አማራና ታሪካዊ ጠላቶቹ (ሙላት በላይ)

ሀ/   የዉጭ ጠላቶች አዉሮፓዊያን  እንዱስትሪዎቻቸዉ  ለማምረት የሚፈልጉት ጥሬ እቃ በርካሽ ዋጋ አፍሪካ ገዝቶ በመዉሰድ እና የተመረተዉን ዉጤት ወደ አገራቸዉ ለመዉሰድ መመላለሻ መንገድ በመፈለጋቸዉ   1ኛ  የሲዊዝ ካናልን    2ኛ  የቀይባህርን መቆጣጣር ሲፈልጉ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ፈለጉ፡፡ ለዚህም እንዲመቻቸዉ የሲዊዝ ካናልን ፈረንሳይና እንግሊዝ በአክሲዮን ገዙና መጠቀም ጀመሩ፡፡

ለዚህም መነሻ ምክንያቱ በእንግሊዝ የጥጥ ፋብሪካ በመስፋፋቱና ሲጠቀሙበት የነበረዉ የደቡብ አሜሪካ ጥጥ በማቆሙ በምትኩ ግብጽ ዉስጥ የአባይን ተፋሰስ ተጠቅሞ ጥጥ ለማምረት ታስቦ ነዉ፡፡ይሁን እንጂ የአባይን ተፋሰስ እንደልብ ለመጠቀም አባይን ከምነጩ መቆጣጠር፤ አባይን ለመቆጣጠር ኢተዮጵያን መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን አምነዉ ኢትዮጵያን በግብጽ እና በኢጣሊያን በኩል በተደጋጋሚ ለመዉረር ሞክረዉ ሰይሳካ ቢቀርም ኢትዮጵያን ለማጥፋት የማይቦዝኑ መሆናቸዉን ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ ሁሉ አዉቀዉና ነቅተዉ መጠበቅ አለባቸዉ፡፡

በ1888ዓ.ም በአደዋ ጦርነት ነጮች በጥቁሮች መሸነፋቸዉ በአፍሪካኖች ላይ የነጻነት ስሜት የጫረ በመሆኑ ለቅኝግዛት እርምጃቸዉ እንቅፋት ሁኖ ማግኘታቸዉ፡፡ለአዉሮፓ ህዝቦች የአፍሪካ ዘመቻ የኋላቀር አገርን ህዝብ ነጻነት ለማስተማር ነዉ የምንሄደዉ የሚሉትን ህዝባቸዉን መልስ ለነጻነት ታጋይ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ በማክሸፉ የነሱ ፕሮፖጋንዳ ዉድቅ በመሆኑ፡፡የአድዋ ድል በኢትዮጵያዊያን ህዝብ መካከል የነበረዉን አንድነት አጉልቶ በማሳየቱ፡፡ለነጮች የታሪክ ስብራት በጥቁር መሸነፋቸዉ የጣሊያን መሸነፍ ነዉ ብለዉ ወሰዱ፡፡ ስለሆነም አማራን የጋራ ጠላት አደረጉ፡፡

ለ/ የዉስጥ ጠላቶች አዉሮፓዊያን ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜና በተደጋጋሚ ለመዉረር በሞከሩበት  ጊዜ ኢተዮጵያን ለማጥፋት ከጠላት ጋር  ተሰልፈዉ አገራቸዉን የወጉ ባንዳዎች ልጆችና የልጅልጆች  የአማራዉ ታሪካዊ ጠላቶች ናቸዉ፡፡ከባንዳ የተወለዱ ባንዳዎች እድገታቸዉ የዉጭ ወራሪዎች እንዴት እንደመጡ፣ ለምን እንደመጡ፣ በማን ድጋፍ እንደተደረገላቸዉ፣ ማን እንደተዋጋቸዉ፣ ለምን እነደተሸነፉ በምደጃ ዙሪያ በአባቶቻቸዉ እና በናቶቻቸዉ እየተማሩ ያደጉት ስለአገር በባእዳን መወረር ቁጭት የሚፈጥር ሳይሆን ለኢትዮጵያ እየተዋጉ ወራሪዉን ማሳደዳቸዉ በዚህም ፍትጊያ ወለጆቻቸዉ የደረሰባቸዉን ጉዳት ከወራሪዎች ሲያገኙት የነበረዉን የገንዘብ ጥቅም መቋረጥ እና የአባቶቻቸዉ ጌቶች ተሸንፈዉ ተመተዉ ኢትዮጵያን ሳያጠፉ መቅረታቸዉ የሚያስቆረቁር ቁጭት ነበር ከእናት ከአባቶቻቸዉ እየተማሩ ያደጉት፡፡

