ኦሮምኛ በግእዝ ፊደል የመጻፉን ጥቅም- ከቋንቋ ምሁሩ ዶ/ር ጌታቸው ሃይሌ

የኢትዮጵያ ፊደል፤

ስለ ኢትዮጵያ ፊደል ሌላ ጊዜ ጽፌ ሌላ ቦታ ያሳተምኩትን በመጠኑ ለዋውጬ ላካፍላችሁ።

ኢትዮጵያ የትም ከሌላ አገር የማይገኝ የራሷ ፊደል አላት። የሩቅ ምሥራቁን (የቻይናን፥ የኮሪያን . . .) ለብቻ ትተን የቀረውን ስናየው የተለያዩ ቋንቋዎች ፊደሎቻቸው ዝምድና እንዳላቸው ምልክት እናያለን። በላቲንና በኢትዮጵያ ፊደል መካከል ያለው ዝምድና እንኳን ደብዛው ፈጽሞ አልጠፋም። ለምሳሌ፥ እነዚህን እናስተያያቸው፤ አ (A), ተ (t), መ (m), ወ (w), ቀ (q).

እዚህ ላይ የኦሮሞ ልሂቃን ቢሰሙት የማይወዱት ነገር አለ። ቁቤ የሚሉት የላቲን ፊደል በብዙ ተዘዋዋሪ ከኛ ፊደል የተወሰደ ነው።

ግን ከፊደሎች ሁሉ ከኢትዮጵያው ፊደል ጋር የበለጠ ዝምድና የሚታይበት “የደቡብ ዐረብ” ወይም “የሳባውያን” የሚባለው ፊደል ነው። ሆኖም፥ ብዙ ጥናት ሳይደረግ፥ የፊደሎችን ተመሳሳይነት በማየት ብቻ፥ “ዝምድናቸው አንዱ የሌላውን ከመውሰድ የመጣ ነው” ማለት አይቻልም። ከተቻለ፥ የኢትዮጵያው ከሳባው ወሰደ ከማለት ይልቅ የሳባው ከኢትዮጵያው ቢወስድ ነው የማይባልበት ምክንያት የለም። “አንድ ጥንታዊ ሕዝብ ለራሱ ቋንቋ የፈጠረውን ፊደል ሌሎች ሕዝቦች ወስደው ለራሳቸው ቋንቋ መጻፊያ እንዲሆን አስተካክለውታል። ከነዚህ ሕዝቦች ውስጥ ኢትዮጵያውያንና ሳባውያን ይገኙበታል” ማለትም ይቻላል።

ስለ ዓለም ፊደሎች ስንነጋገር በኢትዮጵያ ፊደል ላይ አንድ የሚገርም ነገር እናያለን፤ የሌሎቹ ፊደሎች በ “አ” ጀምረው ሲዘልቁ፥ የኢትዮጵያው የሚጀምረው በ “ሀ” ነው። ይኸ አሰላለፍ ምን ምስጢር ይዞ ይሆን? መልሱ አልተገኘም።

ሌላ ተዛማጅ ጥያቄ፥ በያንዳንዱ ቋንቋ ውስጥ ያሉ የቋንቋ ድምፆች እጅግ የተወሰኑ ከሆኑና ማንኛውም ሕዝብ ለቋንቋው ፊደል የሚቀርጸው ለአንድ ድምፅ አንድ ፊደል ብቻ ከሆነ፥ ታዲያ በአማርኛ ውስጥ ለአንድ ድምፅ ለምን ሁለት ፊደል (አ፥ ዐ፤ ሰ፥ ሠ፤ ፀ፥ ጸ)፥ እንዲያውም ሦስት ፊደል (ሀ፥ ሐ፥ ኀ) አስፈለገ? ፊደሉ የግዕዝ ፊደል ነው። ግዕዝ ፊደል የቀረጸ ጊዜ እነዚህ ፊደሎች የሚያገለግሏቸው ድምፆች ነበሩት። ድምፆቹን ትናጋው ሊያሰማቸው የማይችል ሕዝብ አማራ ስለሆነ ጠፍተዋል። ታዲያ ፊደሎቹን አሁን ምን እናድርጋቸው? እርግጥ፥ “ሐሳብ፥ ኀይል፥ ዐይን፥ ሠናይ፥ ፀሓይ” እያልን በመጻፍ ፈንታ “ሀሳብ፥ ሀይል፥ አይን፥ ሰናይ፥ ጸሀይ” እያልን ልንጽፍ እንችላለን። እንዲያውም፥ ሐሳቡ ቀርቦ ተቀባይነት እያገኘ ሄዷል። ግን በእነዚህ ፊደሎች የተጻፉትን የጥንት መጻሕፍት ምን እናድርጋቸው? እነሱንም እንፋቃቸው? ቃላቱ አማርኛ ውስጥም አሉ፤ ሐሳብ፥ ኀይል፥ ዐይን፥ ፀሐይ፥ ወዘተ. ዛሬም ጥንትም አማርኛ ናቸው። እነዚህንና መሰሎቻቸው ቃላትን ስንጽፍ ምርጫችን የጥንትነታቸውን አክበረን እንደዱሮው መጻፍ፥ ወይም የዱሮ መልካቸውን ማስቀረት ነው። እንደዱሮው መጻፍ spelling መማርንና ዕውቀትን ይጠይቃል፤ ማበላሸት ግን ማንም ይችልበታል።

