የወያኔ የስምምነት ሰነድ/ህገ መንግስት (ሙላት በላይ

በበርሀ በዉንብድና ዘመን በኢሳይያስ አፈወርቄ በመለስ ዜናዊ እና በሌነጮ ለታ ኢትዮጵያ እንዴት አድርገን እናጥፋት፣ ይህን የጥፋት ዘመቻችን ለማፋጠን ለጥፋተ ሥራችን እንቅፋት የሚሆነዉን  አማራ ከሌሎች ብሄረሰቦች እያጣላ ለአፈጻጸም የጋራናል ያስማማናል ያመቸናል የሚሉትን የዉልሰነድ ጽፈዉ የተጠቀሙበትን ቤተመንግስት ሲገቡ ከአማራዉ ጋር ያጣሏቸዉን ገለሰቦች አሰባስበዉ ህገመንግስት በሚል ሰይመዉ ኢትዮጵያንና አማራዉን በማነጣጠል እየአጠፉበት ነዉ፡፡ ወደፊትም ሊያጠፉበት አቅደዋል ለዚህም ነዉ ህገመንግስቱ የሚቀየረዉ በኛ መቃብር ላይ ነዉ የሚባለዉ፡፡ይህ የወያኔና የኦነግን የስምምነት ሰነድ ምን እንደሚል በአጭሩ አናያለን፡፡ አያየንም እንገመግማለን፡፡ ተወያይተንም ለጋራ ዉሳኔ እንበቃለን፡፡

የወያኔ የስምምነት ሰነድ/ህገመንግስት/ አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤት ናቸዉ ይላል ፡፡ ይህ ሰነድ እዉቅና የሰጠዉና የሚሰጠዉ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ለሚላቸዉ ቡድኖች ነዉ፡፡ ለግልሰብ ነጻነት ፣መብት፣ እዉቅና አልሰጠም ምክንያቱም ገለሰብ ዘርን ጎሳን ብሄረሰብን ሰለማይለይ ፍቅርን እነጂ ጥላቻን ሰለማያመጣ በዚህም የወያኔን  የማጣላት የመበታተን እቅድ ሰለ ማይፈጸም፡፡በወያኔ ህገመንግስት ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በግለሰብ ደረጃ የኔ ነዉ የሚለዉ ምንም ነገር የለም የክልል መንግስታት በየክልላቸዉ የስልጣን ባለቤትነት የማን እንደሆነ

መብትና እዉቅና የሰጠዉ የክልሉ ስም መጠሪያ ለሆኑት ነገዶች ነዉ፡፡ በአማራ አማራ በትግሬ ትግሬ በኦሮሞ ኦሮሞ ወዘተ ሲሆኑ ከዚህ በተቃራኒ በአማራና በጋምቤላ የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ናቸዉ ይላል፡፡ለምንድን ነዉ የአማራዉ ህገ ከሌሎች የተለየዉ መልሱን እያንዳንዱ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ አንብቦና መርምሮ እንዲደርስበት ይፈለጋል፡፡

የወያኔ እና የኦነግ የስምምነት ሰነድ ወደየ ክልሎች ሲወረድ እያንዳንዱ ነገድና ጎሳ አማራዉን ተከታትሎ እንዲያጠፋዉ በእቅድ የተያዘ በመሆኑ አማራዉ በየክልሎች የሥልጣንና የመብት ባለቤትነት መበት እንዳይኖረዉ ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት አማራዉ ከቤንሻንጉል ጉምዝ፣ከጂማ ዞን ከወለጋ ከኢሊባቡር ከሀረር ወዘተ እንደ ዱር አዉሬ እየታደነ በቀስት ፣በገጀራ፣ በጥይት፣በመርዝ  እየተገደለ እስካሁን የኖረዉ ወደፊትም እንዲኖር እየተፈለገ ያለዉ ይህ ሁሉ የተፈጸመዉና ወደፊትም ሊፈጸም የታቀደዉ በወያኔዎች የማጥፊያ ስምምነት ሰነድ /ህገመንግስት/ ነዉ፡፡ታዲያ ተጨፍጫፊዉ ኢትዮጵያዊ ምን ያስባል መልሱን ለአንባቢያን ለዉይይት ትተነዋል፡፡

