የኤፈርት የባለቤትነት መብት ገና ኣልጠራም ? (አስገደ ገብረስላሴ)

የኤፈርት ኩባንያዎች የባለቤት መብት ቀደም ሲል የትግራይ ህዝብ ነው ይባል ነበር ።ቆዮት ብሉ የታጋዮች የጦርነት ኣካል ጉዳቶኞች ተባለ ። ጥያቄ ሲበዛቸው በጥቂት ማእከላይ ኮሚቴ ባለቤትነት በኣክስዮን ስም ተሰጥተው ።ኣሁንም ማጭበርበራቸው በመቀጠል ሁሉም ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው ሓላፍነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ተባሉ ። ኣንድ ጊዜ ደግሞ ለስብሀት ነጋ የኤፈርት ኩባንያዎች ባለቤትነታቸው የማን ነው ተብሎ ሲጠየቅ የህዋሓት ነው ብሎ ነበር ።ባለፈው ኣመትም የኢፈርት ኩባያዎች የትግራይ ህዝብ ናቸው ስለሆነ ከእንግዲህ በትግራይ ክልል ምክርበት የባለቤትነት ስም ሆነዋል ተባለ ። ይሁን እንጅ ካለፉት የነበሩ የኣጭበርባሪ ባለቤትነት ወደ ክልል ትግራይ ምክርቤት እንዴት ይሸጋገርሩ የሚል የተቀመጠ እና የርክክብ ህግና ደንብ ኣሳራር ኣልተቀመጠም ነበር ። በኣሁኑ የክልል ትግራይ ኣመታዊ ግምገማም የኤፈርት ኣጀንደ ተነስቶ የደረሱት ውሳኔ ኣሁንም የኤፈርት ኩባንያዎች በትግራይ ክልል ምክርቤት ባለቤትነ መሆኑ ተወስኗል ተባለ ።

የትግራይ ህዝብ ኣስተውለው የኤፈርት ኩባንያዎች ከተቋቋሙ 27 ኣመታት ኣስቆጥረዋል ። በስምህም ተነግዶባቸዋል ።እነዚህ ኩባንያዎች ቀደምሲል በስብሀት ነጋ ፣ኣባዲ ዞሞ፣ስዬ ኣብርሀ፣ በኣርከበ ዕቁባይ ፣ ሙሉጌታ ገብሪሂወት(ጫልቱ) ፣በኣባይ ጸሀዬ ፣ በርድና በሁሉም ማእከላይ ኮሚቴ ባለቤትነት ሆነው ኖረዋል ፣በመጨረሻም መለስ በበላይነት በኣዜብ መስፍን ፈላጭ ቆራጭነት ተይዘዋል ፣ኣሁንም የነስብሀት ፍጹም ታማኝ የሆነ ተድሮስ ሀጎስ እንደፈለገ እያደረገው ያለው ነው ።

እነዚህ ኩባንያዎች ከተመሰረቱ ጀምረው ከኣንዱ ባለቤትነት ወደ ሌላ ባለቤትነት ሲዛወሩ ኦዲት ተደርገው ሀላፊነት ባለበት ርክክብ ተደርጎው ኣያውቁም ።እጅጉን እሚገርመው ስማቸው ኣልጠቅሰውም በኣሁነ ጊዜ መቐለ ኣሉ እጅግ የታወቁ ከፍተኛ የኦዲት ሙያና ተመኩሮ ያላቸው 2 ከፍተኛ ኦዲቶሮች በኤፈርት የሁሉም ኩባንያዎች የውስጥ ኦዲቶሮች ሆነው ሲሰሩ እያሉ በዛ የኦዲተር ሀቀኛ ኣሳራር ተከትለው በሚሰሩበት ጊዜ ኣጭበርባሪ የሆነ የሸፍጥ እዲት ስሩ ተብለው ሙሁራዊ ህሊናቸው ሊቀበለው ባለመቻሉ ከነስብሀትና ፣ኣባዲ፣ ዞሞ ፣ኣርከበ ዕቑባ ፣ቴድሮስ ሓጎስ ባለመስማማታቸው ስራው ጥለውት ወጡ! ስለሆነ የኤፈርት ኩባንያዎች ባለቤቶች የህዋሓት ኣማራር በሙሉ ከጀምር እስከ ኣሁን የኤፈርት መነሻ ካፒታል ፣የ27 ኣመት ሙሉ ትረፍና ኪሳራ ለህዝብ ይፋ ኣድርገውት ኣያውቁም ።