ምሥጢሩ ትልቅ ነው። ከሌላ ቦታ እንደጻፍኩት፥ የአሜሪካን እንግሊዝኛና የእንግሊዞች እንግሊዝኛ አነገገር ይለያል፤ ለምን? የአሜሪካን እንግሊዝኛ ከእንግሊዞች እንግሊዝኛ (ከኦክስፎርድ እንግሊዝኛ) የተለየው እንግሊዞች ያልነበሩ ሕዝቦች እንግሊዝኛ እየተነጋገሩ አሜሪካኖች ስለሆኑ ነው። የግዕዙና የአማርኛውም ሁኔታ እንደዚሁ ነው። የሴም ቋንቋ (ትግርኛ፥ አማርኛ፥ ወዘተ.) የማይናገሩ ኢትዮጵያውያን (ዶርዜ፥ ሐዲያ፥ አዳል፥ ሱማሌ፥ ኦሮሞ) አማርኛ እየተናገሩ አማራዎች ስለሆኑ ነው። የነሱ ቋንቋና ድምፅ ተጽዕኖ በግዕዝና በአማርኛ አነጋገር፥ በቃላት፥ በሰዋስው ላይ ለውጥ አምጥቷል። በለውጡ ከማጕረምረም ሕዝባችን በአማርኛ አማካይነት ወደ አንድነት በመምጣቱ መደሰቱ ይበልጣል።

የኢትዮጵያ ፊደልና የኢትዮጵያ ቋንቋዎች፤

የኢትዮጵያ ፊደል ከምንጩ የተቀዳውና የተስተካከለው የግዕዝን ቋንቋ ለመጻፊያ ነበር። በዚያ መሠረት፥ ግዕዝን እስከዛሬ እያገለገለ ነው። ከዚያ ቀጥሎ የአማርኛ መገናኛነት ሲስፋፋና የትምህርቱ ኀላፊዎች፥ ማለትም አስተማሪዎቹና ደራሲዎቹ፥ አማሮች ሲሆኑና፥ በዚያ ላይ የውጪ ሰዎች ሃይማኖታቸውን በአማርኛ ማስተማር ሲጀምሩ፥ ላለመቀደም፥ በአማርኛ መጻፍ አስፈለገ። “አንድ ቋንቋ የሌላውን ፊደል መውሰድ ሲያስፈልገው፥ መምህራኑ የሚወስዱት አጠገባቸው ያገኙትን ፊደል ነው” ባልኩት መሠረት፥ የአማራ መምህራን የግዕዝን ፊደል ወሰዱ።

