በዘገበልን መሰረት ከአዲስ አበባ አልፈው ባህርዳር ውስትምጥ ታላቅ ጉባኤ ለማድረግ ይንቀሳቀሳል

ስለዝህ ጅግ በጣም የተሳካ ጉባኤ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን እስክንድርና ጓደኞቹ ኢትዮጵያ ለምታደርገው ሃገረ መንግስት ምስረታ በጎ አስተዋጾ በማድረግ ያንን ለዘመናት የተበደለውን ሕዝብ እንዲያረጋጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ባህር ዳር ለአዲስ አበባ ባላአደራ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበች፡፡

ባለአደራ ም/ቤቱ ጥሪዉን ተቀብሎ ወደባህር ዳር ሊጓዝ ነው፡፡

የአ/አ/ባ/ም/ቤት ቀደም ብሎ በወሰነው ውሳኔ መሠረት፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተጓዘ ከህዝብ ጋር ለመወያየት እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡
በዚህም መሠረት፣ ቅድሚያ ሰጥቶ ተመሳሳይ የመብት ጥያቄ ባላቸው ድሬዳዋ ከተማ እና ሐረር ክልል ትስስሮችን ለመጀመር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፤ ቅድመ ዝግጅቱ እንዳለቀም የምክር ቤቱ አባላት ወደ ድሬዳዋና ሐረር ተንቀሳቅሰው ከህዝብ ጋር እየተወያዩ የትብብር መሠረት ይጥላሉ።
ለአሁኑ ግን፣ የምክር ቤቱ አባላት በባህር ዳር ከህዝብ በተውጣጣ አስተባባሪ አካላት በተደረገለት ጥሪ መሠረት፣ ሰኔ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ በህር ዳር በመጓዝ ከህዝብ ጋር እንደሚወያይ ለማሳወቅ ይወዳል.፡፡

የባለአደራ ምክር ቤቱ፣ የሀገሪቱን ፀጥታና መረጋጋት ግምት ውስጥ እያስገባ፣ ወደ ተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በመጓዝ ተመሳሳይ ህዝባዊ ውይይቶችን ለማድረግ ዕቅዶችን እየነደፈ ስለሚገኝ፣በሌሎች ከተሞች የምትገኙ ሁሉ በትዕግሥት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አዲስ አበባ
ሰኔ 4 2011 ዓ.ም.

1 COMMENT

  1. ድንቅ ነው የእስክንድርና ባልደረቦቹ በየከተሞች ተመሳሳይ ውይይት ማድረግ። አማራ በፈጠራቸው ከተሞች፣ ደሙን አፍሦሶ ባቆማት ሃገር ባይተዋር አይሆንምና። ኢስኪያልፍ ቢያለፋም፣ ድል የባለበቱ መሆኑ አይቀሬ ነው። እግዜር/አልህ ይርዳን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.