በፍርሀት ሳይዋጡ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ተረድቶ ምን ማድረግ ይቻላል የሚለው ነው? ተግዳሮቱን የሚያመሳቅለው ባንድ በኩል የዴሞክራሲ ትግል በሌላው አገርን እንዳ አገር መሰበት ሆኖብን አይደለም ወይ? ዛሬ ከውጭ ሆኖ መጮህ ሳይሆን ትግሉ ኢትዮጵያ ገብቷል።ነባራዊው ሁኒታ ይህ ነው።የዴሞክራሲ ትግሉን ለማራመድ ባለው ሁኔታ ምን ይመከራል ነው ዋናው ጉዳይ።ለተራ ተወዳጅነትን ማትረፍ (populism) ብዙ ማለት እና ተግባር የተለያዩ ናቸው።ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው ይባል የለ?!

በነአንዱ ዓለም ለመሳለቅ ሻለቃ በስብሰባው ላይ “እዚህ አገር ያላችሁት[አሜሪካን ለማለት ነው] የዴሞክራሲ ፓርቲ የሚሮጠው ሬፑብሊካን ፓርቲውን ለማገዝ ነው” በማለት ተናግሯል።በመሰረቱ ሁለቱ የአሜሪካ ፓርቲዎች ለስልጣን ይወዳደራሉ።በአገር ጉዳይ ይተባበራሉ እንጂ እንዲሁ አይናቆሩም።ሻለቃ እነአንዱ ዓለምን “ተቃዋሚ አይደሉም።” ብሏል።አሁን አቅም አይኖራቸው ይሆናል።ከ“ዓይናችሁ ላፈር” ይልቅ ላገር የሚያስብ በርቱ ማለት አይጠበቅበትም?ብዙ አውቃለሁ ከሚል በተለይ?

እንደመፍትሄ ሻለቃ የሚያቀርበው “የሲቪክ ማህበሮች የተሰባሰቡበት ጉባኤ ተጠርቶ መንግስት እንዲመሰርት ነው” “የሽግግር መንግስት” ! እግዚኦ! ይህ ደግሞ ከየካቲት ስልሳ ስድስት “ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም” መፈክርን ትዝ የሚያሰኝ ነው። ደርግ ምን አንዳደርገ ሻለቃ ረሳው ወይ? ለምን ያኔ ሳይሳካ ቀረ? ዛሬስ ምን እንዲሳካ ያደርገዋል? እንዲሁ ስለ ሽግግር ቢያውሩት ድልድዩ እኮ በወሬ አይገነባም። ሌሎች ነጥቦችን ደግሞ እንይ።

በአንድ አገር ወንጀል ተበራከተ ማለት”የከሸፈ መንግስት” አለ ያስብላል? ኢትዮጵያ ዛሬ የመንን ሆናለች?ሶማሊያን? ደቡብ ሱዳንን ሆናለች? አሁን ደግሞ አዲስ መፈናቀሎች አሉ?በጥቂት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች አሳዛኝ እና አሳፋሪ በሆነ የዘር ግጭት ተጠመዱ ማለት መንግስትን ያከሽፋል?እንዴት ሰለመንግስት ስላጣን ጉዳይ፤የመንግስት ስልጣን በተናጋባቸው ህብረተ ሰብ ስለደረሰ ጉዳት አውቃለሁ፤አማክራለሁ ለሚል ተመራማሪ ይህ እውነት አልታየው ይላል?ተራ ተውዳጅነትን መሻት ህሊናን ማወሩ ግልጽ ነው።

