ኦህዴድ/ኦነግ በዐማራው የአደረጃጀት ድክመት ምክንያት ባንድ ድንጋይ ሁለት ሳይሆን ብዙ ወፍ መታ! (ይመኑ ወንድአለ)

በግላችን በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 3 አመታት የተከሰተውን ሂደት እንዲህ ቃኝተንዋል:-

ትህነግ በተለይ “ጠላት” ያለችው ዐማራው ጉሮሮ ላይ ቆማ የቻለችውን ሁሉ እያግበሰበሰችም አልጠግብ በማለቷ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል አመፅ እንደተነሳባት እና አብዛኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ እስካልታሰረ ወይንም እስካልተገደለ ድረስ ስልጣን ላይ እንደማትቆይ ስትረዳ ምን ማድረግ እንዳለባት አውጠንጥና የተለመደ የሸፍጥ ውሳኔ ከአሽከሮቿ ጋር ሆና አስተላለፈች::

ለትህነግም ሆነ ለኦህዴድ/ኦነግ ወዘተ ቅዠታቸው ዐማራ እና ኢትዮጵያ ናቸው በዛው ልክም የኢትዮጵያን ስም ካልጠሩ ዐማራውንም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ማታለል አይችሉም:: በመሆኑም የኢትዮጵያን ስም እየጠራ ግን ደግሞ በልቡ የኦህዴድ/ኦነግን የሸከፈው አብይ አህመድ ተመረጠ:: አብይ ኦህዴድ/ኦነግ እንደጠነከረ እና ትህነግ ጥጏን እንደያዘች በ”አንድነት” እና በዐማራነት የተደራጁትን በቃላት ማርኮ አፍረከረካቸው ብዙዎች ከኦህዴድ በላይ ኦህዴድ ሆነው ተገኙ::

እየቆየ ሲሄድ በተለይ የኦህዴድ/ኦነግ እየጠነከረ እና አስፈሪ እርምጃዎችን መውሰድ ግን እንደ ዐማራ የተደራጀውንም ሆነ በአንድነት ተደራጅተው በኢትዮጵያ ውስጥ በእውነተኛ እኩልነት መኖር የሚፈልጉ ሀይሎች እጅጉን ስላስደነገጠ ከአብይ ማደንዘዣ ሰመመን ነቅተው እንደገና መደራጀት እና መጠናከር ጀመሩ::

በመሆኑም ሁሉን “የኔ ብቻ” የሚለው የኦነግ/ኦህዴድ ሀይል እና በዐማራነትም ይሁን በአንድነት ድርጅቶች ውስጥ ተደራጅተው በኢትዮጵያ ውስጥ በእኩልነት መኖር የሚፈልጉ ሀይሎች መካከል ከፍተኛ ፍጥጫ መፈጠር ተጀመረ::

የ”ፌደራል” መንግስትን የተቆጣጠረው የኦህዴድ/ኦነግ መንግስት የኦህዴድ/ኦነግ የተደራጀ ሀይል እያደረሰ ያለው ጥፋት (ግድያ: ዝርፊያ: ማፈናቀል ወዘተ) ሳይሆን የሚያሳስበው በአንድነትም ይሁን በዐማራነት ተደራጅቶ ያለ ሀይል አቅም አበጅቶ ከእኩይ ግባቸው እንዳያስቆማቸው ነው::የሚያሳዝነው ተባብረው መስራት የሚገባቸው በእውነተኛ እኩልነት የሚያምኑ በዐማራነትም ይሁን በኢትዮጵያዊነት የተደራጁት ሀይሎች ተባብረው አለመስራታቸው ነው:: ለማንኛውም ኦህዴድ/ኦነግ ተሰብስቦ እርምጃ መውሰድ አለብን በሚለው ተስማማ ይህንንም አብይ አህመድ ሲፎክር የከረመ ቢሆንም በአቶ አዲሱ አረጋ በኩል ለእርምጃ መዘጋጀታቸውን በግልፅ አስነገረ::

