የጉራጌ ሕዝብ ከ158 ዓመታት በፊት. . .- አቻሜለህ ታምሩ

የጉራጌ ሕዝብ ከ158 ዓመታት በፊት. . .

ሰማዩም ምድሩም የኛ ነው የሚሉን ኦነጋውያን የሚይዙት ቅጣምባሩ ጠፍቷቸዋል። ከሰሞኑ ደግሞ ባሰራጩት በምስል የታገዘ ዜና በጉራጌ ምድር ከ158 ዓመታት በፊት ተቋርጦ ነበር ያሉን የገዳ ስርዓት ማስጀመራቸውን ነግረውናል። እንዲህ አይነት ዜና ሲሰማ ዝም ማለት ተገቢ ባለመሆኑ ከ158 ዓመታት በፊት የጉራጌ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ጋር ስለነበረው ግንኙነት፣ የነበረውን የውስጥ አስተዳደር ታሪክና ገዳ የሚባለው የወረራና የዘመቻ ስርዓት ወደ በአካባቢው በደረሰበት ወቅት ስለተከተሉ ሁኔታ ሳነብ ከተማርሁት የሚከተለውን ጀባ ብያለሁ።

የጉራጌ ምድር ከጥንት ጀመሮ የኢትዮጵያን መንግሥት ያቆሙ ዋናዋና የጦር መሪዎችን ያፈራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አውራጃ ነበር። ተመዝግቦ ከምናገኘው ታሪክ ብንነሳ እስከ ሞቃድሾ ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ግዛት ባስተዳድሩት ዐፄ ዐምደ ጽዮን [እ.ኤ.አ. ከ1314 ዓ.ም. – 1344 ዓ.ም. ድረስ የነገሡ] ዜና መዋዕል ውስጥ ጉራጌ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ጋር ቅርብ ቁርኝት የነበረው ሕዝብ እንደነበር ተጽፎ እናገኛለን። በዘመኑ የጉራጌ አውራጃ የውስጥ አስተዳደር ይመራ የነበረው በጉራጌ ተወላጅ አበጋዞች ነበር።

ጉራጌ አውራጃውን ከራሱ በተወለዱ አበጋዞች ያስተዳድር የነበረው ኦሮሞ በገዳ መተዳደር ከመጀመሩ ቢያስ ከ208 ዓመታት በፊትና ኦሮሞ ደቡብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና መካከለኛው ኢትዮጵያን መውረር ከመጀመሩ ከ200 በላይ ዓመታት በፊት ነበር። የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን “The Oromo and the Christian Kingdom of Ethiopia” በሚል ማሳተመው መጽሐፉ ገጽ 158 ላይ እንደጻፈው ኦሮሞ በገዳ መመራት የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1522 ዓ.ም. እንደሆነና የመጀመሪያው ገዳ “ገዳ መልባ” እንደሚባል ነግሮናል። ጉራጌ ግን ኦሮሞ ገዳ ከጀመረበት ከ1522 ዓ.ም. በመቶዎቹ በሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ቆዬት ብዬ የማቀርብላችሁ ከገዳ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላው የራሱ የውስጥ አስተዳደር ሥርዓት ነበረው።

የጉራጌ ምድር ክርስትና ቀድሞ በሰፊው ከተሰበከበትና ከጸናበት የኢትዮጵያ አውራጃዎች አንዱ ነበር። በወቅቱ የተጻፈው ድርሳነ ዑዔል ይህንን ያረጋግጣል። ከድርሳለ ዑራኤሉ በተጨማሪ ራሳቸው የጉራጌ ተወላጆችም ይህንን ታሪክ ጽፈዋል። የጨቦ ኡዳደ እየሱስ ሕዝብ ታሪክ ጸሐፊው አቶ ምስጋናው በላቸው “የጨቦ ኡዳደየሱስ ሕዝብ አጭር ታሪክና ባሕል” በሚል በመጋቢት 1985 ዓ.ም. ከጀርመን በጻፉት የታሪክ መጽሐፋቸው ገጽ 66 ላይ እንደጻፉት አይመለል በሚባለው የጉራጌ ምድር የሚኖረው «ክስታኔ» የሚባለው ሕዝብ መጠሪያ «ክስተነ» ከሚል ከቦታው ቋንቋ የመጣ መሆኑንና ትርጉሙም ክርስቲያን ማለት እንደሆነ ነግረውናል። አይመለል የመጀመሪያዎቹ ክስታኔዎች ወይንም ክርስቲያኖች የሰፈሩበት ምድር ነው።

ክስታኔ፣ ጉራጌ በመባል በወል ከሚጠሩት የቤተ ጉራጌ ማኅበረሰቦች ውስጥ አንዱ ሲሆን ሶዶ ጉራጌ እየተባለም ይጠራል። የክስታኔ ሕዝብ ቋንቋ ክስታኒኛ ይባላል። አቶ ምስጋናው በላቸው በመጽሐፋቸው ገጽ 63 እንደነገሩን በጨቦ ምድር ብቻ ከግራኝ ወረራ በፊት 40 ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት የነበሩ ሲሆን ከወረራው በኋላ የተረፉት ግን 13 ስደተኛ ታቦቶች የተዳበሉበት ታሪካዊው የዋሻ ሥላሴ ቤተክርስቲያንና በወንጭት ደሴት ላይ የነበረው የቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ብቻ መሆናቸውን ነግረውናል። አቶ ምስናጋው ጨምረው እንደጻፉት የዋሻ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት የተሰራ መሆኑን ከጉራጌ ታሪክ አዋቂ አባቶች አገኘሁት ያሉትን ታሪክ ነግረውናል። ይህ የጉራጌ ሕዝብ ክርስትናን ከተቀበሉ ቀደምት የኢትዮጵያ ነገዶች መካከል መሆኑን ያሳየናል።

