ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የአማራ ክልል ገለፀ

በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ከተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ግድያ ጀርባ አሉ ተብለው የተጠረጠሩት ብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የክልሉ የሰላም ግንባታና ህዝብ ደኅንነት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በትናንትናው ዕለት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ብርጋዲየር ጄኔራሉ በልዩ ኃይሎች ታጅበው እንደመጡና በመጀመሪያም የርዕሰ መስተዳደሩ አጃቢዎች ላይ ተኩስ እንደከፈቱ፤ ቀጥለውም የክልሉ አመራሮች ላይ የተኮሱ ሲሆን በዚህም ሦስቱ እንደተመቱ አቶ ገደቤ ይናገራሉ።

• ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው

•ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ

•መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች

“ጥቃቱ በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው” ያሉት አቶ ገደቤ የፀጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮና የአዴፓ ጽህፈት ቤት ላይም ጥቃት እንደደረሰ ገልፀዋል።

“ጥቃቱ ያልተጠበቀ ነው” የሚሉት አቶ ገደቤ በወቅቱም የክልሉ ፀጥታ ኃይል አካባቢውን ለመቆጣጠር ጥረት ባደረገበት ወቅት ብርጋዲየር ጄኔራሉ እንዳመለጡ ገልፀው፤ ከርዕሰ መስተዳድሩና ከአማካሪያቸው በተጨማሪ አጃቢዎቻቸው የተገደሉ ሲሆን እስካሁን ባለው ሁኔታ የሟቾች ቁጥር እንደማይታወቅ ገልፀዋል።

በባህርዳር ሁኔታዎች ቢረጋጉም የርዕሰ መስተዳድሩን ሞት ተከትሎ ከተማዋ በድንጋጤ መዋጧን አቶ ገደቤ ተናግረዋል።

“ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ህዝብ ሌት ተቀን የሚሰራ ሰው ነበር፤ እንዲህ ባለ ሁኔታ መሰዋቱ በጣም አስደንጋጭና አሳዛኝ ነው” በማለት አቶ ገደቤ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

BBC

 

1 COMMENT

  1. You guys use western media like BBC and DW as your sources, that is not good in this case.
    You or the sources do not mention that the Abiy regime and the so-called EPRDF, including ADP, are tribalists and therefore are unpopular among Ethiopians, as written below.

    ” በየከተማው ሰልፉን በሚያካሂደውና ለውጡ ፈላጊው ሕዝብና ለውጡን በሚመሩት የመንግሥቱ ክፍል መካከል ክፍተት ተፈጥሯል። ለምሳሌ፤ የትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባር በሰንደቅ ዓላማችን ላይ ያስቀመጠውን ምልክት ጥለው፤ አረንጓዴ፣ ብጫና፣ ቀይ ቀለማት ብቻ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፤ ሕዝቡ እያውለበለበ፤ “ተደምሬያለሁ!” እያለ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም እያሞገሰ ወጥቷል። ነገር ግን፤ የትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባርን ሰንደቅ ዓላማ ለማስከበር፤ መንግሥታዊ መዋቅሩ፤ እኒህን አውለብላቢዎች እያሰረ ነው። ሕዝቡ ቀድሞ፤ “አንለያይም!” “አንድ ነን!” “በዘር አጥር መከፋፈሉ ያብቃ!” “ኢትዮጵያዊ ነን!” እያለ ነው። አሁንም በየክልሉ ያሉትን መሪዎች ይሄ የሚጋፋቸው ሆኗል። ”

    Source: ethioforum dot org

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.