ከዛም የኦህዴድ/ኦነግ ሊቀመንበር ጥጏን ይዛ ቁጭ ወዳለችው ግን ወደሚፈራት ወደ መቀሌ አምርቶ ከትህነጉ ሊቀመንበር ደብረፅዮን ጋር መከሩ የተስማሙትን ተስማሙ::

አሁን ማወቅ የምፈልገው ታላቁ እስክንድር ነጋ ወደ ባህርዳር እንዲመጣ ማን ሀሳቡን አነሳ: ማነው የጋበዘው የሚለውን ነው:: Nafkot Eskinder እባክሽ መልሱን አጣርተሽ ንገሪን:: የዚህ ጥያቄ መልስ በአንድ ድንጋይ ብዙ ወፍ ለመምታት መቼ እንዳቀዱ ፍንጭ ይሰጣል::

የመቀሌ ጉብኝቱን ተከትሎ ጭፍጨፋ እንዳቀደ ፍንጭ እንደሰጠ ለማወቅ አብይ አህመድ ደሴ ላይ የተናገረውን ልብ ይሏል:: ግፈኛውን ጌታቸው አሰፋን እንዳትነኩ ያለው ደብረፅዮን አሁን የዐማራ ልጆች ሲታሰሩ እና ሲገደሉ ከዚህ በፊት አድርጎ በማያውቀው መልኩ አብይ ላይ ከመፎከር ድጋፍ መስጠቱ የተቀናበረ ሴራ እንዳለ ማሳያ ነው::

የኦህዴድ/ኦነግ አገዛዝ ያሰበውን አይነት እርምጃ ለመውሰድ ለአለም መንግስታት ምላሽ እንዲሆን የሆነ ምክንያት ማግኘት እንዳለበት ያውቃልና የ”መፈንቅለ መንግስት” ድራማ ጥሩ ሆኖ ተገኘ ምክንያቱም የቱርኩን ኤድሮጋንን ጨምሮ ሌሎች አገሮች ላይ የሰራ የአምባገነኖች ስልት ነውና::

በዚህ መሀል ዐማራ የኦህዴድ/ኦነግም ሆነ የትህነግ ” ጠላት” መሆኑ ብቻ ሳይሆን በህዝቡም ሆነ በአዴፓ ባለስልጣናት መካከልም ከፍተኛ የሀሳብ ልዩነት ስላለ እና በባለስልጣናቱ መካከል የሀሳብ ውዝግብ ያለበት አዴፓ/ብአዴን በሩን ክፍት አድርጎ ተገኘ::

በዚህ አይነት operation ሁል ጊዜም collateral damages እና unintended consequences ስለሚኖሩ ምንም እንኳን ሁሉም የተከሰተው የግድ መጀመሪያ የታሰበው ላይሆን ቢችልም ኦህዴድ/ኦነግ በ”መፈንቅለ መንግስት” ድርማው በአንድ ድንጋይ ሁለት ሳይሆን ብዙ ወፍ መቷል:-

1. በጣም የሰጉትን ብ/ጄ አሳምነው ፅጌን ጨምሮ በርካቶችን የነቁ ያሏቸውን ዐማሮች ገደሉ/አሰሩ:: ይህ ብቻ አይደለም በሞቱት ምትክ እልም ያሉ የኦህዴድ/ኦነግ ሎሌዎችን ለመተካት እና የዐማራ ህዝብን ህይወት ከድጡ ወደማጡ የማድረግ እቅድ ያለ ይመስላል::

2. በየትኛውም መድረክ ሲያፍኑት የቆዩትን የባልደራስ እንቅስቃሴን በተለመደው የ”ሽብር ክስ” እንቅስቃሴ በመክሰስ ድርጅቱን በግልፅ ማገድ:: በመሆኑም የታላቁን እስክንድር ነጋን እንቅስቃሴ በሽፍንፍን ሳይሆን በግልፅ አግዶ ታከለ ኡማ የጀመረውን demographic re-engineering እንዲያስፈፅም እድሉን ያመቻቻል ማለት ነው::