የወሰዱትን የግዕዝ ፊደል ለአማርኛ እንደሚያስፈልገው አስተካክለው እነሆ እየሠራንበት ነው። ማስተካከል ማለት የግዕዝ ፊደል ኆኅያት ለአማርኛ ቋንቋ አልበቃ ስላለ የሚያባቁ ኆኄያት ፈጠሩለት ማለት ነው። ለምሳሌ፥ በግዕዝ ፊደል “ጀመረ”፥ “ጨረሰ”፥ “ሸኘ”፥ “ቸኮለ” ብሎ መጻፍ አይቻልም። ምክንያቱን በግዕዝ ፊደል ውስጥ “ጀ”፥ “ጨ”፥ “ሸ” ፥ “ኘ”፥ “ቸ” የሉም። ስላላስፈለገው አልፈጠራቸውም። አማሮች የነዚህ ኆኄዎች ምንጮች የቶቹ የግዕዝ ኆኄዎች እንደሆኑ አጥንተው፥ “ጀ”ን ከ “ደ”፥ “ጨ”ን ከ “ጠ”፥ “ሸ”ን ከ “ሰ”፥ “ኘ”ን ከ ”ነ”፥ “ቸ”ን ከ “ተ” አስወለዱ። (ውሰድ–› ውሰጂ፤ ጠጣ –› ጠጪ፤ ተመለስ –› ተመለሺ፤ በተነ–› በትኚ)።

ማንኛውም ፊደል ለማንኛውም ቋንቋ መጻፊያ ሊሆን ይችላል ባልኩት መሠረት፥ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በገበያ ላይ ካሉት ፊደሎች (የግሪክ፥ የላቲን፥ የዐረብኛ፥ የቻይና፥የኢትዮጵያ . . . ፊደሎች) የትኛውንም ፊደል መርጠው ሊወስዱ ይችላሉ። ግን በሚወሰድበት ጊዜ፥ እንኳን ፊደልን ያህል ትልቅ ነገር ቀርቶ፥ ነገ አርጅቶ የሚጣል ዕቃ እንኳን የሚገዛው አማርጦ፥ አገላብጦ አይቶ፥ ይበልጥ የሚስማማ የመሰለው ተመርጦ ነው። አውጥተን አውርደን፥ የሩቁን አስበን ስናየው፥ ምርጫው ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች መጻፊያ ከሆነ፥ በብዙ ምክንያት፥ የኢትዮጵያ ፊደል ከመምረጥ የተሻለ ምርጫ የለም።

አንደኛ፥ አጻጻፋችን ከቋንቋው ጋር አብሮ ይሄዳል። ቋንቋው ሲለወጥ አጻጻፉም (the Spelling) አብሮ ይለወጣል፤ ተለውጦ በጊዜው ትክክል የሆነው ቃል ይጻፋል። ለምሳሌ፥ ዱሮ “ኸየት”፥ “አንቲ” ነበር የሚባለው። ወደሸዋ ስንመጣ “ኸየት” ተለውጦ “ከየት” ሆኗል፤ “አንቲ” ከሁሉም አገር “አንቺ” ሆኗል። አጻጻፉ አብሮ የማይለወጥ ቢሆን ኖሮ፥ አሁንም የትም ቦታ “ኸየት”፥ “አንቲ” እያልን እየጻፍን፥ “ከየት”፥ “አንቺ” እያልን (ያልተጻፈውን) እናነብ ነበር። ምሳሌውን ከእንግሊዝኛ ባመጣ የበለጠ ይብራራ ይሆናል። ለምሳሌ፥ በእንግሊዝኛ laugh, doubt የሚሉ ቃላት አሉ። የቃላቱ ድምፅ ተለውጦ ሳለ፥ አጻጻፉ (the spelling) ባለመለወጡ አሁንም የሚጻፈው laugh, doubt እየተባለ ነው። የቃላቱ ድምፅ ግን ተለውጦ laf, dout ሆነዋል። የአጻጻፍ ልምዳችን የተማርነውን ሳይሆን የምንሰማውን ነው።

የአማርኛ ፊደል የሚመረጥበት ሁለተኛው ምክንያት “ሳይቸግር ጤፍ ብድር” የሚባለው ነው። የሚፈለገው ለመጻፍ ከሆነ የሌላ አገር ፊደል የሚመረጥበት ምክንያት የለም። ስለኦሮምኛ አጻጻፍ በምንወያይበት ጊዜ፥ “የላቲኑ ፊደል የተመረጠው፥ በጥናት ላይ ተመርኩዞ ነው” የሚለው ክርክር ይነሣል። አያዋጣም፤ “የአማራ ፊደል አንፈልግም” ብሎ እቅጩን መናገር እውነተኛ ያደርጋል። አጥኒዎቹ ምርጫ የሚደረገው ለመጻፍ መሆኑን ብቻ ዓላማቸው ያደረዱ ገለልተኞች የቋንቋ ምሁራን መሆን አለባቸው።

