ወያኔ እና በኤርትራ ጉዳይ ላይ ያላት ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም – አለም ታፈሰ

የኤርትራ ጥያቄ
የኤርትራ ጥያቄ መንስኤው ምንድነው? ለዚህ ጥያቄ መሠረታዊ መልስ ለመስጠት የሚከተሉትን ታሪካዊ መረጃዎች መመልከት ያስፈልጋል።
ሀ. ሁለት ህዝቦች፣ ሀገሮች ወይም ብሄሮች በተለያየ ጊዜ የየራሳቸውን አስተዳደር ይዘው ቆይተው አንዱ ባንዱ ላይ የሚያደርገው በሃይል የተደገፈ ግዛት የቅኝ እገዛዝ ተግባር ነው።
ለ. እንዲሁም ሁለት ሀገሮች በሁለቱም ፈቃድና ፍላጎት የየግላቸው መብት ጠብቅው ከተባበሩ በኋላ እንደኛው ሌላውን ቢያምጽ እርምጃው የቅኝ አገዛዝ እርምጃ ነው።
እላይ በተጠቀሰው ታሪካዊ ሃቅ መሠረት የኤርትራ ጉዳይ ስንመረምር የሚከተሉት ነገሮች ያጋጥሙናል።
ሀ. በ1890 ዓ.ም አካባቢ ኤርትራና ኢትዮጱያ ለየብቻቸው የተለያየ አስተዳደር ይዘው ይኖሩ ነበር። ይኽውም ኤርትራ እንደ የኢጣሊያ ቅኝ ግዛት ኢትዮጵያ ደግሞ እንደ አንድ “ነፃ” አገር ሆነው የኖሩ ነበር።
ለ. በ1952 ዓ.ም ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌደረሽን መተዳደር በጀመረችበት ጊዜ ሁለቱም ሀገሮች ያደረጉት ስምምነትና የተባበሩት መንግሥት ውሳኔ ኤርትራ ራሷን የቻለች አገር መሆንዋን ይጠቅሳል።
ሐ. ይሁን እንጅ በ1962 ዓ.ም ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የወሰደችው እርምጃ ስምምነቱ “አንደኛው ወገን ብቻ ለተባበሩት መንግሥታት ሳይጠየቅ ሊጥሰው አይችልም።” የሚለውን ሕግ በግለጽ የሚፃረር ሆኖ ይገኛል።
ስለዚህ ኤርትራ ውስጥ የሚደረገው ትግል ያላንዳች ጥርጥር ሃቀኛና ታሪካዊ መሠረት ያለው ፀረ- ቅኝ አገዛዝ ትግል ነው።
                              **********
ይህ መረጃ ኤርትራ በአይል ከእናት አገሯ ኢትዮጵያ በጣሊያን መነጠሏን አይገልፅም:: በተጨማሪም የኤርትራ ህዝብ የጥንቷን ገናናዋን እና የረዥም ዘመን ባለታሪኳን ኢትዮጵያን ከመሠረቱት መካከል መሆኑን ዘንግቷል:: በቀላሉ ወያኔ ከሻቢያ ባልተናነሰ መልኩ የኤርትራን መንገጠል ትፈልግ እንደነበር በግልፅ ያሳያል:: ተወደደም ተጠላም ወያኔ ድሮም ሆነ አሁንም ፀረ-ኢትዮጵያ ናት:: እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ለ27 አመታት ኢትዮጵያ በወያኔ መገዛቷ እና አሁንም ወደ ቀድሞ ስልጣናቸው ለመመለስ የሚያደርጉት መፍጨርጨር ነው::
ምንግዜም የናንተ;
አለም ታፈሰ

3 COMMENTS

 1. “ሀ. በ1890 ዓ.ም አካባቢ ኤርትራና ኢትዮጱያ ለየብቻቸው የተለያየ አስተዳደር ይዘው ይኖሩ ነበር። ይኽውም ኤርትራ እንደ የኢጣሊያ ቅኝ ግዛት ኢትዮጵያ ደግሞ እንደ አንድ “ነፃ” አገር ሆነው የኖሩ ነበር።” ይህ እጅግ የተሳሳተ አተያይ ነው!!

