ሲዳማ ስም የተደራጁ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ

የውሳኔ ህዝብ የሚካሄድበት ቀን የጊዜ ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት በሚቀጥሉት አምስት ቀናት ቀን ተቆርጦ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን በሲዳማ ስም የተደራጁ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ አሳሰቡ፡፡

በሲዳማ ክልልነት ጥያቄና በውሳኔ ህዝብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ይመክራል ባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎችና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ውይይት ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ የሲዳማ ዓርነት ንቅናቄ /ሲዓን/ ፣ የሲዳማ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሲብዴፓ/ የሲዳማ ሀዲቾ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ሲሀዴድ/ ናቸው፡፡ 

VOA Amharic

1 COMMENT

  1. የሰለጠነው ዓለም ጨረቃን ዳስሶ ከተመለሰ 50 አመት ሞላው። አሁን ደግሞ የዘመኑት ባለሃብቶች በክዋክብት መካከል ኑሯቸውን ለማድረግ እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ሃበሻው ጥርሱ አልቆ አኞ ሥጋ እንደተሰጠው አራዊት አፉ ያለውን ያን ለዘመናት እያኘከ ይገኛል። ችግራችን የክልል ፓለቲካ እና የተጣመመው ህገ መንግሥት ነው እያልን አሁንም የክልልና የዘር ፓለቲካ የሙጥኝ ማለት ሁሉንም ሰው አይነ ስውር እንደሚያደርግ የታወቀ ነው። የሰለጠነው ዓለም ድንበሩን ከፍቶ፤ ገንዘቡን አንድ አርጎ በሰላምና በጤና እየኖረ እኛ የበሬ ግንባር በምታክል የሰፈርተኞች መሬት ላይ ስንፋተግ እንገኛለን። የአማራነት፤ የኦሮሞነት፤ የሲዳማነት ወዘተ… መለኪያው ምንድን ነው? አብሮ መኖር አይደለምን? የሰው ውበቱና ጌጡ ያለውን የሚጋራለትና የሚያደንቅለፍት ሲኖረው አይደል? በመሰረቱ የክልል ፓለቲካ አፓርታይድ ነው። ያልመሰለውን ይገላል፤ ያባርራል፤ ይዘርፋል ለእኔ ብቻ ብሎ በዘር ቆጠራና በቋንቋ ዙሪያ በተሰመሩ ፈራሽ ህጎች የህዝብን ሰቆቃ ያባብሳል።
    በመሰረቱ የሃገሪቱ በሽታዎች ከትምህርት ተቋማት በ 50ዎቹ እና 60ዎቹ የወጡ የጠባብ ብሄርተኛ መሪዎች ናቸው። የሻቢያው አለቃ ኢሳይያስ አፈወርቂ በዛሬው አዲስ አበባ ዪንቭርስቲ በያኔው ቀ.ኃ. ዪንቨርስቲ ተማሪ የነበረ ሰው ነው። የወያኔው መሪም የዚሁ የትምህርት ተቋም ተማሪ እንደነበር ግልጽ ነው። የዘውድን አገዛዝ በመቃወምና የተሻለ እናመጣለን በማለት ከመንግሥት ጋር ልፊያ የጀመሩት እነርሱ ብቻ አልነበሩም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና የሰራተኛ ማህበራትም አብረው ተሰላፊዎች ነበሩ። ከዚያ ፍትጊያ የተረፈው ደርግ ብቅ ካለ በህዋላ ከውጭም ከውስጥም በመሰባሰብ በሃሳብና በጥይት ሲጠዛጠዙ ይህ ነው የማይባል የሰው ህይወት መቀጠፉ ለቋሚ ግልጽ ነው። ያ ዘመን ነበር ለሃገራቸው የሚያስቡ ሁሉ በጠለፋ ፓለቲካ በውስጥ አርበኞችና በየዋህ የደርግ እይታ አፈር የተመለሰባቸው። ጄ/አማን እና ተፈሪ ባንቲ ቀድመው በግፍ ከተገደሉት ናቸው። ታዲያ ይህን ሁሉ ምን አመጣው ይል ይሆናል አንባቢ። ጉዳዪ እንዲህ ነው። የዛሬው ችግራችን መሰረቱና ዛሬም ሃገሪቱን የሚያምሷት የዚህ የፓለቲካ እሰጣ ገባ ትራፊዎች ናቸው። የሻቢያ፤ የወያኔ፤ የኢህአፓ፤ የተለያዪ የኦሮሞን ህዝብ እንወክላለን የሚሉ በየክልሉ ነፍጥ ያነሱ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ሃገሪቱን የሚተራምሷት የቀድሞ የፓለቲካ ሸራቢዎችና በዛሬው የግርግር ፓለቲካ የግል አትራፊዎች ናቸው። የሲዳማም ሆነ የሌላው ክልል ተቀማሁ፤ ክልል ይበጅልኝ በማለት በማለት ቡራ ከረዮ መባባሉም ከዚሁ ከጠባብ ብሄርተኝነት የመነጨ የጎጠኝነት በሽታ ነው። መድሃኒትም የለውም። ሞት ብቻ ነው የሚገላግለው። እይታን አስፍቶ አለምን ማየት በዘር ተሰላፊዎች ዘንድ አይታሰብም። አንድ እንሁን ሲሏቸው የእኔ ድርሻ ምን ይሆን ብሎ ከሚጠይቅ ሰው ጋር አንድ ቤት መስራት አይቻልም። የአለም መሳለቂያ የሆነው ጥቁሩ ዓለም ራሱን አስከብሮና በሌሎችም ተከብሮ የሚኖርበት ጊዜ ይናፍቀኛል። ያ ግን አይታየኝም። የራሱን ቤት እሳት ለኩሶ የሌላውንም በማቀጣጠል የድረሱልኝ እኡታ ከማሰማት የተሻለ ምርጫ አይታየውም። የዚህ የክልል ፓለቲካም ዜይቤ ለማንም አይጠቅምም። ግን ከስር ይህ የፓለቲካ መስመር ጉልበት እንዲኖረው ሃገሪቱ እፎይ እንዳትል እሳትን በመለኮስ የሚያቀጣጥሉ የውስጥና የውጭ የህዝባችን ጠላቶች አንድ በመሆን እስካልመከትናችው ድረስ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሃገሪቱን ለማፈራረስና ህዝባችንን እንደ ሶሪያና ሶማሊያ ለማድረግ ጭራሽ አያንቀላፉም። ያኔ አንድም አትራፊ አይኖርም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.