ሦስተኛው ምክንያት፥ ብሔራዊ አንድነት ነው። አንድ አገር፥ አንድ ፊደል፥ አንድ ባንዲራ ይመረጣል።

አራተኛው ምክንያት፥ አንድ የተማረና መማር ያለበት ዜጋ ቋንቋው ያልሆነ ሌላ የኢትዮጵያ ቋንቋ ለመማር ቢፈልግ አዲስ ፊደልና አዲስ አነባበብ መማር አያስፈልገውም።
የኢትዮጵያ ፊደል የሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መጻፊያ እንዲሆን ተሞክሮ ፈተና አልፏል። “ወድቀሃል” አንበለው። “የአማራን ባህል አታሳዩን፥ አታሰሙን” ከሚሉ ሰዎች መካከል፥ “የኢትዮጵያ ፊደል እንኳን ለሌላዎቹ ቋንቋዎች ለአማርኛም አይስማማውም” የሚሉ አሉ። እንዲህ የሚሉት ወሬ ሰምተው ፊደላችንን ለማጣጣል እንዲመቻቸው ነው እንጂ፥ እውነት ለአማርኛ አዝነውለት ወይም በአማርኛ የሚጽፉ ሰዎች ሲቸገሩ አይተው አይደለም። የትኛውን የግዕዝና የአማርኛ መጽሐፍ ነው በኢትዮጵያ ፊደል ስለተጻፈ ሳናነበው ያለፍነው? አንዳንዶቹን መጻሕፍትማ ከመውደዳችን የተነሣ፥ ከእጃችን እንዳይወጡ እስከምንፈልግ ድረስ እንንከባከባቸዋለን።

አንባቢ ልብ ብሎት ከሆነ፥ “ፊደል የሚመረጠው ለመጻፍ ከሆነ” የሚል ሐረግ ደጋግሜ ጽፌያለሁ። ፖለቲካም አለበት ለማለት ነው። ለአማርኛ ባህል ቢደብቁት የማይደበቅ፥ እንደ እሳት የሚያቃጥል ጥላቻ አለ። “ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወገጥ” እንደሚሉ፥ አማርኛም በአማሮች ላይ ከተሰነዘረው ጥላቻ ገፈት ቀማሽ ሆኗል። የአማርኛን ቋንቋ ለልጆቻችን አናስተምርም ማለት የፍቅርና የአብሮ መኖር ምልክት አይደለም። አንዳንዶቹማ፥ “ኦሮሞዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ተሸክመው ማይጨው የዘመቱት ተገድደው ነው” እስከ ማለት ደርሰዋል። ይህን ለማለት እነ ክቡር ጀኔራል ጃገማ ኬሎ እስኪያልፉ ድረስ መታገሥ አልቻሉም።

“የኦሮሞ ሊቃውንት ባደረጉት ጥናት መሠረት ለኦሮምኛ የሚስማማውን ፊደል (ላቲንን) መርጠውለታል፤ ይህ ያለቀ፥ የደቀቀ ጉዳይ ነው፤ ኦሮሞ ያልሆኑትን የሚገዳቸው ጉዳይ አይደለም” የሚሉም ሰምቻለሁ። የኦሮሞ ሊቃውንት በኢትዮጵያው ፊደል ላይ ያገኙት ዋናው ድክመት “ለሚጠብቅ ድምፅ ምልክት የለውም” የሚል ነው። ሊቃውንቱ የቋንቋ ተመራማሪዎች ከሆኑ፥ ላቲን እንኳን ለሚጠብቅ ድምፅ ምልክት ሊኖረው እስከጭራሹም የሚጠብቅ ድምፅ የለውም። እንደሌለው እያወቁ በዚህ የመሸፈን አቅም በሌለው ሽፋን ጀሌውን ሕዝብ አታለውታል ማለት ነው። የብዙ ሕዝብ ፊደሎች (ዓረቢኛንና ዕብራይስጥን ጨምሮ) ለቋንቋዎቻቸው ለሚጠብቅ ድምፅ ምልክት የላቸውም። ግን መፍትሔ ፈልገውለታል። የኦሮሞ ሊቃውንት የሀገራቸውን ፊደል ወስደው ለዚች ትንሽ ችግር እንኳን መፍትሔ መፈለግ አቅቷቸዋል።

