አዎን አብይ አታለለን (በፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው)

አዎን አታለለን አብይ  አህመድ በመሳጭ ንግግር ቅጥፈቱ
የዘመናት ታሪካችንን በምንመኘው መልክ በኢትዮጲያዊነቱ
ድርሳን መጽሃፍቱን  ከግራም ከቀኝ በመቀራረም መቃኘቱ
በዘፋኝ አዝማሪዎችን በንግርት ናና አብዩ ናና  ማሰኘቱ
የተጣሉ ጳጳሳት ኢማሞች  ለሰውር አላማው  ማስማማቱ
የታሰሩ  ወገኖቻችን ሳይቀር ከስደተኞች ጋር  ማምጣቱ

ሆኖም ወንበር ሲደላደል  የሕዝቡን ልብ ክፉኛ አማለለ
የጭቃ ጅራፉ ተከተለ  ዛቻው ፉከራውና ድራማው ቀጠለ
ሆ ብሎ የደገፈውን የአዲስ አበባን ወጣት በረሃ እየጣለ
በሁከት ፈጣሪነት ያለአግባብ በሃሰት  ሊወነጅል ተማማለ
የቡራዩ ጨፍጫፊዎችና የራሱን ግድያ ሞካሪ አቀማጠለ
ለደሞዝ ጭማሪ መጡ ያላቸውን ለመፈንቀል ነው አለ
የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ በማለት ከመሰሎቹ ተማከለ
እኔን ቢነኩ ኖሮ ከ እስከ ጅማ ጎሳን አካለለ
የለየለት ጽንፈኛ የምእራብ ወለጋ ጃል መሮን አከለ
ባንኮቹን ሲዘርፉ የገበሬ በሬ ሲያርዱ ምንም ያላለ
እስክንደር የአዲስ ፊንፊኔ መብት ይከበር ብሎ ስለታገለ
በጦረኛነት ፈረጀውና   ይዋጣልን ይለይልን ሲል ተንጎማለለ
በነጃዋር በነበቀለ ገርባ ክፉ ቅስቀሳ ህዝቡ በጌዲኦ ተፈናቅለ
ሃገሪቱ በመፈናቀል ከአለም ሃገሮች በቀዳሚነት ተብጠለጠለ
ይህን አይን ያወጣ ሃቅ በሚዲያው ሳይተነፍስ ህዝቡን አታለለ
በምሳሌ በተረት አሮጌ ቤት ሲፈርስ የሚወጣው ሲል አጃጃለ

ከዚያም ኢትዮጲያ ሱሴ ያለው ባልደረባው  ድብቅ ተቀመጠና
በጨፌ ኦሮሚያ  ስለዲሞግራፊና ልዩ ጥቅም በዘር ተነተነና
በአካባቢ  መሆን የሚገባውን ተገቢ ማካካሻ በዘር ቀመረና
የራሱን ዘር ሊጠቅም ሌላውን የበይ ተመልልካች አደረገና
የቦሌ ክፍለከተማ መጀመሪያ የዲሞግራፊ ፕሮጀክት ሆነና
መታወቂያው ለኦሮሞ ዘር ብቻ መታደል በይፋ ተጀመረና
ማታለሉ ቀጥሎ ነበር ግን አንዲት  ሴት አደረገችው መና

በዚያ የጨፌ ስብሰባ አዲሱ አረጋ  የደበቁትን ዘረገፈው
የአብይን ዋና ማታለያ ሿሿ አናደርግም ሲል ገለጠው
የአብይ ልዩ ተሿሚ ታከለ ኡማ ለኦሮሚያ የሚያደርገው
በሚዲያ  ፈጽሞ የማይነገረው እጅግብዙ ነው ሲለው
አብይ በእቅድ ይህን ሴራ እንዳደረገው ህዝቡ ለየው                                                                        በዩንቨርስቲ  ዘረኛ የነበረ ታከለን  እንደሰየመው
ከዚያም አታላዩ አማሮችን አምቦ ላይ ደገሰላቸው
አምባቸው ተታለለና ለዘር ልዩ ጥቅም ቆመላቸው                                                                                 የአማራ ብሄረተኛነት የከፋው  ነው ሲል አሞኛቸው

በዚህ ሁሉ ያልተገበረ የላስታው አንበሳ አሳምነው ነበረ
የዘረኞችን የከሚሴ የወልቃይትን ጭፍጨፋ የሰባበረ
በሁሉ ክልል የሚደረግ ለአማራ ልዩ ሃይል ያጠናከረ
በዚያ የተደበቁ ኦነጎችን በአባ ገዳ ሰንበቶ  የተነገረ
የኦህዲድ ጄነራሎች ወሬ ሃቅ በሃሰት እየተቀየረ
በአምባቸው ጫና በማድረግ የገዳዮቹ ክስ ተሻረ
አሳምነውን  ለማገት ለማስወገድ ሴራ ተጀመረ
ይህን ግን የላስታው  ጀግና ቀድሞ የነቃበት ነበረ
በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ተፋላሚ ለጊዜው ተቀበረ                                                                                                               የተለመደው ሴረኛ ሄርማን ኮሕን ጥላቻው ተጀመረ
ይህን ሪስን ማዳንን በቆየው ክፉ  ባሕሪው መነዘረ

ለስልጣን ካበቁት ሎሌያቸው ከአታላዩ ተባበረ
የፋሽስቶች ወረራ  በሃገራችን ላይ የተቀናበረ
ታሪካችን ነው በሃያላኑ መካዳችን ያለና የነበረ
ሊሰሙ ያልፈለጉ በራሳቸው ቆይቶ  የተጨመረ
ፈጣሪ ያታደጋታል ሃገራችን ከደረሰባት መከራ
ሁሌም ይሰማታል ጌታ  የቅኖች ሁሉ ባላደራ

2 COMMENTS

  1. This stupid guy is a pastor from hell. He is a disciple of devil.

    Stay away from the beautiful Oromia. Oromia does not want to entertain the devil and its disciples.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.