ጉራጌ የኢትዮጵያን ሰለሞናዊ መንግሥት በሸዋ ምድር ካቆሙ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ነገዶች መካከል ቀዳሚው ስለመሆኑ ሌላው ማስረጃ በዐፄ ናዖድ ዘመነ መንግሥት የተጻፈው ድርሳነ ዑራዔል ነው። በዘመኑ ድርሳነ ዑርዔል እንደተጻፈው እግዚአብሔር መስፍንነት ከጉራጌ፥ ከመንዝና ከወረብ እንዳይወጣ ለአጼ ናዖድ [የንግሥና ዘመናቸው እ.ኤ.አ. ከ1494-1508 ዓ.ም. ድረስ ነው] ቃልኪዳን ገባለት ይለናል። ይህ በድርሳነ ዑራዔሉ ከገጽ 311-315 ተጽፎ የሚገኝ ሲሆን ሙሉው ቃል እንዲህ ይነበባል፤

“ወእምድኅረ ፡ ዝንቱ፡ወሀቦ ፡ ለናዖድ ፡ እግዚእነ ፡ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ኪዳነ ምሕረት ፡ ከመ ፡ ኢይጥፋእ ምስፍና ፡ ወምልክና ፡ በምድረሸዋ ፡ ወመንዝህ ወበሀገረ ፡ ጐራጌ ፡ ዘይብልዎ ምድረ ፡ ወረብ ፡ ወምሁር።”

ትርጉም፡

“ከዚሀ ፡ በኋላ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ከምድረ ፡ ሸዋ ፡ምሁርና ፡ምድረ ፡ ወረብ ፡ ከሚባለው ከጐራጌ ፡ አገር ፡ ከመንዝም ፡አገዛዝና ፡ መስፍንነት ፡ አንዳይጠፋ ፡ ለናዖድ ፡ ቃል ፡ኪዳን ፡ ሰጠው።”

በድርሳኔ ዑራዔሉ እንደተገለጠው የጉራጌ ሕዝብ በዘመኑ የኢትዮጵያ መስፍን ሆነው እንዲሾምላቸው ከተወሰነላቸው ሶስት የኢትዮጵያ አካባቢዎች መካከል አንዱ ነበር። በዚህ መልክ እስከ መካከለኛው ዘመን የማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ዋልታ የነበረው ጉራጌ ከግራኝ ወረራ በኋላም ለኢትዮጵያ ቤተመንግሥት በጣም ቅርብ ነበር። ከግራኝ ወረራ በኋላ ዋናኞቹ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ራሶች ጉራጌዎች ነበሩ።

ከግራኝ ወረራ በኋላ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የመንግሥት ስልጣን ከነበራቸው አራጊ ፈጣሪ ጉራጌዎች መካከል በዐፄ ያዕቆብ [ እ.ኤ.አ. ከ1597 ዓ.ም. – 1603 ዓ.ም.፤ እንዲሁም ከ1604 ዓ.ም. -1607 ዓ.ም. ድረስ የነገሡ] እና በዐፄ ዘድንግል [ እ.ኤ.አ. ከ1603 ዓ.ም. – 1604 ዓ.ም. ድረስ የነገሡ) ዘመናት የነበሩትን ራስ ዘሥላሴን ለአብነት መጥቅስ ይቻላል። የጉራጌ ተወላጁ ራስ ዘሥላሴ ዐፄ ዘድንግል “መልከ ሐራ” በሚል ያቋቋሙትን የንጉሥ ሠራዊት ይመሩ ነበር። ዐፄ ሰርጸ ድንግል እ.ኤ.አ. በ1597 ዓ.ም. ከሞቱ በኋላ ደግሞ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያን የገዙት ራስ ዘሥላሴ ነበሩ ማለት ይቻላል።

ራስ ዘሥላሴ በዐፄ ሰርጸ ድንግል ዘመን «ቁርባንና ሚዛን» የተባለው ደምብያ የሰፈረው ሰራዊት መሪ ነበር። ዐፄ ዘድንግል ለወታደሩ አመጽ ምክንያት የሆነ ገባሩን ነጻ የሚያወጣ አዋጅ አውጀው ነበር። ይህ አዋጅ ወታደሩንና ገባሩን ወይም ዜጋውን እኩል ያደረገ አዋጅ ነበር። በዚህ ምክንያት ራስ ዘስላሴና ቁርባንና ሚዛን የተባለው ሰራዊት በንግሡ ላይ አምጾ ደምብያ ውስጥ ባርጫ ከተባለ ስፍራ ዐፄ ዘድንግልን ገደሉት። ጣሊያናዊው የታሪክ ተመራማሪ ኮንቲ ሮሲኒ ያሳተመው በዘመኑ የተጻፈው ታሪከ ነገሥት መንግሥት በጉራጌው በራስ ዘስላሴ እጅ ገብቶ ነበር ይላል። ኮንቲ ሮሲኒ ያሳተመው ታሪከ ነገሥት ውስጥ የሚገኘው ይህ ታሪክ የሚከተለውን ይመስላል፤