ጉዳዩ የሚገደው ኦሮሞዎችን ብቻ ከሆነና ኦሮሞዎች ከተስማሙበት በጥላቻ ላይ የተመሠረት ምርጫ ሊያደርጉ ይችላሉ። ኦሮምኛ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን ከታሰብ ግን፥ ጉዳዩ ብሔራዊ እንጂ ኦሮሞዎች ብቻቸውን የሚወስኑበት የኦሮሞዎች ጉልማ ሊሆን አይችልም። ጥያቄውም ከሌሎቹ ቋንቋዎች ይልቅ በኦሮምኛ ላይ የሚነሣው በዚህ ምክንያት ነው። የእነሱ ፖለቲከኞች ቋንቋቸውን የአማርኛ ባላንጣ አላደረጉም።

አማሮች ኢትዮጵያን የመሰለች አገርና መንግሥት ለመፍጠር፥ ትምህርት ለመዘርጋትና ሕዝቧን በዓለም ደረጃ ለማስከበር ምክንያት ሆኑ እንጂ፥ በአገሪቱም ሆነች በመንግሥቱ በረይቱማና ቦረን የተጠቀሙትን ያህል አልተጠቀሙም። በረይቱማና ቦረን ነባሩን ሕዝብ ጨርሰው በሰባው መሬት ላይ ሰፍረዋል። ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልሆኑ አንዳንድ የአማራ ቤተ ሰብ በአጠገባቸው ቢያዩ፥ ለወያኔ ዕድሜ እየለመኑ ፈጇቸው። አማሮች “የኦሮሞ ደም ደማችን ነው” እያሉ ሲጮሁ፥ እነሱ “የኢትዮጵያን ባንዲራ አታሳዩን” እያሉ ይጮኻሉ። ምነው የኦሮሞ ፖለቲከኞች ነገር “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ሆነብን!!

10 COMMENTS

 1. “የኦሮሞ ሊቃውንት ባደረጉት ጥናት መሠረት ለኦሮምኛ የሚስማማውን ፊደል (ላቲንን) መርጠውለታል፤ ይህ ያለቀ፥ የደቀቀ ጉዳይ ነው፤ ኦሮሞ ያልሆኑትን የሚገዳቸው ጉዳይ አይደለም”!
  እና በግድ እንጫንባችሁ ነው?? የኦሮሞ ሊቃውንት ያቀረቡትን ምክንያት፣ በሳይንሳዊ እና ስነ ቋንቋ በሆነ አመንክዮ መሞገት እንጂ ፖለቲካዊ እና ምኞታዊ ትረካ መደርደር ከምንም አያደርስም! አሊያም ጦር ሰብቃችሁ ኦሮሞን ወደባርነት መልሱና ጥያቄውን ከነጭራሱ አዳፍኑ! ችግራችሁ የኦሮምፋ ስነጽሁፍ ወይም የሃገር አንድነት አይደለም! የሚያብከነክናችሁ በኦሮምፋ መጻፍ ለምን ተቻለ፣ እንዲጠፋ የለፋንበት ቋንቋ እንዴት አንሰራራ? አሁንስ እንዴት እናጥምደው?! የሚል የኦሮሞ ጠላቶች ጩሄት መሆኑ ላልተማረዉም ግልጽ ነው። እና አትልፉ!

 2. ፕሮፌሰር ጌታቸው የእውቀት ሚዛን መለኪያ እድሜ ይስጦት ብእሮ ይለምልም። ይህን የእውቀት ድርቅ ለመታውና ባረብና በሚስዮን ብስኩት አእምእሮው ለታወረው ምሁር ነኝ ባይ የእውቀት ጠበል እርጩበት። ለጥልያን፣ለዮሀን ክራፍት፣ለአረብ ቃል ስለገባ እነሱ የላኩትን ካላስፈጸመ እረፍት የለውም ። ኢትዮጵያን አምላኳ ይጠብቃታል እነሱ ግን ሰላም አጥተው እንደባነኑ ይኖራሉ።

 3. ” ኦሮምኛ በግእዝ ፊደል የመጻፉን ጥቅም- ከቋንቋ ምሁሩ ዶ/ር ጌታቸው ሃይሌ ”

  I have yet to read the article.

