በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከጠዋቱ 1፡30 አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

ቆሻሻው የተደረመሰው በመንገድ አካባቢ በመሆኑ በምን ያክል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ አልታወቀም፡፡

በአካባቢው በቁፋሮ አንድ የ60 አመት አዛውንት ከነህይወታቸው ለማውጣት ቢቻልም አለርት ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

አሁንም ቆሻሻው የተደረመሰበት አካባቢ የሰው ህይወት ለማዳን በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በኤክስካቫተር የታገዘ ቁፋሮ እየተከናወነ ነው፡፡

በአካባቢው የሚገኘው የቆሻሻ ክምር የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች ተጠግቶ የሚገኝ በመሆኑ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ የአካባቢው ነዋሪዎች ከስፍራው ሊነሱ እንደሚገባ ለመታዘብ ችለናል፡፡

ሪፖርተር፡- ሀምራዊት ብርሀኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.