  ከ1890 ዓ. ም በፊት ለመቶና ሺ አመታት “ኤርትራ” የኢትዮጵያ አካል ነበረች:: ኤርትራ የሚባል ስም ወይንም ሀገር ወይንም መንግስት አልነበረም:: ትክክለኛ ስሟ ምስራቁ ባህረነጋሽ ደጋማው ምድሪ ሀማሴን ነበር::
  በአስብ ለጣልያን መርከብ ነዳጅ ማራገፊያ የተገዛው ቦታ ተስፋፍቶ ለኤርትራ ቅኝ ገዢዎች በመደላደል Jan 1,1890 የዛሬይቱ ኤርትራ በጣልያን ገዢዎች Mare Erythraeum ( የጥንት የላቲን የቀይ ባህር ስም – Red Sea) በጣልያን ንጉስ ኤርትራ የሚባል መጠሪያ አግኝታለች::ከ 1890 የጣልያን ንብረትነት ውጪ ኤርትራ የብቻዋ ታሪክ የላትም:: በ 40 አመታት በጣልያን ስትገዛ ኤርትራ በአለም ካርታዎች በሙሉ የምትመዝገበው as an occupied territory . ነፃ ሀገር ወይንም መንግስት ሆና አታውቅም:: ይህ ግልፅ ታሪካዊ ሀቅ ነው::
  ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራ ነፃ ሀገር የሆነችው በታጋይ ኤርትራዊው መለስ ዜናዊ ወዲ አዲቋላ ነው::እኔ በግሌ ኢሳይያስ አፈወርቂ ስልጣን ከልቡ ቢወድም ከኢትዮጵያ መገንጠል እንደ መለስ ያቃጥለው ነበር የሚል እምነት ኖሮኝ አያውቅም::

 2. አዎ ኤርትራ ወይንም ባህር ምላሽ፣ በርግጥ የኢትዮጵያ አካል እንደነበረች አለም ያወቀው ጠሃይ የሞቀው ሃቅ ነው።
  ክህደት አይነተኛ ባህርያቸው ስለሆነ ፣ መሪዎቿም ሆኑ የትግሬ አጋሮቻቸው ፣ አዲስ ታሪክ ፈትረዋል።
  እንደኔ፣ ከነኚህ ፍጡራን ጋር በመልክና በታሪክ፣ በባህል ብንገናኝም፣ በስነልቦና፣ እጅግ የተለያየን ነን። እነኝህ ሰዎች ኢትዮጵያውያንን እጅግ በድለዋል። ይቅር የማይባል ግፍ በኢትዮጵያን ወታደች ፈጥመዋል።
  እንክዋን ዔርትራ፣ ትግሬ ጥርግ ብሎ ከኢትዮጵያ ይውጣልን። እነርሱን ለመሰለ ነቀርሳ፣ ብዙ ነፍስና ንብረት ጠፍቷል። ከነርሱ መገላገል የማንም ኢትዮጵያዊ ምኞት ነው።
  የትግሬ ህዝብ እንኚህን አረመኔ መሪዎቹን ለፍርድ ሲያቀርብ፣ ዎይንም ራሱ ሲቀታቸው ብቻ ነው፣ ከቀረው ኢትዮጵያ ጋር አንድነቱ የሚዘለቀው።
  ጣልያኖች ኢትዮጵያን ወርሮ ፣ ለታላቅ ውርደትና ስቃይ የዳርገውን መሪያቸውን ሙሶሎኒን ቁልቁል ነበር የሰቀሉት ።
  እነ አባይ ዐሃይ፣ ሴሰኛው ደብረዖዮን፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ዎልዱ፤ ስብሃት ነጋ፣ ጌታቸው አሰፋን ።ሳሞራ የሱፍን ወዘተን አስሮ ለፍርድ ሲያቀርብ ብቻ ነው ።

 3. ሳተናው የዚህ ጽሁፍ አላማው ገብቶሀል? ኤርትራ ነጻ ሀገር የነበረችና በኢትዮጵያ ቅኝ ሙያዟን ነው የአንተም እምነት እንዱህ ሁኖ ካወጣኸው ደህና ነው ሳይገባህ ከሆነ ለወደፊት ጽሁፎች ይመርመሩ።
  በአንድ ድንጋይ እንዲሉ አንትን ለማስደሰት ወያኔ ምናምን ብሎሀል። በመሰረቱ በሁለቱ ትግሬዎች መሀል ልዩነት አለ ብለህ አታስብ።
  እነሱ ከበቂ በላይ የመገናኛ መስመር ስላላቸው ከዚህ እንኳን ብታባርሩልን። ጸሀፊው ሀጎስ ነው በኔ ይሁንብህ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.