“ወበውዕቱ ፩ዓመት ተጻልዕዎ ሐራሁ ለሐጼ ዘድንግል እለ ይብልወሙ ቁርባን፥ወሚዛም ወእርስ ዘስላሴ በምክንያተ ዝንቱ አዋጅ ዘአንገረ ውእቱ እንዘ ይብል ሰብእ ሐራ ፤ ወገብራ ምድር። እስመ ዓመፁ ኩሉ ዜጋሆሙ ወቀተልዎ በኵናት ማዕከለ ደምብያ ዘውእቱ ባርጫ [1604 ዓመተ ምህረት] ። […] ወእምድኅረ አዘዘ እራስ ዘሥላሴ ከመ ያንስእዎ ለሐጼ ዘድንግል ወአንሥእዎ ወወሰድዎ ውስተ ደሴተ ዳጋ ወቀበርዎ ህየ። ወነበረት መንግሥት በዕዴሁ ለጉራጌ ራስ ዘሥላሴ።” [ ምንጭ፡ Conti Rossini, C. (1893). Due squarci inediti di cronica etiopica. Rendiconti della reale accademia dei Lincei. C/asse di scienze morali. storiche e. filologiclre; Page 807.

ትርጉም፡

በአንድ ዓመት ውስጥ ቁርባንና ሚዛን የተባሉት ወታደሮች እንዲሁም ራስ ዘሥላሴ “ሰው ነጻ ነው፤ምድር ገባር ነው” በሚለው አዋጅ ምክንያት ዐፄ ዘድንግልን ተጣሉት። ዜጎች [ንጉሡን ደግፈው አመጹ]። በደምብያ መካከል ባርጫ ውስጥ በጦር ወግተው ገደሉት። ከዚህ በኋላ ራስ ዘሥላሴ ዐፄ ዘድንግልን እንዲያነሱት አዘዘ፤አንስተው በዳጋ ደሴት ቀበሩት። መንግሥት በጉራጌው በራስ ዘሥላሴ እጅ ነበረች።
ከዚህ የምንረዳው በዘመኑ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት አራጊ ፈጣሪ የነበሩት የጉራጌ ተወላጁ ራስ ነበሩ።

ወደ ውስጥ አስተዳደሩ ስንመጣ የጉራጌ ሕዝብ አውራጃውን የሚያስተዳድረው ከተወላጆቹ በሚመረጡ አበጋዞች ነበር። የጨቦ ተወላጁ አቶ ምስጋናው በላቸው የጉራጌ ሕዝብ አካል የሆነውን የጨቦ ሕዝብ የውስጥ አስተዳደር በሚመለከት “የጨቦ ኡዳደየሱስ ሕዝብ አጭር ታሪክና ባሕል” በሚለው መጽሐፋቸው ከገጽ 85-89 የሚከተለውን ጽፈዋል፤

“አበጋዙ የሕዝቡ ጠቅላይ አስተዳዳሪ ሆኖ እንደ አባት የሚታይ መሪ ነው። አበጋዙ እንደኃላፊነቱ ሥፋትና የሥራው ክብደት ከእጩነት አስንቶ እስከተሾመበት ድረስ በጥልቅ ተጠንቶ የሚመረጥበት ሁኔታ ጥንቃቄ የተሞላበት ነው። ይህም የሚሆነው በየሁለት ዓመት ግፋ ቢል በሶስት ዓመት አንድ ጊዜ ነው። የአንድ አበጋዝ የአገልግሎት ዘመኑ ለሁለት ዓመት ብቻ ሲሆን በዚሁ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዳኝነቱና ተወዳጅነቱ ከፍ ያለ ምስክርነት ካገኘ ያለ ምንም ተቃውሞ አንድ ዓመት ተመርቆለት ለሶስት ዓመታት ያስተዳድራል። ድጋሚ መመረጥ የለም። . . .

አበጋዝ ሲመረጥ በጊዜው ሥልጣን ላይ ያለው የአመራር አካል ሥልጣን ከመልቀቁ ከብዙ ወራት በፊት አበጋዝ መመረጥ የሚገባው ሰው ስም ከየጎሣው በሚስጥር ይጠየቃል። አበጋዝ መሆን ይችላል ተብሎ ከየጎሳው ከየአካባቢው የተጠቆመውን አዛውንት የእያንዳንዱን ሁኔታ ማለት ባሕሪው፣ ተቀባይነቱና የማስተዳደር ችሎታውን በሚስጥር አጥንቶ አበጋዝ ይሆናል ብሎ ያመነበትን ለጠቅላላው የሕዝብ ጉባኤ ያቀርባል።

ሕዝቡ ካመነበት በኋላ የሹመቱ ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበትን ቀን ራቅ አድርጎ ይቀጥራል። ቀጠሮው ራቅ የሚለው በሕዝቡ ጥያቄ ሆኖ እንደተለመደው በሥርዓተ ሹመቱ ቀናት ሕዝቡ በፈቃዱ የሚደሰትበትን የእርድ በሬዎች፣ የሚበላና የሚጠጣውን ከየጎሳውና ከየአካባቢው አጠራቅሞ ለማምጣት እንዲመቸው ብሎ ነው። የተሿሚው ጎሳ አብዛኛውን ያቀርባል።