ስለመንግስት አመሰራረት፤የመንግስት ስልጣን አያያዝ ለይቶ ያውቃል የሚባል ሰው እንዴት ሰዎችን ሰብሰብ፤ሰብሰብ በሉና ስልጣን ተረከቡ ብሎ ይናገራል? የዶክተር አቢይን መንግስት መቃወም አንድ ነገር ነው።የሚሰራ የሚመስል አማራጭ ማቅረብ ደግሞ ለብቻው ነው።ምሳሌ ጎረቤት ሱዳን ዛሬ ምን እየሆነ ነው? ከዚህ ብቻ ማስተዋል ይበቃል።አቋራጭ መንገድ የለም።በኢትዮጵያ አገራችን ህዝብ በአገራዊ ዓላማዎች ዙሪያ መደራጀቱ ብቻ ነው የጎሳ እና የዘረኝነትን ቅስም ሰብሮ አገር ሊያድን የሚችል።ለዚህ የሚጥሩ እንዳሉ ማየት አለመቻል ትዝብት ላይ አይጥልም?”እኔ ካላማሰልኩት ወጡ አይጣፍጥም” እይመስልም ወይ?

ዛሬ በኢትዮጵያ በሰፊው ጊዜ ወስዶ የተደራጀ መንግስትን የሚወዳደር ሀይል ገና የለም።እዚያ ደግሞ ይደረሳል።አይቀርም! ህወሃት መሩ መንግስት በነበረበት ወቅት መንገዱን ሁሉ ዘግቶት ቆይቷል።ዛሬ ግን ትልቅ የመደራጀት፤በፖለቲካ (አገራዊ ዓላማ ዙሪያ) መሰባሰብ እድል አለ። ግን ይህ ጥረት ጊዜ የጠይቃል። እንደምሳሌ ለመጥቀስ የህዝቡ ጹኑ ፍላጎት ነውና በኢዜማ መስራቾች በአጭር ጊዜ የተገኘው ውጤት አመርቂ ነው። ይበል የሚያሰኝ ነው።ዝም ብሎ ከመስራት የትገኘ ነው።ይህን ግጥም አድርጎ ክዶ የሻለቃ ዳዊት “ተቃዋሚ የለም” ብሎ ማለት ማንን እንዲበጀው ይሆን? ደግሞስ ተጨባጩን ሁኔታ መካድስ አይሆንም?ለዘረኞች ለጎሰኞች መልካም ምኞት መግለጽስ አይሆንምን?

ሌላው ቪኦኤን አጎበደደ ማለት፤ኢሳትንም ጨምሮ አጎበደደ ማለት ትንሽ አያሳፍም? ሻለቃ ዳዊት የነዚህን ሁለት ተቋሞች ለትግሉ የነበራቸውን ዛሬምያላቸውን አስተዋጾ አሁን በዚህ መንገድ መግለጽ ደግ አይደለም።ሚዲያም መንግስትም ሊተቹ ይግባል።ትችትን ሊቀበሉ ይገባል።ቪኦኤ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ በሆነው የአሜሪካ መንግስት የሚደገፍ ነው።እሳት ግን የህዝብ፤በህዝብ፤ለህዝብ ነው።እሳትን መንካት የተርብ ቤትን መንካት ነው።እኔን ደስ የሚለኝ ከሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ ቀድሞ የሻለቃ ዳዊት በዋሽንግቶን ዲ ሲ ንግግርን ያቀረበ ኢሳት ነው። አጎብዳጅ ይህን ያደርጋል ሻለቃ ?በኢሳት የምኮራው ለዚህ ነው።በአፋዳሽነት ለውጥ አይመጣም።ጊዜው

2 COMMENTS

  1. You Gamada, you guys are so stupid and ignorant people. So greedy, you guys do not even how to govern. Savage, low level greedy people. since you are so trash and ignorant, you are insulting Eskinder. That cheater OLF Abiy Ahmed is so stupid and try to cheat the people. Every one knows about him. You guys are Savage, Savage, Savage people. No brain at all. Power is not by turn, it needs quality mind. Non of you have that leadership quality. Leadership by cheating, killing people, displacing 4 million people, robbing 20 banks, and many more dirty actions are yours and the OLF Abiy’s. This is a shame and trash. Just shut up your dirty mouth. Wow, you guys are like wild animals. No one will keep quite and see you.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.