የኮሌራ ወረርሽኝ ተጠቂዎች ቁጥር 614 መድረሱን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ

የኮሌራ ወረርሽኝ ተጠቂዎች ቁጥር 614 መድረሱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ወረርሽኙ በሀገሪቱ በሚገኙ 4 ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ መከሰቱን አስታውቋል።

እስካአሁን ባለው መረጃ በኦሮሚያ 294፣ በአማራ 198፣ በሶማሌ 33፣ በትግራይ 18፣ በአዲስ አበባ 70 እንዲሁም በድሬዳዋ 1 ሰው በበሽታው መጠቃታቸውን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬተር ዶ/ር በየነ ሞገስ አስታውቀዋል፡፡

የተጠቂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት ምክትል ዳይሬክተሩ፤ ከሳምንት በፊት በበሽታው 525 ሰዎች ተያዘው ነበር ብለዋል፡፡

የተጠቂዎች ቁጥር አሁን ባለው ሁኔታ ወደ 614 አሻቅቧል፤ በእስካሁኑ መረጃ መሰረት 16 ሰዎች በዚሁ ወረርሽኝ ህይወታቸው አልፏል፡፡

ከእነዚህ መካከል 14ቱ በአማራ ክልል 2 ደግሞ በኦሮሚያ ክልል መሆናቸው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ወረረሽኙን ለመቆጣጠር ቅንጅት ተፈጥሮ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች 18 የለይቶ ማከሚያ ቦታዎች ተቋቁመው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ማረሚያ ቤቶች፣ ማገገሚያ ተቋማት እና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከነገ ጀምሮ የኮሌራ ክትባት መሰጠት እንደሚጀምርም ተገልጿል፡፡

በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከ17 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሁለት ዙር በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት የሚሰጥ መሆኑን አንስተዋል።

በፍጹም ግርማ/ebc

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.