  That said,
  let us consider some facts:

  1. Oromos IMPOSED their language on Native Ethiopian tribes.

  2. Native Ethiopians are some 90% of the Ethiopian population and are also the majority in the so-called oramia region.

  3. Native Ethiopian tribes can anytime drop the oromigna language that they were forced to speak.

  4. Given those facts it is totally unacceptable that oromo extremists dared to force Native Ethiopian tribes to use the non-Ethiopian and non-African Latin Alphabet (i dont care whatever name they give it, “qube” or whatever) instead of Geez, which will soon become the Alphabet of Africa. By forcing Ethiopians to use the Latin Alphabet oromo extremists like Abiy and his ODP insulted Ethiopia, Africa and our ancestors and worshipped ferenjis. By imposing the Latin Alphabet oromo extremists showed that they are slaves of ferenjis, and they tried to spread ferenji culture in Ethiopia. Native Ethiopian tribes can punish oromo extremists for that sin.

  5. Well, an appropriate punishment for oromo extremists who forced Native Ethiopian tribes to use Latin Alphabet instead of our own Geez could be for Native Ethiopian tribes to no longer speak oromigna. That way, that language will become less important than Tigrigna and Somaligna, or even Guragigna.

 4. @ semere

  You are absolutely correct.

  Oromo extremists are desperate to spread ferenji culture.

  Warning oromo extremists, dare not spread ferenji culture in sacred Ethiopia !

  Dare not insult us with your Latin Alphabet !

  There is no place for Latin Alphabet and ferenji culture in Ethiopia, neither in Africa.
  Ferenji culture is being wiped out around the world, including in Africa. Dear oromo extremists, try to spread ferenji culture at your peril !