የነዚህ ትዉልድ ነዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከዚህ ደረጃ ያደረሳት፡፡አማራ የኢትዮጵያ ሌላዉ ገጽ በመሆኑ እነዚህ የባንዳ ዘርአዝርት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተጠቀሙበት ስልት በቅድሚያ አማራዉን ማጥፋት ነዉ ብሉዉ የሚመሩበት መረሀ ግብር ነድፈዉ የሚያስፈጽሙበት ህገመንግስት አዉጥተዉ የሚፈጽምና የሚያስፈጽም ባነዳዎችን ገዝተዉ አማራዉንና ንጹሁን ኢትዮጵያዊ እየገደሉ ከዚህ ደረሱ፡፡ አሁንም በመግደል ላይ ያሉት  ወደፊትም ለመግደል በነበረዉ ፖሊሲና ህገመንግስት ለመስራት የመጣዉን የህዝብ አመጽ በጥግንግን እና በሽፍንፍን ሊሰሩበት ሲጥሩ የሚታዩትን የባንዳዎች ዘርአዝርት ዘመናዊ ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የጌቶቻቸዉን ታሪክ ከወላጆቻቸዉ ትርክት ጋር አዛምዶና አጣጥሞ ተግባራዊ ለማድረግ እድል ሰጣቸዉ፤ አመቻቻቸዉ፡፡ የዓለም ህዝብ የካፒታሊስትና የሶሻሊስት እርዮተ ዓለም በሚል ሽኩቻ ዉስጥ ሲገባ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመዉ የኢትዮጵያ አብዮት የሚል መሰረቱ መደብ ሳይሆን የነገድ ጥላቻ የሆነ የግራዉን የፖለቲካ ሀይል በሽፋን  በመጠቀም የአማራዉን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ዓልመዉ በመነሳት እየጨፈጨፉት የሚገኙት፤ ወደ ፊትም በልጆቻቸዉና በልጅ ልጃቻቸዉ ለማስጨፍጨፍ እቅዳቸዉን በመለስ ኑዛዜ ያራዘሙት ፡፡ስለዚህ አማራ ቋሚ የዉጭ እና የዉስጥ ጠላቶች ያሉብህ መሆኑን አዉቀህ በቋ ሚነት  ጠንካራ ድርጅት መመስረት አለብህ፡፡ የአማራ ህልዉና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አማራዉንና ለኢትዮጵያ አንድነትና ደህንንት የሚታገለዉን ሁሉ በወጥነትና በጠነከራ ድርጅት ለማሰባሰብ ያላሳለሰ ጥረት ያደርጋል እያደረገም ነዉ፡፡

ሙላት በላይ

ቁጥር 4 ይቀጥላል

 

2 COMMENTS

  1. ወንድሜ ሙላት – ሃሳብህን እጋራለሁ። ይሁን እንጂ ባንዳ የነበሩት ኤርትራውያንና ትግሬዎች ብቻ አልነበሩም። አማሮችም ነበሩበት። ማን እና ከየት ለሚለው ግን ጠለቅ ያለ ምርምር ያሻል። እዚህ ላይ ማየት የሚኖርብን አንድ ነገር አለ። ሰው በኖረበት ዘመን ነው መመዘን ያለበት። እኛ በዛሬ ላይ ቆመን ይህን እና ያን ብንል በእነርሱ ጫማ ስላልሄድን የምንለው ሁሉ ሚዛናዊ አይሆንም። ግና ዳሩ ጥቁር ጥቁርን እንዲገድለው ነጮች ይገለገሉባቸው የነበሩት ባንዳዎች ከሁሉም አቅጣጫ የመጡ ነበሩ። ለምሳሌ ብርሃኑ ድንቄ “አልቦ ዘመድ” በተባለው መጽሃፍቸው ላይ በአዲስ አበባ በጣሊያን የታጠቁ ኤርትራውያን ከውጭ ቤት ዘግተው በሰዎች ላይ እሳት ሲለኩሱ ማየታቸውን ጽፈዋል። ያኔ እሳቸው ገና የቄስ ትምህርት ቤት ተማሪ ነበሩ። በሌላ መልኩ ከሊቢያ፤ ከቀድሞዋ ኢጣሊያ ሱማሊያ የተወጣጡ ታጣቂ ሃይሎች በኢትዮጵያ በጣሊያን መሪነት ሲገሉና ሲዘርፉ እንደነበሩ በመረጃ የተደገፈ ሃቅ ነው።
    በመሰረቱ ነጩ ዓለም ለጥቁሩ ህዝብ ደንታ የለውም። ዛሬም ያ ሃሳባቸው እንዳለ ነው። ምን አልባት በሚቀጥለው መጣጥፍህ ላይ ታነሳው ይሆናል:: በእኔ ግምት ጣሊያን በአማራም ሆነ በሃገራችን ላይ ከበደለው በደል በላይ የበደሉንን ደርግ፤ ሻብያና ወያኔ ናቸው። አሉ የሚባሉ የሃገሪቱ ሴትና ወንዶች ልጆችን የመነጠሩና ዘረኝነትና የጎሳ ፓለቲካን ለህዝባችን ያስታጠቁት ሻቢያና ወያኔ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ይህን ጉዳይ በሚቀጥለው ላይ ልታነሳው ስለምትችል ያኔ ልመለስበት። ለአሁኑ ይብቃኝ፡

