የአማራ ሳታለያት ቴሌቭዥንና (አስራት) ራዲዮ ጋዜጠኞች ታሰሩ

የአሥራት ሚዲያ አስተባባሪና መስራች አቶ በሪሁን አዳነ “የመፈንቅለ መንግስት” ተሳታፊ ነህ በሚል ዛሬ በአራዳ ፍርድ ቤት ችሎት ክስ እንደተመሰረተባቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከአቶ በሪሁን ጋር ወጣት ጌታቸው አምባቸውም ለእስር እንደተዳረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ሁለቱም የአስራት ሜዲያ ባልደረቦች በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በጨለማ ቤት ውስጥ እንደታሰሩና ጠያቂም እንደተከለከሉ አስራት ሜዲያ ዘግቧል።

ሰኔ አስራ አምስት ቀን ተፈጸመ ያሉትን “መንፈቀለ መንግስትን” ተከትሎ ፣ ከመንግስት ከሚሰጡ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑና የተዘበራረቁ መግለጫዎች ውጭ፣ ምን አይነት ገለልተኛ ሆነ ከዚያ ወገኝ የሚሰጥ መግለጫ የሌለ ሲሆን፣ በኦህዴድ/ኦዴፓ የሚመራው ገዢው ፓርቲ ልክ ህወሃት ሲያደርግ እንደነበረው ህዝብ እነርሱ ከሚሰጡት መረጃ ውጭ ሌላ ምንም አይነት መረጃ እንዳያገኝ ኢንተርኔቱን ጠርቅሞ በተለይም በአማራ ክልል ዘግቷል።

ከአስራት ሜዲያ በተጨማሪ የባላደራው ምክር ቤት እንዲሁም  የአብን አባላት እየታሰሩ ነው።

 

2 COMMENTS

  1. በመሰረቱ መፈንቅለ መንግሥት አልተደረገም። የሆነው ረብሻ ነው። ያው የሰው ህይወትን የቀጠፈ። ይህ በጅምላ ገፈፋና እስር ችግር ይፈጥራል። የተማታበት የአዲስ አበባ ፓሊስ የተጣራ መግለጫ እንኳን መስጠት አይችልም። አሁን በሆነ ባልሆነው የባለአደራውንም ሆነ ሌሎችን በዘፈቀደ ጨለማ ቤት ውስጥ ማሰሩ ውሎ አድሮ ሌላ መዘዝ ያመጣል። ትላንት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ያፈናቀሉና የገደሉ ዝም ተብለው ዛሬ መረጃ አልባ ሰውን ማገት ተገቢ አይደለም። አደብ መግዛት ይኖርብናል። እኔ በግሌ ጀ/ል አሳምነው ጽጌ የቀቢጠ ተስፋ ወይም የሚያሳብድ መድሃኒት ካላጠጧቸው በስተቀር በህዝባቸው ላይ ይተኩሳሉ ብሎ ማመን ይከብደኛል። ግን የፓለቲካ ሽኩቻና መናናቅ ከነበረ ቁጣንም መቆጣጠር ካልተቻለ በጊዜአዊ ግፍልተኝነት እንዲህ ያለ መገዳደል ሊኖር እንደሚችል መገመት ይቻላል። የፓለቲካ መቆሳሰል ሁልጊዜም ውጤቱ ሞት ነው። አሁን በማህል መንግሥት ትዕዛዝ በየምክንያቱ የሚታፈሱት ሆን ተብሎ የሆነውን ነገር በእርግጠኛነት ህዝባችን እንዳያውቀው ከሆነ ጊዜአዊ ማደናገሪያ እንጂ እውነቱን ሽፍኖት አይቀርም። ንገሩን እስቲ ጀኔራሎችን የገደላቸው አለ ወይስ ሞቷል? በህይወት ካለና መናገር የሚችል ከሆነ በገለልተኛ አካል ሁኔታውን እንዲያስረዳ ቢጠየቅ መልካም ይመስለኛል። እንዲያው ዝም ብላችሁ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገ አትበሉን። አናምናቹሁም። ደግሞም በዓለም ላይ ከሚደረጉት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች የሚሳኩት ጥቂቶቹ ናቸው። በሃገራችን የቆየ ታሪክ ውስጥ ሁለት ጊዜ የተሞከረው የመንግሥት ግልበጣ ገልባጮችን ነበር ለዝንተ ዓለም ያስተኛቸው። ያው ደርግ ግን በማታለል በእድሜ የገፉትን ንጉስ በቀስታ የሾኬ ጠለፋ ለማውረድ በቅቷል። የደርግም አወዳደቅ የሮም አወዳደቅ ነው የሆነው። የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል እንዲሉ የጄኔራሎችን ህልፈት አስመልክቶ በመቀሌ በተደረገው ስብሰባ ላይ ግብታዊ በሆነ መልኩ ጋዜጠኛ ለጠየቃት ጥያቄ ምላሽ የሰጠችው የትግራዪ ምክርቤት አፈጉባኤ እንዲህ አለች። “ትግራይ የጀግና ሃገር ናት። እንዲህ እየሞትን እስከመቼ፤ ይህን የሰሩት የደርግ ትራፊ ባለስልጣኖች ናቸው” በማለት ሲናገሩ ጭፍን ሃሳብን ሁልጊዜ የሚነዛው Tigrayonline የተሰኘው አፍቃሪ ወያኔ ድረገጽ ደግሞ መገንጠል አለብን ይለናል። ሁለቱም ሃሳቦች የፓለቲካ ቅጥፈት አለባቸው። ጀግና ጠፍቶ አይደለም ሁለቱ ሃገራቸውን የሚወድ ጄኔራሎች የተገደሉት። እምነት የለሽ፤ ፈጣሪን የማይፈራ፤ ምን አልባትም በዘር ፓለቲካ የሰከረ የአመኑት ጠባቂያቸው እንጂ። ስለሆነም ሲዘከሩ እንደ ኢትዮጵያዊ እንጂ በጎሳና በዘር በመከፋፈል የሚደረገው ጠንጋራ ፓለቲካ ሁላችንንም እውር ያደርጋል። መቆም አለበት። የመገንጠሉም አባዜ ለያዛችሁ የትግራይ ተወላጆች አስመራ ቅርብ ነው ለምን ወደዚያ አትሄድም የቆመ ቤትን ለማፍረስ ሴራ ከመሸረብ። ባጠቃላይ በሶሻልና በሌሎች ዜና አናፋሽ ሚዲያዎች የሚወራውንና የሚባለውን ሁሉ ሳያኝኩ እየዋጡ ሃገርና ህዝብን የሚያፈርስ ሃሳብ የምትሰነዝሩ በተለይም ዘርና ቋንቋን ተገን ያደረጉ ስድቦችና ጽሁፎች ጠቃሚ አይደሉም። ግን አንድ ነገር ለእኔ መቶ ፕርሰንት ግልጽ ነው። የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ አልተደረገም። ተደረገ ከተባለ ሌላ ለህዝብ ያልተነገረ ነገር አለ ማለት ነው። የአዲስ አበባው ግድያና የባህርዳሩ ግብግብ እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት አንድም ነጥብ ቢሆን የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ለመሆኑ በምንም ሂሳብ አያመላክትም። የደበቃችሁት ሌላ ነገር ካለ ንገሩን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.