ጌታቸው አምባቸው በጨለማ ቤት! (ጌታቸው ሽፈራው)

እነ ጌታቸው አምባቸው የታሰሩበት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን (3ኛ) ጨለማ ቤት ነው። ቤተሰብ የላከላቸውን ምግብ እንኳ ከታሰሩበት ክፍል ወጥተው መቀበል አይችሉም። ፖሊስ ነው የሚያደርስላቸው። አየር ለማግኘት፣ ወደ ሽንት ቤት ለመሄድ የፖሊስን ይሁንታ ጠይቀው ነው። በቀን አንዴ ወይንም ሁለት ጊዜ ከጠባብና ቀዝቃዛዋ ክፍል መውጣት ቢችሉ ነው። በፖሊስ ይሁንታ!

ጌታቸው አምባቸው በጨለማ ቤት ውስጥ፣ በፖሊስ ይሁንታ መሆኑን ማሰብ ይከብደኛል። በገዥዎቹ አዝናለሁ! ጌታቸው አምባቸው ብዙዎችን የሚያግዝ ሰው ነው። አሥራት ሚዲያ መኪና ከመግዛቱ በፊት ለዘገባ ስናንከለከልው የነበረው ጌታቸውን ነው። (እንደ ጌታቸው የሚያግዘን ሌላኛው ጓደኛው በወከባ ላይ ነው) ጌታቸውም የትም ይሁን ዘገባ እንዳለን ገልፀን ለጋዜጠኞች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥልን ስንጠይቀው ስራው ጥሎ በፍጥነት ቢሯችን ይደርሳል። በተለያዩ ቢሮዎች የምናስፈፅማቸው ጉዳዮች ሲኖሩ ይዞን ሲዞር የሚውለው ጌች ነው። የራሱን ስራ ትቶ የሚያስፈፅምን ጉዳይ ይበዛል። ለራሳችን ስራ ጠርተን ስናስጠብቀው ተሳቅቆ አያውቅም። የራሳችን ጉዳይ እንዲያስጨርስልን ጠይቀነው እየዘገየንበት እንደራሱ ጉዳይ ቶሎ እንድንጨርስ ሲወተውተን የሚው ትሁት ነው፣ ጌታቸው አምባቸው። የእኛን ጉዳይ ጨርሶ የራሱን ወይንም አግዘኝ የተባለውን የሌላ ሰው ጉዳይ ለመከወን እንደገና ይባክናል።

ብዙዎችን ስራቸውን እንዲከውኑ በበጎ ፈቃደኝነት ይዞ ሲዞር የሚውለው ጌች ዛሬ የእሱ እንቅስቃሴ በጠባብ ክፍል ተወስኗል። በፖሊስ ይሁንታ ተወስኗል። ይህ የሆነው ደግሞ ወንጀል ሰርቶ አይደለም። መከራ የገጠመው ሕዝብ ሌላ ችግር ውስጥ እንዳይገባ ለማረጋጋት መጣሩን እንደ ወንጀል ቆጠሩበት። አማራው እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ አካላት “ማበጣበጥ እንጅ ማረጋጋት አልነበረብህም” ብለው ጨለማ ቤት ውስጥ አሰሩት። “አጣርተን እናስራለን እንጅ አስረን አናጣራም” ሲሉን ከርመው አማራነቱን ብቻ አጣርተው አሰሩት። የብዙዎችን ስራ ሲያሳልጥ የሚውለው ጌታቸውን በጨለማ ቤት፣ በጠባብ ቤት፣ በፖሊስ ይሁንታ ውስጥ መሆኑን ሳስበው የሀገራችን ነገር ያሳዝነኛል። ገዥዎቹ፣ አሳሪነታቸው የከፋና መሆኑ ያሳዝነኛል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.