በስርዓተ ንግሡ ቀን አበጋዙ በሻሽ ጥምጥም ዘውድ ሰሠርቶላቸው፣ የአበጋዙ ባለቤት በፀጉራቸው ጉንጉን ዘውድ ተሠርቶላቸው አበጋዙ በሠንጋ ፈረስ፣ ባለቤታቸው “እቴ” ተብለው [እቴጌ ማለት ይመስላል] በሰጋር በቅሎ ላይ ተቀምጠው በጎሳቸው እጀብና ሆታ ሰንበት ወራቡ ሲደርሱ እዚያ ተሰብስቦ የሚጠብቃቸው ሕዝብ በዘፈንና በእልልታ ይጠብቃቸዋል። ሰንበት ወራቡ የመጀመሪያ ሥርዓተ ንግሥ የሚፈጸምበት ቦታ ነው። እዚያ ቦታ ከመድረሳቸው ቀደም ብሎ አበጋዙና “እቴ” የሚቀመጡበት በሦስት ድርብ የተሰራ የእንጀራ መደብ ይዘጋጃል። እንጀራ ላይ የሚቀመጡበት ምክንያት እነሱ በሚያስተዳድሩበት ክልል ጥጋብ እንዲሆን ተመኝተው ነው ተብሎ ይታመናል።

ተሿሚዎቹ የክብር ሥፍራቸውን ከያዙ በኋላ በገንዙና በአባጅልባዎች አማካኝነት ሕዝብ በተሰበሰበበት ሥርዓተ ንግሡ ይፈጸማል። ወዲያውኑ ቃለ መሐላ ሲፈጸም ወይፈኖች፣ በሬዎች ታርደው ፈንጠዝያው ይቀጥላል። ይህ የደራ ድግስ በየደረጃው እየተበላ አምስት ቀን ይቆያል። በአምስተኛው ቀን አበጋዙና “እቴዋ” ዋሻ ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደዚያ ታጅበው ሄደው የመጨረሻ ሥርዓተ ንግሥ ከተፈጸመ በኋላ አበጋዙ ወደ ጅሎት ቦታው ተመልሶ አገልግሎቱን ከፈጸመው አበጋዝ መንበሩን ይረከባል። አንዴ አበጋዝ ሆኖ የተመረጠ አዛውንት መንበሩንና አስተዳደሩን በፍቅርና ራሱ ቃለ ቡራኬ ሰጥቶ ለአዲሱ አበጋዝ ሲያስረክብ በትረ መንግሥቱ [በእጁ ይይዘው የነበረው ዘንድ] ለክብሩ ሲባል በእጁ ይቀራል። የአገልግሎቱ ዋጋም ዕድሜውን ሙሉ አበጋዝ ተብሎ መጠራት ሆኖ ይኸው የማዕረግ ስሙና የሚይዘው አንድ ነበሩ።”

የጉራጌ ሕዝብ የውስጥ አስተዳደር በዚህ መልክ የተገለጸውን ይመውላል። አበጋዞቹ በሕዝብ ፊት ሥርዓተ ንግሥና ከፈጸሙ በኋላ የሥርዓት ንግሥናው ፍጻሜ የሚሆነው አበጋዙና እቴዋ በጥንታዊው ዋሻ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሄደው የመጨረሻውን ሥርዓተ ንግሥት ከፈጸሙ በኋላ ነው። በዚህ መልክ አውራጃውን ሲያስተዳድር የኖረው የጉራጌ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ጋር የነበረው ግንኙነት የተቋረጠው በኦሮሞ ወረራ ምክንያት ነው። በኦሮሞ ወረራ ምክንያት ከማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የነበረው ግንኙነት የተቋረጠው የጉራጌ ሕዝብ በተለይም የጨቦ ክስታኔና ምሑር ሕዝብ በኦሮሞ ወረራ ምክንያት ክሥታኔና ምሑር የነበረውን ቋንቋውን በአባገዳዎች ተገዶ እንዲተውና ኦሮምኛ እንዲናገር በመገደዱ ብዙ ስቃይ እንደደረሰበት አቶ ምስጋናው በመጽሐፋቸው አትተዋል። አቶ ምስጋናው በመጽሐፋቸው ገጽ 50 ላይ እንደጻፉት ኦሮሞ በገዳ ስርዓት እየተመራ የጉራጌን ምድር ሲወር የነበረውን ጥፋት እንዲህ ይገጹታል፤

“በዚህ ጊዜ [ኦሮሞ ወደ ግራጌ ምድር በተስፋፋበት ወቅት ማለታቸው ነው] ስለ ቋንቋ የነበረው እምነት ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ” የሚል ሆነ። ትርጉሙም ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ” ማለት ነው።”

