ከጋዜጠኛ አበበ ገላው ለአቶ ነዓምን ዘለቀ የተሰጠ መልስ

እኔ የታገልኩት ከወያኔ የተሻለ ስርዓት እንዲፈጠር ነው” ጋዜጠኛና የኢሳት ዋና ስራ እስኪያጅ የነበረው አበበ ገላው

**** ለአቶ ነዓምን ዘለቀ የተሰጠ መልስ
ወዳጄ ነአምን ዘለቀ፣

በቦርድ ስም በኢሳት ላይ የተፈጸመውን ተደጋጋሚ ጥፋትና ደባ ሁሉ ስለምታውቀው እየወጣህ ከሁሉ ጋር ባትሟገት ይመረጣል።

እኔን ከሁሉ በላይ ያስገረመኝ ነገር እነ አዲሱ መንገሻ (ገድሉ) የእነርሱ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሊያደርጉኝ የሄዱበት እርቀት ነበር። እኔ ግን አበበ ገላው ሆኜ ተፈጥሬ የማንም ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሆኜ እንደማልሞት ሃላፊነቴን ከመልቀቄ በፊት በደብዳቤ ግልጽ ማድረጌን እንደምታስታውስ እርግጠኛ ነኝ።

እኔ የታገልኩት ከወያኔ የተሻለ ስርአት በአገሬ ለማምጣት እንጂ የማንም ተላላኪ ለመሆን ወይንም ወያኔያዊ አሰራርን ለመድገም አይደለም። ብዙ አታናግረኝ። ለዛሬ ቢበቃ ይሻላል። ከጨለማው ወጥቻለሁ። አመሰግናለሁ!

1 COMMENT

  1. ምራቁን የዋጠ አንድም የለባችሁ። በአደባባይ ተፋለሙ፣ የአበበ ጎራ፣ የነኣምን ጎራ፣ እስቲ ደግሞ ህዝብ ህዝብ የምትሉትን በጒራችሁ ግራ አጋቡት፡፡ ቀድሞውንም “አክቲቪስት” እንጂ የጋዜጠኛ ምግባር ሆነ ስብዕና አልተላበሳችሁ፣ ምን ይደረግ? ህወሓት አቅም እንደሌላችሁ ስለሚያውቅ የአሉባልታ ፍርፋሪ ጣል ያረግላችኋል፣ እንደ ሠፈር ውሻ ትባሉበታላችሁ። “እኔ ግን አበበ ገላው ሆኜ ተፈጥሬ የማንም ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሆኜ እንደማልሞት” ይለናል “ትልቁ ዳቦ!”
    ነኣምን ደግሞ “አሳዳጊ የበደላቸው፣ ስነምግባርም የሌላቸው ድሃ አደግ (የኢኮኖሚ ሳይሆን የአስተዳደግ ድሆች ናቸው)። ከዚህም ቋንቋ በከፋ ምላሽ ለመስጠት አቅቶን ሳይሆን፣ እንደነሱ በአደባባይ ሕዝብንም እንዳናሳፍር፣ እንዳንዘቅጥም በማሰብ ነው። በመጨረሻም ይህን ጫጫታ በማቀጣጠል ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩት በዚህም በዚያም ጎራ የተሰለፉ በአመዛኙ አክራሪና ጽንፈኛ ብሄረተኞች ናቸው” ይለናል!!

    ኢሳት (ነኣምን፣ መሳይ የአንድ ሰሞኑ ሽፍታ፣ አበበ ገላው ወዘተ) አልነበረም ወይ ኤርትራ ድረስ ዘልቆ “ዘራፍ! ኢሳይያስ፣ ዘራፍ! ግንቦት 7” ሲለን የነበረ? ምሥጢር አይደለም እኮ፣ ሁሉ ሲያይ ሲሰማው ነበር! ኢሳት የኢትዮጵያ ህዝብ ዐይንና ጆሮ ነው አላችሁ፣ ጆሮአችሁ ይሰማ የነበረው ህዝብ ሰምቶ የጨረሰውን፣ ወይም ቅዠታችሁ ነው። ያስተላለፋችሁትን ጥናታዊ፣ ቃለምልልስ፣ ትንታኔ ወደ ኋላ ተመልሼ ስመለከት ነበር። ያሳፍራል!! ተንታኝ የተባሉት እነ ኤርምያስና ሌሎች ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው! የኢሳትን ጋዜጠኞች ያገናኛችሁ በህወሓት በደል ደረሰብን ማለታችሁ ነበር፣ ተገናኝታችሁ ስትተያዩ ግን ያ የቆየ ዐመላችሁ ብቅ አለ፣ አንደኛችሁ ከአንደኛችሁ የማትሻሉ፣ መናናቅ፣ በጥቅም ላይ መነካከስ ጀመራችሁ። ጋዜጠኛነት እውነትን አጥብቀው ለሚሹ፣ ለእውነት አጥብቀው ለሚቆሙ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.