  2. ዋናው የአማራው ጠላትም ሆነ የዓለም ጠላት የጽዮኒዝም ርዕዮተዓለም ነው። የጽዮኒዝምን ርዕዮተዓለም የማታውቅ ከሆነ ስለአማራው ጠላት በጭራሽ ልታውቅ አትችልም።
    ደርግ፤ሻብያ፤ወያኔ፤ አሁን ደግሞ የአብይ አብዮት እነዚህ ሁሉ የሚመሩበት የጽዮኒዝም ርዕዮተዓለም ነው። የዚህን ርዕዮተዓለም እንዴት አድርጐ እንደሚገድል ፤እንዴት በግሩፕ እንደሚሰባሰቡ፤ እንዴት አድርገው በዓለም ዙሪያ እርስ በርሳቸው እንደሚናበቡ፤ በየትኛውም የሃይማኖት፤የነጻ አውጭ ግንባር ውስጥ፤ የማህበራዊ ሜድያ ውስጥ እንዴት እንደሚቀሳቀሱና መርሃቸውን ማጥናትና ማወቅ ያስፈልጋል። ይሄንን ሳታውቅ ፖለቲካ ውስጥ ገብቼ እጫወታለሁ ብትል ባላወቅሀው መንገድ ህይወትህን ይቀጥፉታል።
    አንተ ጠላቴ የትግሬ ወያኔ ነው ብለህ ስጠብቅ እነሱ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለ የዙሉ ባንዳ ይልክብሃል። አንተ ደርግ ነው ብለህ ጠላቴ ስጠብቅ የአረብ ጽዮናዊ ይጠብቅሃል። አንተ ወያኔ ነው ጠላቴ ብለህ ስጠብቅ የራስህ የፓርቲ ሊቀመንበር የእነርሱ አባል ሆኖ ያለውን ሚስጥር አሳልፎ ሰጥቶ ባልጠበከው መንገድ ወይ ጦር ሜዳ ላይ ወይ አውቶብስ ማቆሚያ አውቶብስ ስጠብቅ ሊያስመታህ፤ሊያስገድልህ ይችላል። የእነሱን ጥቅም የሚጻረር ፖለቲከኛ ሆነህ አንተ አሞኛል ውጭ ሄጄ እታከማለሁ ብለህ ስንት ገንዘብ ከከሰከስክህ በኋላ እዛ ላለው ነፍሰ ገዳይ ሰርጀር ድብቅ ትእዛዝ ይሰጠዋል ያንተን ህይወት ለማጥፋት ፥ማለት ገንዘብም ተቀብለው የሰው ህይወትን ያጠፋሉ። ስለዚህ እንዴት እንደሚያጠቁና መርሃቸውን ማወቅ ያስፈልጋል። ጠላትን መርሆቹን በሙሉ ማወቅ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ጋዜጠኛ ደምስን ማን ገደለው? ለሚለው እስካሁን መልስ የለም። ጋዜጠኛ ደምስ የኮሙኒዝሙንና የካፒታሊዝሙን የፖለቲካ ጨዋታ ማን እንደሚመራው አሳምሮ ያውቅ ነበር። ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ገዳዩ ያልታወቀውና ሚስጥር የሆነው።
    የእነዚህ ሰዎች ዋናው ዓላማቸው ምድርን በሙሉ መቆጣጠርና የጠፋውን አጥፍተው ሌላውን ባሪያ ማድረግ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.