 5. 1/ ፕሮፌሰር ጌታቸው በቋንቋዎችና ጥንታዊ ታሪክ ሊቅ መሆናቸው ግልጽ ነው። ሆኖም በተለያዩ ጊዜአት የጻፏቸው አዋራጅ ፖለቲካዊ ጽሑፎች ተኣማኒነት እያሳጣቸው ነው። ለምሳሌ ይህን ይመልከቱ፣
  “አማሮች ኢትዮጵያን የመሰለች አገርና መንግሥት ለመፍጠር፥ ትምህርት ለመዘርጋትና ሕዝቧን በዓለም ደረጃ ለማስከበር ምክንያት ሆኑ እንጂ፥ በአገሪቱም ሆነች በመንግሥቱ በረይቱማና ቦረን የተጠቀሙትን ያህል አልተጠቀሙም። በረይቱማና ቦረን ነባሩን ሕዝብ ጨርሰው በሰባው መሬት ላይ ሰፍረዋል። ኦሮምኛ ተናጋሪ ያልሆኑ አንዳንድ የአማራ ቤተ ሰብ በአጠገባቸው ቢያዩ፥ ለወያኔ ዕድሜ እየለመኑ ፈጇቸው። አማሮች “የኦሮሞ ደም ደማችን ነው” እያሉ ሲጮሁ፥ እነሱ “የኢትዮጵያን ባንዲራ አታሳዩን” እያሉ ይጮኻሉ። ምነው የኦሮሞ ፖለቲከኞች ነገር “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ሆነብን!!”
  1ሀ፤ መንግሥት መፍጠር የአማራ ብቻ እንደ ሆነ ሲናገሩ አያፍሩም። ሌላው ተመልካች ነበረና ነው?
  1ለ፤ “ቦረን ነባሩን ሕዝብ ጨርሰው በሰባው መሬት ላይ ሰፍረዋል” ይሉናል። እዚህ ላይ የታሪክ መረጃ ሳይኖራቸው ነው የዘላበዱት! ኢትዮጵያ የአንድ ክፍል ነው፣ ሌላው መጤ ነው እያሉን ነው! ምድራችን በጦርነት ብዛት አንዱ አንዱን ሲገፋ ሲጨርስ ነው የኖርን፤ ባዕድ ሲመጣብን ደግሞ ተባብረን አባረርን፤ “የሰባውን መሬት” ማን ለማን ሰጠ? አንዱን አጽድቆ ሌላውን መኮነን ጥላቻ ማበራከት ነው!
  1ሐ፤ በጭፍን በጥላቻ መላው ኦሮሞ መሬት እንደ ሠረቀ፣ ሌላውን እንደ ጨፈጨፈ ያህል ያጋንናሉ። ወዲያው ደግሞ የተቀላቀለ ሕዝብ ነን ይሉናል!
  2/ የኦሮሞ “ሊቃውንት” ላቲን እንጂ ግዕዝ (ሳባዊ) ፊደል አንፈልግም ማለታቸው ለምን ይደንቃል? የፕሮፌሰር ጌታቸው ዓይነቶች ንቀት፣ ወራዳነት ሌላስ ቢያስደርግ ለምን ይደንቃል? የሆነውም ይኸው ነው። እልህና ጥላቻ፣ ጥላቻና እልህ እንጂ ምን ይወልዳል? የኦሮሞ “ሊቃውንት”ም በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ያደረሱት በደል ተጀምሮ አያልቅም። ነጻ እናወጣዋለን ብለው አስፈጅተው፣ ለራሳቸው በአውሮጳ፣ በሰሜን አሜሪካ ተንደላቅቀው ኖረው፣ ሃብት አፍርተው፣ ቤት ሠርተው፣ ልጆቻቸውን አስተምረው ድረው ዛሬ ተመልሰው ያደነቆሩት ሕዝብ መሓል እንደ ታገሉለት ያህል ያወናብዳሉ። ለእነርሱ አማርኛ የቅኝ ገዥ ቋንቋ ነው! አንድ ታሪክ ልጥቀስ፣ በ1989 ዓ.ም. ጆርጅ ኮተር የተባለ ግለሰብ 5ሺህ የሚያህሉ የኦሮሞ አባባሎችን አሰባስቦ በመጽሐፍ ለማሳተም ሥራ ጀመረ፤ ህትመቱን በአማርኛ ፊደል ወጥኖ ነበርና የኦሮሞ “ሊቃውንት” በላቲን ይሁን ማለት ሲጀምሩ፣ በቅድሚያ ሕዝቡ ምርጫው ምን እንደ ሆነ ጠየቀ፤ የሚገርመው የኦሮሞ ሕዝብ ፊደል ስለሚቀለን ከላቲን (ቊቤ) ይልቅ በአማርኛ ፊደል ይሁንልን አለ። እነ ዶ/ር ጥላሁን ገምታ ግን ለዓላማቸው ሲሉ የሕዝቡን ፈቃድ ንቀው የጆርጅ ኮተርን እቅድ አስቀየሩ። ይህን ጉዳይ መጽሐፉ መግቢያ ላይ ማንበብ ይቻላል። እነ ዶ/ር ጥላሁን ኦሮምያ የተባለች አዲስ ሪፑብሊክ ወዲያ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ እነርሱ ወይ ፕሬዚደንት ወይ ሌላ ሥልጣን የሚይዙ መስሏቸው ነበር። ኢሳይያስ አፈወርቂና መለስ “ኦሮምያ” የምትል ማታለያ ሽጠውላቸው ነበር፤ አግባብተው ኢሳይያስም ከቅኝ ገዥዋ ኢትዮጵያ አገሩን ነጻ ካወጣ በኋላ፣ እነ መለስም ሥፍራቸውን ከተቆናጠጡ በኋላ የኦሮምያ መሪዎችን ወጊዱ አሏቸው። ሲንከላወሱ ከርመው በምህረት ወደ አገር ተመለሱ። መለስም ሞተ፤ ህወሓትም ከመሓል ወጥቶ ጥጉን ያዘ። ይገርማል የታሪክ አካሄድ! ይገርማል የመሪዎች የሥልጣን ጥመኛነትና አርቆ አለማስተዋል የሚያስከትለው መከራ! በሌላ አነጋገር፣ የነፕሮፌሰር ጌታቸው ዓይነቶች ታሪክ ነው ብለው የሚጽፉት ጥላቻ፣ ጥላቻ ወልዶ አገራችንን እያመሰ ይገኛል።
  3/ ቅርብ ጊዜ ጎልጒል የተሰኘ ድረገጽ ላይ ስለ ቋንቋ የተጻፈውን ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘሁት ላካፍላችሁ፣

 6. ሰመረ ባጭሩ የሚለን፣ ከኦርቶዶክሳዊt እምነት ውጭ ያለ ሁሉ (ዐረብና ሚስዮኑ) በእርሱና በፕሮፎሰር ጌታቸው ኢትዮጵያ ሥፍራ የላቸውም ነው! አይገርምም? በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንዲህ ያለ ኋላ ቀር አስተሳሰብ አለመጥፋቱ!? “የእውቀት ድርቅ የመታው አእምሮ” ማለት ይልቅ ይህንን ነው!