እንግዲህ! ኦነጋውያን በጉራጌ ምድር ከ158 ዓመታት በፊት ነበረ ያሉትን ገዳ ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ያሉት ገዳ የሚባለው የወረራ ስርዓት ሳይመሰረት የራሱ የውስጥ አስተዳደር የነበረውን የጉራጌ ሕዝብ “ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ” እያሉ አባገዳዎች የጉራጌን ሕዝብ ያጠፉበትን፣ ከርስቱ ያፈለሱበትን የወረራና የጦርነት ስርዓት መልሰው ለመትከል ነው። አባገዳዎች ወደ ጉራጌ ምድር ብቻ ሳይሆን ወደ ምዕራብ፣ መካከለኛውና ደቡብ ኢትዮጵያ የተስፋፉት “ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ” እያሉ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት እየፈጸሙ ነው። ኦነጋውያን በጉራጌ ምድር መልሰው ሊተክሉ እየፈለጉት ያለው የገዳ ስርዓትም “ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ” እያሉ አባገዳዎች ዘር ያጠፉበትን፣ ባላመሬቱን ከርስቱ ያለፈሉበትን የወረራና የዘር ማጥፋት ስርዓት ነው።

የጨቦ ተወላጁ አቶ ምስጋናው በላቸው በመጽሐፋቸው ገጽ 66 እንደነገሩን አባገዳ አካባቢውን ከወረረው ጀምሮ የነበረው ስቃይ፣ ጭቆና መከራ ተወግዶ በጨቦ ምድር ፍቅርና ሰላም የወረደው ዳግማዊ ምኒልክ ሲደርሱላቸውና ከአባገዳ ባርነት ሲያላቅቋቸው እንደሆነ ጽፈዋል። «የሰላሙ ዘመን» ያሉት የዐፄ ምኒልክ ፀሐይ በጨቦ ምድር መውጣት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የጨቦ ካሕናት ከዐፄ ምኒልክና ራሶቻቸው ጋር እየዞሩ በኦሮሞ ወረራ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የጥንቱን ወንጌል የማስፋፋት ተግባራቸውን በመቀጠል እስከ ዳር አገር ድረስ እየዞሩ ክርስትና መነሳት የሚፈልገውን ክፍል እንዳጠመቁና ከመሐል ኢትዮጵያ እስከ ኖኖና ጡቁር ምድር ድረስ በመሄድ አዳዲስ አማኞችን ያጠምቁት የጨቦ ቄሳውስት እንደነበሩ አውስተዋል።

ባጭሩ የጉራጌ ሕዝብ ለሺ ዘመናት የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ዋልታ የነበረ፣ የራሱ የሕዝብ አስተዳደር ስርዓት የነበረው ሰራተኛ ሕዝብ እንጂ ገዳ የሚባል ከዲሞክራሲ ጋር የስናፍጭ ቅንጣት ታህል ግንኙነት የሌለው የወረራ፣ የጦርነት፣ የመስፋፋት ዘመቻና የዘር ማጥፋት የተካሄደበት ስርዓት ባለቤት አልነበረም!

12 COMMENTS

 1. Native Ethiopians, who are the overwhelming majority in Ethiopia, including in so-called oramia, should give oromo extremists, that should include Abiy and his ODP, the choice:

  1. to accept the non-tribalist “All Ethiopia for all Ethiopians” formula where there will be no tribal homelands and to be no threat to the continued existence of ancient Ethiopia or

  2. to go back to where they came from. We now have more than enough historical evidence that prove from where the oromos came. We all are aware that millions of oromigna speaking people in so-called oramia are native Ethiopians who were forced to speak oromigna, ancient Ethiopians like Damot, Enaria, Kembata, Welayita, Sidama, Hadiya, Gurage, Gamo, …

  Let us the extremist oromos make the choice.
  Native Ethiopians make up some 90% of the Ethiopian population. So, this may be the time to ask extremist oromos either to behave or go back to where they came from. Imagine, European Americans are longer in the USA than oromos are in Ethiopia, still Native Americans are now telling European Americans to go back to Europe.

  That said,

  be warned !

  We have an evil person in power in Ethiopia called Abiy Ahmed,

  * who lied to Ethiopians when he preached Ethiopiawinet,

  * who mocked Ethiopians a number of times (remember, a year ago he called Ethiopians to go to the streets to welcome Isayas. When he said that he made Ethiopians think that something big was achieved in talks with Eritrea. Now we know, there were no gains for Ethiopia, only for Eritrea),

  * who sends OLF’s attack dogs to kill and rob Ethiopians,

  * who displaces millions from their lands and demolishes their homes, …

  This Abiy Ahmed is an evil person and should be removed from power ASAP before he inflicts more damage on the country.

 2. Achameleh , All you think and breath is about Oromo people. That is a classic Oromo phobia. If you spend even a little time and energy to bridge the gap between the people that you said you advocate for, The Amharas and the Oromo’s, we would be in a better place. This kind historical bickering is not helping us at all. Be positive my brother, Be progressive, and use your talent to bring us all for a common good……. Not Abebe Bikila’s identity or getting Credit to whatever happened 158 years ago is helping us to stay remain as one country. let the lessons of Rwanda be your guide….

 3. ለኦሮሞ ያለህ ጥላቻ እስከምን ድረስ ነው?? ከጥንት የጀመረ የመሳሪያ ጦርነት ሳያበቃ፣ ኦሮሞ ሰላም እናዉርድ በሚልበት ባሁኑ ሰአት የፕርፓጋንዳ ጦርነታችሁ ወሰን አጣ! ምን እንዲመጣ ነው ይህ ሁሉ?? የመደዴ የፈጠራ ታሪክ ማዥጎድጎድህ ኦሮሞ ተመልሶ ገባር እንዲሆንላችሁ ነው ??

