አስመጪና ላኪዎች በዶላር እጥረት ተማረሩ

በሃገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ የዶላር እጥረት አስመጪና ላኪዎችን ማማረሩን ዘጋቢያችን ምንጮቹች ዋቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ የላከው ዜና ያመለክታል።
የቡና ኤክስፖርት ከቆመ ወራት ተቆጥረዋል፣ በሃገሪቱ ያሉ ባንኮች ዶላር ሽያጭ አቁመዋል የሚለው ዘጋቢያችን፣ ከዲያስፖራው የሚገኘውን የውጭ ዶላር ገቢ ለማሳደግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አዘጋጅቷል ብለአል።
በአስመጪና ላኪ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ዶላር ማገኘት ያልቻሉበት መንገድ አልተገለጸላቸውም። ይሁን እንጅ የቡና ዋጋ መውደቅ፣ የቆዳና ሌጦ ዋጋ መውረድ እንዲሁም የሰሊጥ መበላሸት የዶላር እጥረት መፍጠሩን መረጃዎች ያሳያሉ።
የዶላር እጥረቱን ተከትሎ ስራ መጀመር የነበረባቸው ፋብሪካዎች ስራ ሳይጀምሩ ቀርተዋል። የዘይትና የስኳር አቅርቦቱም ቀንሷል። በግል የተያዙ ብቻ ሳይሆን መንግስት የሚያካሂዳቸው ግንባታዎችም በዶላር እጥረት እየቆሙ ነው።
መንግስት በቅርቡ ከአለማቀፍ አባዳሪ የግል ብንኮች 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መበደሩ ይታወሳል።

Source:: Ethsat

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.