የአማራ ክልል በምእራፍ 2 አንቀጽ 8 ነኡስ አንቀጽ 1 የአማራ ክልል ሀዝቦች የብሄራዊ ክልላዊ መንግስቱ የበላይ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸዉ ይላል፤ ከዚህላይ ለሁሉም ነዋሪዎች እኩል መብት ሰጥቷል፤ በዚህ ላይ አማራዉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን አቀፎና ደግፎ እንዲይዝ በመደረጉ አማራዉ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ጥፋት የማይፈልጉ ሁሉ እጅግ በጣም ደስተኞች መሆናቸዉን የአማራ ህልዉና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ያምናል፡፡በዚህ የአንድነት ኑሮም ደስተኛ መሆኑንም ያረጋግጣል፡፡

ሙላት በላይ

ቁጥር 6 ይቀጥላል

 

 

 

1 COMMENT

 1. ኢትዮጵያን ለማጥፋት ፣ አይነተኛው እንቅፋት አማራው በመሆኑ፣ ካላፉት 123 አማእታት ወዲህ (ከአድዋ ድል በሁዋላ) በባእዳን የተደመደመ ጉዳይ ነው። በአድዋም ሆነ በማይጨው ፣ ጣልያን 100፣ 000 ቅጥረኛ ባንዶችን የሰበሰበው ከየት እንደሆነ አገር ያወቀው ጠሃይ የሞቀው ሃቅ ነው።
  ወያኔእና ሻብያ የነኛ ምንደኞች ፣ ክብረቢስ አገር የሸጡ ወንጀለኞች ዝርዮች ናቸው፣።
  የኦሮሞ መነአጆዎች ኦነጎች ደግሞ፣ የታላላቅ አገር መስራቾችን በሃሰት የሚወነጅሉ፣ የአልባሌ መንፈስ ተገዢዎች ናቸው ። በነርሱ አንደበት ሊደፈሩ የማይገባቸውን ጀግኖቻችንን እነ ራስ ጎበናን፣ ፊታውራሪ ሃብተ ጊዮርጊስን፣ ደጃች ባልቻን፣ ራስ ቱሉን፣ ደጃች ገረሱ ዱኪን፣ ገነራል ጃገማ ኬሎን፣ እና ኮሎነል አብዲሳ አጋን ውዝት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ እያብጠለጠሉ፣ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አድረዋል።
  አዎ የማራን ሴቶች ሳይቀር በጠላት የ አምስት አመት ወረራ ያሳርድ እንደነበረው፣ እንደ ከፋው ገዥ አባ ጆቢር ፣ የኦነግ አረመኔዎች የበርካታ ሺህ ያልታጠቀን፣ ያልጠረጠረን አማራ ለ 28 አመታት አስጨፍጭፈዋል። ዛሬም በ አቢይ መንግስት ፍጅቱና ስደቱ ከአማራው አልፎ፣ ሌሎች ዎገኖቻችንንም ሚሊዎን የሚጠጉ ጌዶዎችን እያመሰ ነው።
  በምናባቸው ለፈጠሯት ኦሮምያቸው ፣ ተወላጁን አባረው ፈጅተው መሬት መያዛቸው ነው። ዎራሪ አውሮጳውያን ዛሬ ስሜን ኢና ደቡብ አሜሪካን እንዲሁም ኡስትራሊአና ኒውዚላንድን እንደወረሱ ሰምተዋል፣ አይተዋልም።
  አዲስ አበባን ከተማቸው ለማድረግ ሲባል ፣ በካባቢውን ከኦሮም ውጭ የሆነውን ነዋሪ መመንጠር አስፈላጊ ነው በሚል ስሌት ነው በቡራዩ፣ በሱሉልታ፣ በሰንዳፋ ኢትዮጵያውያን የሚፈናቅሉት፣፣
  ስለዚህ ዛሬ እስክንድርንና ድፍን የአዲስ አበባን ህዝብ የህልውና ትግል ፣ የኦሮሞው የአቢይ መንግስት ለማፈን የሚውተረተረው፣ ለዚህ አላማ ነው። ምን ያህል እንደተደፈረ እኔን መሰል እትዮጵያዊ ግልዕ ነው፤።
  ኢስካፍንጫቸው ታጠቀው የመጡብንን የውጭ ጠላቶች የመከተ ክንድ፣ ዛሬ ድንገት አይጠፋም። ለእናት እትዮጵያ ስንል ብዙ በተሸከምን ፣ ለዘመናት አልቀናል፣ ነደናል።
  እትዮጵያን አላተረፍንም። “ለዳር ሲሳሱ የመሃሉን ይነሱ” እንዲሉ፣ ባቆማንት ሃገር እንኖራለን። ለዚያ ፍልሚያ ደግሞ አፈር ቅጠሉ አብሮን ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.