  ያልተወራረደ ሂሳብ ካለ ከ16ኛ ክ ዘመን ሳይሆን ዛሬ እየሆን ካለው እንጀምርና ወደሁላ መሄድ ካስፈለገ እስከ 3000 አመታትም ማወራረድ እንችላለን። ስለዚህ መጀመሪያ፣ የኢህአድግ መንግስት በኢትዮጵያ ስም ለጨፈጨፋቸው መቶ ሺህዎች፣ አካል ስንኩል ለተደረጉና ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ሚሊዮን ኦሮሞዎች ካሳ ሳይሆን ጉማ ከፍሎ ሲያበቃ፣ እንደዚሁ ከሚኒሊክ እስከ ደርግ የነበሩ የሃበሻ መንግስታት ላካሄዱት ጭፍጨፋ፣ ለባርነት መሸጥ፣ ጭቁን ህዝቦችን በገዛ ምድራቸው ከባርነት በታች ገባር በማድረግ ለደረሰው አካላዊ፣ ስነልቦናዊ እና እኮኖሚያዊ ድቀት ሃበሾች ለተወላጆቹ ካሳ ሲትከፍሉ፣ አጼ ቴዎድሮስ እና አጼ ዮሃንስ በወሎ ኦሮሞዎች ላይ ላካሄዱት ጀኖሳይድ፣ ንጉስ ሃይለ መለኮት እና ሌሎች የሸዋ ነገስታት በቱላማ ኦሮሞዎች ላይ ያደርጉት ለነበረው የተደራጀ ወረራ እና ጭፍጨፋ … እያለ ይቀጥላል! ለነዚህ ሁሉ እስከዛሬ ላልቆሙ የዘር ፍጅቶች ጉማ ስትከፍሉ፣ ከዚያ በፊት ለነበረው ደግሞ እንመካከራለን! እስከዛሬ ላልቆመው ግፍ እንኳን ይቅርታ ልትጠይቁ፣ እንኳን ካሳ ልትከፍሉ፣ ግፍ መፈጸሙን እንኳ እየካዳችሁ፣ በ16ኛው ክ ዘመን እና ከዚያ በፊት ተፈጽሞ ይሆን ይሆናል ለሚትሉት ድርጊት የጭካኔ ተረት እየደረታችሁ ትተርካላችሁ! ይህ ምሁርነት ሳይሆን የገዳዮች ሽሙጥ እና ዉንብድና ነው!

  ለፕሮፓጋንዳህ እንዲያመችህ ታሪኩን በቁንጽል አቀረብከው። ሙሉው እውነት ግን ጉራጌ በአክሱም ዘመን የኩሽ ህዝቦችን ለማስገበር ከሰሜን በወታደርነት ተልከው እዚያው የቀሩ የቅኝ ግዛት አስፋፊዎች ቅሪቶች ናቸው። ግን ጉራጌ “የራሱ የሕዝብ አስተዳደር ስርዓት የነበረው ሕዝብ” መሆኑን የካደ ያለ አይመስለኝም። ለጽሁፍህ መነሻ የሆነው ዜና ግን ስለጉራጌ ህዝብ ሳይሆን፣ ጉራጌ ተብሎ በተከለለው ዞን ዉስጥ ስለሚኖሩ ኦሮሞዎች ነበር! እናም የኦሮሞ ጥላቻ ማገናዘቡን ስለነሳህ ኦሮሞ ላይ የተለመደ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻህን ቀጠልክ! ምንም እንኳ የፍጹማዊ ዲሞክራሲ ተምሳለትነቱ ምሁራን የመሰከሩለት እና UNESCO ከሰው ልጆች የፈጠራ ቅርሶች አንዱ አድርጎ የመዘገበውን የገዳ ስርዐት “የወረራ፣ የጦርነት፣ የመስፋፋት ዘመቻና የዘር ማጥፋት ስርዓት” ማለትህ የራስህን ድንቁርና እና በጥላቻ የጨቀየ ስነ ልቦናህ ብቻ ነው የሚገልጠው! @sinbirroon baaritti fincoofte jedhnan, ‘balagummaa ishee’! jedhe Oromoona@

