ክንደ ብርቱው ኮነሬል አለበል አማረ! (አብሳሌም ፍቅሩ)

ኮነሬል አለበል አማረኮነሬል አለበል አማረ በብቃታቸው አንቱ ከተባሉ የጦር መኮንኖች አንዱ ነው። ኮነሬል አለበል ለወያኔ ስርአት አልተመቹም በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔን ስርአት ንደው አማራዊ መንግስት ለመመስረት እያደቡ ነው ከተባሉት የአማራ የጦር መኮንኖች ውስጥ አንዱ ነበር። ሚያዚያ 8 2001 “የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል” በሚል እኚህ መኮንኖች እንዲታፈኑ ትእዛዝ የወጣ ቢሆንም በኮነሬሉ ጥበብና በፈጣሪ እርዳታ ሊያመልጣቸው ችሏል። አምልጧቸውም እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም። ይህንን አንባገነን ስርአት በመጣል የአማራን ህዝብ ህልውና ከጥፋት መታደግ የሚቻለው አማራ በአማራነቱ ሲደራጅ ብቻ ነው ብሎ በማመን ለዚሁ እቅዱ በወቅቱ አመቺ ወደ ሆነችው ኤርትራ አመራ። ከ2002 አንስቶ አማራ የሆኑ ታጋዮችን በመሰብሰብ፣ ካሪኩለም በማዘጋጀት፣ የድርጅቱን ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ በማርቀቅ፣ የውስጥና የውጭ አወቃቀሮችችን በመዘርጋትንና ኤርትራ ውስጥ የድርጅቱን ካምፖች በመመስረት አሳልፎ የካቲት 2002 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን መስርቶ ድርጅቱን በሊቀመንበርነት እስከ 2004 ለመምራት የቻለ ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ቀጥሎ አማራ በአማራነቱ ተደራጅቶ መብቱን ማስጠበቅና ወደርተኞቹን መመከት አለበት ብሎ ብረት ያነሳ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የበኩር ልጅ ነው።

ይህ ጀግና አማራ በወታደራዊ ብቃቱ የተመሰገነ፣ በአማራ ብሄርተኝነትና በአማራ ህዝብ ትግል የማይደራደር፣ አማራ ብሄርተኞች ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ እውቀታቸውና በአመራር ችሎታቸው አንቱ የተባሉ ታጋዮች እንዳሉት ዋቢ ምሳሌያችን ነው። ግንቦት 7 ከሻቢያ መንግስት ጋር በመመሳጠር የአዴሃንን ትግል ለማኮላሸት በሚውተረተሩበት ጊዜ ድርጅቱን ከግንቦት ሰባትና ከሻቢያ ጣልቃ ገብነት ለመከላከል በሚችለው ሁሉ ሞክሮ በመጨረሻም ከኤርትራ በመውጣት የስደት ትግሉን በአውሮፓ አድርጎ ነበር። ይህ እንቁ የአማራ ታጋይና የህዝባችን መከታ አብረን በሰራንበት ጊዜ ሁሉ ለእኛ ለወጣቶቹ የፖለቲካን ሀሁ ያስቆጠረን መምህራችን ነው። በአሁኑ የአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ ካየኃቸው የትግል አመራሮች ሁሉ አምጡ ድገሙ ቢባል እንደ ኮነሬል አለበል አማረ አይነት ሁሉን ያሟላ ፖለቲከኛ ማግኘት ፈታኝ የሚሆን ይመስለኛል። ለአማራ ህዝብና ለትግል አጋሮቹ ያለው ቅንነት፣ የፖለቲካ እውቀቱና ብስለቱ፣ በወታደራዊ አደረጃጀትና የስትራቴጂ ንድፍ ላይ ያለው ችሎታ፣ አንደበተ ርእቱነቱ፣ የአመራር ብቃቱ፣ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች በግልፅ ማወቁ … የትግላችንን መዳረሻ ምን መሆን እንዳለበት መረዳቱ… አረ ስንቱ… …

ይህ የፖለቲካና የስነምግባር መምህራችን የፕሮፌሰር አስራት የበኩር ልጅ ለሚወደው ህዝብ ዳግም በአገሩ ላይና በወደረኞቹ ፊት ሊታገል ባለፈው ክረምት ነበር ወደ ሀገሩ የተመለሰው። ወደ ሀገሩ ከተመለሰም በኃላ የአማራ ክልል የፀጥታና ደህንነት ምክትል ሀላፊ በመሆን ህዝቡን በቁርጠኝነት አገልግሏል።
 በስራ በአሳለፋቸው ጥቂት ወራትም ጀግንነቱን የጠላትን አከርካሪ በመስበር አስመስክሯል። በከሚሴ የሚገኙ አማሬዎችን ሲጨፈጭፍ የነበረውን የኦነግ ታጣቂ ልዩ ሀይሉን ይዞ በመሄድ ደምስሶ ተመልሷል።
 በሚያዚያ ወር አጣዬንና አካባቢውን ሲያሸብር የነበረውን የኦነግ አሸባሪ ቡድን ቦታው ላይ በመገኘት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ተመልሷል።
 ግንቦት ወር ላይ እንዲሁ በደራ አካባቢ ግጭት ሲፈጠር አማሬዎች ላይ ችግር ተፈጠረ በተባለበት ቦታ ሁሉ ፈጥኖ የሚደርሰው ኮነሬል አለበል የአካባቢውን ህዝብ አረጋግቶ የወረዳው አመራሮችም ተገቢውን ማጣራት አድርገው ጥፋተኞችን ወደህግ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቶ ተመልሷል። በዚህም ተግባሩ በእነ አብይ መንግስት ተከሶ ነበር (ኦሮሞዎችን ጨፈጨፍክ ተብሎ) በወቅቱ የነበሩት የአማራ ክልል አመራሮች ናቸው ከእሱ ወግነው ክሱን ያጣጣሉት። ይህ ድርጊት ግን ኦነጎቹ ጀ/ል ጌታቸው ጉዲናን፣ ጀ/ል ከማል አቢሶ በኮነሬሉ ላይ እንዲያቄሙ አድርጓቸው ነበር። ዛሬ እነዚህ ጀነራሎች የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች ሆነው በፌደራል መንግስቱ የተሾሙ ሰዎች ናቸው። እንደተመኙትም ጀግናውን ኮነሬሉ በፍልሚያ ሜዳ ማንበርከክ ቢያቅታቸው በተዘዋዋሪ በፈበረኩት ድራማ ከእጃቸው አስገብተውታል። ነፍሱን አስይዞና ጠላትን ፊት ለፊት ገጥሞ ድል ለነሳልን ለዚህ ብርቱ ጀግና ድምፅ እንሁነው። በጠላት ፊት ሞገስ ሆኖልናልና ከጎኑ እንቁም።

በባሕርዳሩ ክስተት ሰበብ ከታሰሩ አማራዎች መካከል የተወሰኑት ስም ዝርዝር

1 COMMENT

  1. ከየካቲት 2002 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን መስርቶ ድርጅቱን በሊቀመንበርነት እስከ 2004 ለመምራት የቻለ ከዚያ በሆላ 2011 ዓ.ም የት ገባ? ለምን አርበኞች ተለይቶ አዲሃን አቋቋመ ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.