3. በታሰበ እና በታቀደ መልኩ ከአንድ አካባቢ የመጡ የብአዴን ባለስልጣኖችን በመግደል ዐማራውን በክፍለሀገር መከፋፈል:: በዚህ አጋጣሚ የምር እንኳን በክፍለሀገር ኖሮ ቢሆን ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ማለፍ ሲገባቸው ለስንት የጠበቅናቸው ዐማራውን ሲከፋፍሉ ማየታችን አሳዝኖናል::

4. አብይ/አህመድ ለስልጣኔ ስጋት ይሆናሉ ያላቸውን ከአጠገቡ በማስወገዱ እና ስልጣኑን ማጠናከሩ ለአምባገነንነት (ethno-dictator) እና ኢትዮጵያ እስካለች ለ”7ኛ ንጉስነት” ቅድመ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ነው::

5. ኦህዴድ/ኦነግ ከሚደግፋቸው ውጪ ያሉ አዲስ የተፈጠሩ ቴሌቪዥኖች/ሬድዮዎች እና ሌሎችንም የመገናኛ ብዙሀን አውታሮች ድሮም “የምትይውን ለመስማት እንጂ ማን ያንቺን ፈቃድ ፈለገ” እንዳለው ፍየል በሰበብ አስባት መዝጋት እና ወደ መደርደሪያ ተጥሎ በነበረ “ፀረ ሽብር ህግ” ሰዎችን ከሶ ዘብጥያ በማውረድ አፈናውን አጠናክሮ ቀጥሏል::

ምንም እንኳን የኦህዴድ/ኦነግ ሰዎች ከሞላ ጎደል ያሰቡትን ቢያሳኩም እንዲህ ያለ የፖለቲካ ድራማ ሲሰራ ነገሮች ከታሰበው ውጪ የሄዱ መሆናቸው የሚታወቀው የሚያሰራጯቸው የተምታቱ ዘገባዎች ናቸው::

ኦህዴድ/ኦነግ የረሳው ግን ልክ እንደ ሁሉም አምባገነኖች በጉልበት እናሸንፋለን ብለው ማሰቡ እና አላግባብ ብዙ ደም ያፈሱ እንደሆነ እንጂ መውደቃቸው እንደማይቀር አለመረዳታቸው ነው (ለነገሩ እነ ኦህዴድ ethno-dictator እንጂ dictators ብቻ አይደሉም):: ኦህዴድ/ኦነግ አንድ ዐማራ ባሰሩ/በገደሉ ቁጥር እንደ ባህርዛፍ ብዙ ዐማሮች ከስር አቆጥቁጠው በዝተው እንደሚወለዱ አለማሰባቸው የተለመደ የአምባገነኖች ፀባይ ነው::

ስለሆነም የነቁ የዐማራ ልጆች የተገደሉት እና እየታሰሩ ያሉት በተጠና መልኩ በኦህዴድ/ኦነግ እና አጋሮቻቸው ሆኖ ሳለ የዐማራ ልጅ የገደሉህን ትተህ እርስ በእርስ ያውም ወደ ክፍለሀገር ወርደህ መከራከር suicide ከመፈጸም አይተናነስም እና ልብ ያለው ልብ ይበል:: ሌላው ቀርቶ ስህተት እንኳን ተፈጥሮ ቢሆን ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ብላችሁ ለጊዜው ዐማራውን አንድ በማድረግ ላይ ማተኮር ይበጃል ምክንያቱም ዐማራውን ከፋፍሎ ለማጥፋት እነ ኦህዴድ/ኦነግ ከነአጋሮቻቸው በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ ነውና::

ጆሮ ያለው ይስማ!

