የባለአደራው ምክር ቤት መግለጫ ረብሻን በተመለከተ (ብርሃኑ ተክለያሬድ)

በመግለጫው ላይ አባይ ሚዲያን ወክዬ ታድሜ ነበር እናም መግለጫው በፅሁፍ ተነቦ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ መስጠቱ እስኪጋመስ ድረስ ፍፁም ሰላማዊ ነበር።

ድንገት እስክንድር ማብራሪያ ላይ በነበረበት ወቅት ሌባ! ዝም በል!! የሚሉ ጩኸቶች ተሰሙ ረባሾቹ ይዘውት ከነበሩት ፌስታል ውስጥ ባንዲራ አውጥተው ለበሱ።ወጣቶች መንገድ ዘግተው ወደ እስክንድር እንዳያልፉ ቢያደርጓቸውም በተደጋጋሚ እየተጋፉ ወደ እስክንድር ለመጠጋት ይሞክሩ ነበር።

ሁላችንም በቦታው የነበርን ሰዎች ቁጭ ብለውና ተረጋግተው ጥያቄ እንዲጠይቁ ብንነግራቸውም የተረፈን ስድብና ለመማታት ማስፈራራት ነበር።

ነገሩ እየጠነከረ ሲሄድ እስክንድር በሌላ በር ከክፍሉ እንዲወጣ ተደረገ የእርሱን ከክፍሉ መውጣት ተከትሎ ረብሸኞቹ ይዘውት የመጡትን ባንዲራ በየወንበሩ ወርውረው እየጮኹ ከህንፃው ወረዱ ።

አስገራሚው ነገር፦
እየተሳደቡና እየጮኹ ከህንፃው የወረዱት ወጣቶች በህንፃው በር ላይ የሰውና የመኪና መንገድ ዘግተው መግለጫ እየሰጡ ፖሊሶች ጥበቃ ያደርጉላቸው ነበር።

እስክንድር መግለጫ በሰጠባቸው ጊዜያት ሁሉ መጥተው የማያውቁ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ይህ ሊከሰት እንደሚችል ያወቁ ይመስል ግርር ብለው ከመገኘታቸው በላይ ረብሸኞቹ እየሰጡት የነበረውን መግለጫ ያስተባብሩ ነበር።

ይህ ሁሉ የሆነው በኛይቱ አዲስ አበባ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 100 ሜትር በማይርቅ ቦታ ነው።

ይኸው ነው!!!!

2 COMMENTS

  1. የአዲስ አበባ ነጻ አውጭ ግንባር (አአነግ) እንዳለው “አሁን ጊዜው አዲስ አበቤ ከተከተተበት አናሳ ጉድጉዋድዋ ውስጧ እንዳለ ሆኖም ቢሆን የሚወረወርበት አፈር እንዳያፍነው አፈሩን ወደተወረወረበት የመመለስ ስራ መስራት ያለበት ጊዜ ነው :: አዲስ አበቤ አፈሩን በጉድጉዋዱዋ ሳያስገባ መክቶ መልሶ አሳይቶ ማንነቱን የማስመስከር ስራ መስራቱን ማሳያው ጊዜው አሁን ነው::”

  2. እጅግ በጣም የወረደ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በትንሿ የስልጣን ጥም ባሳወራት የስክንድር ጭንቅላት የተሸረበች የከሸፈች ፖለቲካ ነች ታከለ እንዳንተ በስልጣን ጥም ሕሊናውን አላጣም ዛሬ ፎቶ አብሮ ተነስቶ ነገ ሂድ ስብሰባ በጥብጥ የሚለው!ጀዝ—

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.