 4. Thanks for sharing this commentary.
  I was expecting some one to say something on this is that was on the news days back but unfortunately no much comment has been made. When I saw this on etv news and on media, I was very angry. I was born and grown up in Gurage region in gurage Family, Sebat bet up until I joined high school in Addis and went to college in Oromia region. I am proud Ethiopian and believe in equality of all human being and respect others.
  In my memory no gurage cultural tie of this extent exists with Oromo. Actually gurage’s perhaps have better tie (not with respect to origin though) with other southern people such as wolayta, kembata and hadiya like in cultures like as meskal and enset etc. The gurage have no root similarity or linguistic similarity with oromo people. As a child I heard parents talking of times of oromo invasion, killing, cutting private parts and rampaging parts of gurage up until Minilik unified the country. Perhaps due to this the oromos might have imposed influenced on the gurage neighbors such as in Sodo Gordona, nothing more elsewhere. It is shameful to make news news in national media (government owned, stupid if they think this is good idea)by stating Geda has been re-instated in Gurage region after 158 years by while there was no such a system or culture in Gurage at all. Gurage have their own well advanced culture like KITCHA, GURDA, YEJOKA, EDIR, EKUB etc. There are peaceful people locally and elsewhere. They have rules to implement peace. They don’t claim others property as theirs but work hard like any other Ethiopian to own by hard work. Personally I respect all other Ethiopian culture that of Oromo’s included. However I don’t as christian like erecha-going to river with ketema, even Gada with Head sign that looks like phallus, Kegna system and gudifecha of owning others. Respect to any one who wants to practice them but not on me at all. As current Ethiopian, Dr Abiy as fair prime minster of the transition, I still expect Oromo’s and Oromo fanatics to respect others feeling, culture and value and keep their “stupid” (for those of us who don’t care about it) culture to themselves and stop this expansionist idea/culture here and fight there to own others. Ethiopian people need peace, job, existence, respect, unity; not show off one tribe/ethnic on other. Please spread ethiopianism, spirit of unity. Please keep your ethnic junk to your own tribe and bring advancement in technology, health service, good roads, nationalism, move away from tribalism.

 5. ሳተናው እኛ አቻምየለህ ታሪክ አስደግፎ ማስረጃ አያይዞ ጊዜውን ለወገኖቹ በመስጠቱ ምስጋና ስንደርስ አታወጡልንም እነ Abaa Caala እየተከታተሉ የአንድነት ሀይሉን ሲያጠቁ በእቅድ እየተንቀሳቀሱ ኢትዮጵያዊነትን ሲያጠቁ ስድባቸው ለህዝብ ይቀርባል ይህ ነገር መልካም ስላልሆነ አስቡበት።

 6. @ Tulu Moti

  It seems the only words you know are ” Oromo phobia”.
  The Bantus from Kenya and the Somalis from Somalia drove you out of your homeland. Ha ha, you tried to keep that secret for yourselves, but now the whole Native Ethiopian tribes know your secret. 🙂
  Bantus and Somalis drove you out of your desert homeland, Ethiopia gave you shelter where you live since the 16th century. Be grateful to Ethiopia for allowing you to stay there.
  But if you don’t like the country, you can still go back to where you came from.
  You have committed horrible crimes against Native Ethiopian tribes and imposed your language on them, so don’t be surprised if they hate you. It is because of your horrible crimes. The Harrar wall was built to protect Native Ethiopian tribes from violent oromo robbers. So, if you can’t be grateful to Ethiopia, you can still go back to where you came from.
  Native Ethiopians may soon lose their patience with you and may start defending themselves and also may dump the language you imposed on them. Shouting “Oromo phobia” nonstop may no longer help you.

  @ Abba Caala

  you must be also Tulu Moti who nonstop repeats the words “Oromo phobia” (ለኦሮሞ ጥላቻ). As i already said, go back to where you came from if you don’t like the situation in Ethiopia. You are an extremist oromo whose brain is full of lies and shit. You are a toxic person. Go back to where you came from, Ethiopia doesn’t have to live with an extremist oromo like you.

 7. Abaa Caala በኦነግና በጁዋር፣መሀመድ ሐሰን፣ህዝቅኤል ጋቢሳ ትርክት ተጠልፈህ ማንነትህን ለነሱ አስረክበህ የሚያስቡልህ እነሱ ሁነዋል።
  አቼምየለህ ማህደር ፈልፍሎ ቃል በቃል እውነትን አቀረበልህ አንተ ግን ከላይ የጠቀስኩት ሰዎች ተረት ጋር ስለተላመድክ ሲስተምህ እውነት የሚባል ነገር አስጠልቶታል በእውነቱ እንዳንተ አይነት ተከታዮች ህክምና እንጅ ምሁራዊ ውይይት አያስፈልጋቸውም።
  በየድረ ገጹ እውቀት የሚያካፍሉንን በእውቀትና መረጃ ሳይሆን በኦነጋዊ ስድብ ታስተናግዳቸዋለህ። ተው ወዳጄ የሳይበር ቄሮ አትሁንብን። በተረፈ በር ትተህ ተሳደበ ባለፈው ሰርጸ ደስታን አሁን ደግሞ አቻምየለህን እንዲህ እንዲህ እያልክ በመገላገያው ትገላገላለህ። ታከለ ኡማ አንድ ቦታ እንዳይሰጥህ እነሱም ሰው በዝቶባቸው እየቀነሱ ነው። ሙሉስራህን ስድብ ላይ አድርገው።

 8. @ SAREMTA

  ===> “The gurage have no root similarity or linguistic similarity with oromo people. As a child I heard parents talking of times of oromo invasion, killing, cutting private parts and rampaging parts of gurage up until Minilik unified the country.”