4 COMMENTS

  1. Oneg, odp wois woyanie, wois ginbot 7, “Amara kiflehager leyto litala new.” blachuh endtastegabu yenegerachuh. Yih endihon yenersu flagot new. Gin yemayhon ayhonm. Yilq yihn yemtastegabu mn yahl denqoro amara endehonachuh yasayal. Yih yemayhon lihon qerto masebachuh dedeb mehonachuhn yasayal. Yalawaqi sami nft yileqelqal nachuh. Semay yiwodqal blo endemecheneq new yenante neger. Yetelat mesariya nacheh, yelieln endihon eyasasebachuh.

  2. በአማራው ውስጥ ለተፈጠረው ልዩነት ምክንያቱ መፈተሽ አለበት። ጎጃሞች በተጠቃን ስሜት ውስጥ ናቸው። ከዚህ ቀደም ከወጥ ጽሁፎች እንደተረዳኩት በጎጃም ዞንና ወረዳ እበሌ ድረስ ሀላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ጎንደሮች እንደነበሩ ነው። አሁንም ፓርላማ ውስጥ እንዳሉም አንብቢያለው። ታዲያ የራኡን የነጠከው ሰው እንዴት ይተባበራል። በውነት ትልቅ ጥፋት ነው የተሰራው። ጎጃሞችን የመጠቃት ስሜት የዶላቸው አስተዳዳሪ ከጎንደር ስለመጣባቸው ነው፡ በውነት ያሳፍራል። ክልሉ ላይ የሞቱት 3ቱም ጎንደሬወ ከፍተኝስ ስልጣን ነበራቸው። ክልሉ ውስጥ ስንት ከፍተኛ አመራር ቢኖር ነው። ይህ ትክክል አይደለም። አንተም ብትሆን ምጣድ እንዳይሰበር አይጥ ትለፍ ማለትክ ትክክል አይደለም። አጥፊውን ለይቶ መናገር ሲገባ አማራ እንዳይበተን አትቃወሙ ማለት ተገቢ አይደለም።

  3. Adult stupidity & selfish mercenaries came from the day1 of The Reformist Pm Starting work,but some old mind victims self centered group & tplf tools mercenaries start working against the equality,justice,equal wealth distribution,&Ethiopia for all Ethiopian through equality and they are working the reformist pm&their group by hidden formation 100s media + NAMA +Eskendir’s + old mind victims elements all merging for work, the move developed up to coup attempt,By Labeling Amara people interest, but they are not belongs Amara people’s,not for the interest of Amara,they work for the goal of tplf by x&y matrix,which is by knowing well Designated& maneuvering&controlled by head owners(tplf)+the merger old mind victims self centerist and their blind stuff- Please leave&say stop Eskedir’s adult stupidity,… Don’t wish bad for anyone,don’t think for old superiority,don’t work for evil anti equality&respect all ethnic work only for respectful equal Ethiopia for all Ethiopian sense

  4. Adult stupidity & selfish mercenaries came from the day1 of The Reformist Pm Starting work,but some old mind victims self centered group & tplf tools mercenaries start working against the reform of equality,justice,equal wealth distribution,&Ethiopia for all Ethiopian through equality-Democratic move and they are working against the reformist pm&their group by hidden formation 100s media + NAMA +Eskendir’s + old mind victims elements all merging for work, the move developed up to coup attempt,By Labeling Amara people interest, but they are not belongs Amara people’s,not for the interest of Amara,they work for the goal of tplf by x&y matrix,which is by knowing well Designated& maneuvering&controlled by head owners(tplf)+the merger old mind victims self centerist and their blind stuff- Please leave&say stop Eskedir’s adult stupidity,… Don’t wish bad for anyone,don’t think for old superiority,don’t work for evil anti equality&respect all ethnic work only for respectful equal Ethiopia for all Ethiopian sense

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.