 7. @ አለም

  EOTC is an Africanized Christian religion that could one day become the religion of Africa. Catholicism and Protestantism are ferenji religions, and the trend around the world is those ferenji religions are being dumped, even in Latin America. Ferenji religions are discredited for many reasons, like the many scandals of the Vatican, genocide of non-ferenji tribes in Latin America, Colonialism in Latin America, siding with ferenji right wing dictators in Latin America, etc.
  So, we can not put EOTC at the same level as the ferenji religions, neither in Ethiopia nor in Africa.

  Quote:

  ‘One more Christian, one less Chinese’: official vows to rid faith of Western influences

  MAR 12, 2019

  A senior Chinese official who oversees state-sanctioned Christian churches has pledged to rid the Protestant faith in China of any Western “imprint,” calling for further “sinicization” of religion.

  Xu Xiaohong, chairman of the National Committee of the Three-Self Patriotic Movement, a government-controlled body that runs state-approved Protestant churches, on Monday attacked what Beijing perceived as “Western influence.”

  “[We] must recognize that Chinese churches are surnamed ‘China,’ not ‘the West’,” Xu told delegates to the Chinese People’s Political Consultative Conference at the Great Hall of the People in Beijing.

  “The actions by anti-China forces that attempt to affect our social stability or even subvert the regime of our country are doomed to fail,” he said.

  We must recognize that Chinese churches are surnamed ‘China,’ not ‘the West’

  For the officially atheist Communist Party, the sinicization campaign is an attempt to place religion under its absolute control and bring it into line with Chinese culture.

  According to a five-year plan to sinicize Protestant churches released by the Chinese religious authorities, efforts to make the faith more “Chinese” included a new translation and annotation of the Bible.

  It also demanded Chinese traditional culture be integrated into liturgy, sacred music, clerical clothing and church buildings. Examples given included using traditional Chinese tunes to compose hymns and encouraging Christians to practice calligraphy and Chinese painting.

  In China, Protestantism and Catholicism are two of the five officially recognized religions. “Christianity” and “Protestantism” are translated as the same term in Chinese and often conflated, while “Catholicism” has a separate translation.

  “In modern times, Christianity was spread widely to China along with the colonial invasion of Western powers, and was therefore called a ‘foreign religion’,” Xu said on Monday, striking a nationalist tone to underline the need for sinicization.

  “Some believers lack national consciousness, and that’s why we have the saying: ‘one more Christian, one less Chinese’.”

 8. @Lema; It is too transparent that you are an ignorant Habesha zealot, but too unashamed to poke your nose everywhere! Only ignorants think that they know better than all others – The curse of ignorance!

 9. Whats up Abba Caala, are you also አለም ?

  You retard can not debate with arguments, you always have to throw insults. That is the behaviour of a loser. Learn a bit more and then you will be able to debate with people without throwing insults. 😉

 10. አለም ነህ ማነህ? በፕሮፌሰር ጌታቸው እንዲገባህ ታስቦ ቀለል ተደርጎ የቀረበው እውቀት ወደ አእምእሮህ ካልዘለቀ ነብስህን አታስጨንቃት ቃሊቻ እየካደምክ ኑር።

  እሳቸውም ደከሙ እኛም ግራ ገባን አንድ ማስተማሪያ ጵሁፍ ሲለቀቅ በያላችሁበት ልቅሶ ነው ከናንተ አካባቢ ደግሞ እንዲህ ያለ ነገር አይሞከርም ባለፈው ድርሳናት ሲፈተሹ ሊቀ ሊቃውንት ህዝቅኤል ጋቢሳ ስለ ጫት ምርቃናና ጠቀሜታው ተገኝ። ሌላ ምንም የለም እናንተ እዚህ የምትሳዱቡትም ምሁራን ሳትሆኑ አትቀሩም ምን ዶሲ አገላበጣችሁ አቋራጩ ስድብ እያለ በርትታችሁ ተሳደቡ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.