  That is also what the other NATIVE Ethiopian tribes know. And with this: “… I heard parents talking of times of oromo invasion, killing, cutting private parts and rampaging parts of gurage up until Minilik unified the country” you are confirming what Achamyeleh wrote here: ” የጨቦ ተወላጁ አቶ ምስጋናው በላቸው በመጽሐፋቸው ገጽ 66 እንደነገሩን አባገዳ አካባቢውን ከወረረው ጀምሮ የነበረው ስቃይ፣ ጭቆና መከራ ተወግዶ በጨቦ ምድር ፍቅርና ሰላም የወረደው ዳግማዊ ምኒልክ ሲደርሱላቸውና ከአባገዳ ባርነት ሲያላቅቋቸው እንደሆነ ጽፈዋል። ”

  Native Ethiopian tribes babysitted oromos for too long, enough with that ! We must start telling the truth about oromos. We must start telling the oromo secret 😉 ,namely that they were driven out of their homeland by Bantus and Somalis and arrived in Ethiopia in 16th century. They should be grateful to Ethiopia, which allowed them to stay, otherwise Native Ethiopians could do to oromos what the Bantus and Somalis did to them before.

  ===> ” I still expect Oromo’s and Oromo fanatics to respect others feeling, culture and value and keep their “stupid” (for those of us who don’t care about it) culture to themselves and stop this expansionist idea/culture here and fight there to own others. ”

  The only way we can force oromo extremists to behave is by telling the “oromo secret” 😉 , namely that they were driven out of their homeland by Bantus and Somalis and arrived in Ethiopia in the 16th century. Ethiopia gave them shelter. So, Native Ethiopian tribes need to tell the oromo newcomers, to be grateful to Ethiopia and to behave or to go back to where they came from.

 9. ደግነቱ ጉራጌ አራዳ ነው። እንዳቻምየለህና አንደ ኦሮሞ አክራሪዎች ባላገር አይደለም። ጉራጌ በአማራ በኦሮሞ ምድር ሓብት እንዳፈራ ያውቃል ።

 10. ደግነቱ ጉራጌ አራዳ ነው። እንዳቻምየለህና አንደ ኦሮሞ አክራሪዎች ባላገር አይደለም። ጉራጌ በአማራ ሳይሆን በኦሮሞ ምድር ሓብት እንዳፈራ ያውቃል ። እውነት እንነጋገር ከተባለ በስራ ምክንያት ስንቀሳቀስ የጉራጌ ሱቅ በአማራ ክልልሎች አለማግኘቴ እጅጉን አስገርሞኛል ። ምክንያቱም ጉራጌ ሌባ ነው የሚል taboo አለ።

 11. @ Fekadu

  ===> አንደ ኦሮሞ አክራሪዎች ባላገር አይደለም።

  Whats up Fekadu ?

  Do you have the ability to think rationally or are you an irrational person ?

  What does this shit supposed to mean —-> ባላገር አይደለም ?

  Gurages are in Ethiopia for thousands of years, don’t you know that ?
  They are native Ethiopians, how are they supposed to have no land or homeland ? Ethiopia is their land. Shewa is their land, etc.

  I don’t know your tribe, if you are from a non-native Ethiopian tribe, making a statement like that would make you a shameless retarded clown.

  ===> ጉራጌ በአማራ ሳይሆን በኦሮሞ ምድር ሓብት እንዳፈራ ያውቃል ።

  Fekadu,
  you have a serious mental problem. You are brainwashed by TPLF.
  Better forget or unlearn this tribalist mindset ===> በአማራ ሳይሆን በኦሮሞ ምድር
  That kind of tribalist thinking is poisonous, dangerous and wrong. Ethiopia belongs to all Ethiopians, every inch of the land.
  People with your kind of tribalist mindset should be put in reeducation camp to cleanse their mind from TPLF’s tribalist poison.
  All Ethiopia has always belonged to all Ethiopians, with the exception of the few decades of TPLF rule. We never had tribal homelands in Ethiopia.

 12. @Lema
  Thanks for responding to @Fekadu apparently a tribalist.

  Many Ethiopians have concern about the direction the country is heading. We all are hoping for better future- Ethiopia lead by reason, law and democracy instead of Ethnic strife. The current regime is hoped to be tasked at least the initial stage of this. However, from what we hear and see, responsible citizens have a real concern of what is going on specially when ethnic extremists appear to strive to ruin the country.

  Extremists appear even to have census of who is working where and what is owned by who which is a dangerous precedence should any conflict of ethnic nature expand (we have pockets of them already with mass eviction!!); this also shows the extent of hate (I will head-but you with another if you don’t support me or are not with me tactic).

  Oromo extremists instead of coming to the center and take responsibility to unify, democratically lead the country, respect others culture they are trying to force their centuries old tribal system in the mouths of neighboring Native people. It would not be that bad if that system was an advanced modern one liked by all others. In reality, many segments of Oromo people themselves (Muslims/Christians) don’t like to practice it.
  In the west we have been called the only Christian nation that remained in darkness in terms of civilization (compared to west; this may be partly due to centuries of ethnic atrocities ormo invasion included and Muslim war-gragn war destroyed much of the country and Islamized large swath of the land-good reason to be skeptical of Muslim extremism and support from our old enemies Turks, Egypt and Arabs)

  I don’t even understand why oromo leaders/extremists are mentally sick with this every thing is ours (Kegna) mentality and imposing trash on others. Is there a way they could stop doing this?

  Trigrian extremist suffered similar mental illness robbed, destroyed, rapped the country in our face, led us to this mess while they were expected to lead the nation their ancestors were part in building. Now they retreated into their den and still blabbering to hide their unhealed wound

  Good bless Ethiopia and its innocent people

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.