የኣሁኑ በደኩተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራ የትግራይ ምክርቤትም የኤፈርት ኩባንያዎች ከዛሬ ጀምሮ የተግራይ ክል ምክርቤት ተረክቦዋቸዋል ሲለን በቅንነት ቢሆን ንሮ ኤፈርት በውጭና በውስጥ ኦዲቶሮች የተረጋገጠ የሀፍት ርክክብ ኣድርጎ መረከብ ሲገባው ፣ኣሁንም ለነዛ ካሁን በፊት ኤፈርትን እያጭበረበሩ ሲመዘብሩ የመጡ መሪዎች እንደ እንቁላል ጉዳቸውን ሸፍኖ ማለፍ ኣልበቃም ብሎት ኣሁንም ለ 7 ሚሊዮን የሚሆን የትግራይ ህዝብ በሚዲያ ኣውጆና ኣጭበርብሮ ማለፉ የትግራይ ምክር ቤት ገና ከጅምሩ ረጅም ሳይጓዝ ሲያጭበረብር ይታያል ።

የኤፈርት ኩባንያዎች የትግራይ ክልል ምክር ቤት ተረከባቸው ብሎ ህዝብ ሊቀበላቹህ ከሆነ ኤፈርት ከቦርድ ጀምሮ እስከታች ያለ የህወሓት ባለስልጣን በፖለቲካ ( የህዋሓት )ኣባልነት ታማኜነት ተገን ተደርጎ ምንም ሙያ የለለው የተሰገሰገው ጠራርጎ ኩባንያዎች ነጳ በሆኑ በሙያ የተካኑ ሙሁራኖች ተክቶ መዋቅሩም ጭምር ኦዲት ኣድርጎ ሲረከብ ብቻ ነው ።ካለበለዚያ በሸፍን ሸፍን የምታውጁት ግን ትርጉም ኣይሰጥም ።የትግራይ ህዝብ እንደሀነ ከእንግዲህ ወዲ ነቅቷል ለሆነ ኣጭበርባሪ መሪ ኣይቀበልም ።

በመሆኑም ኣሁን የኤፈርት ኩበንያዎች ከህወሓት መሪዎች ነጻ ኣልወጡም ።የትግራ ምክርቤት እኮ 100 % የህዋሓት ኣባላት ናቸው ።ኢፈርት እየመሩ ያሉም የህወሓት ኣባላትና መሪዎች ናቸው ።ስለሆነ በእኔ እምነት ትእም ወደ ህዝብ ባለቤትነት ተዛውረዋል ብለን ልንቀበላችሁ ከሆነ ከሁሉም ነጻ የሆኑ ስቢል ቡቁ ሙሁራን ይምሯቸው ! ! ምክርቤት ቁጥጥርን የፈርት ሁኔታ ለህዝብ ይፋ ማድረግ ብቻ መሆን ኣለበት ።
ከድሮ ጀምረው ኤፈርት ሲመሩ የነበሩ ኣሁንም ያሉ እኮ በፎቶዎ ያሉ ናቸው ።

3 COMMENTS

 1. እቶ አሰግድ ሀሳቡ ተነቧል የምትለው ለድፍን ትግሬ ለምን አልተሰጠንም ነው። እኔ ደግሞ የምለው ይህ የተጭበረበረ በደም የተገኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ወደ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ይመለስ ነው።
  ጠንቅቀህ እንደምታውቀው አንተም እንዳገለገልከው ህወአት ነጋዴ ድርጅት ሳይሆን ትግሬን እገነጥላለሁ ሻቢያ ጌታዬ ሲጠቃ ዝም ብዬ አላይም ብሎ በባንዳ ልጆች የበላይነት አገሩን ምስቅልቅሉን ያወጣ ድርጅት ነው። ይህን እንደ ብርታት አትውሰደው ነገ ከማንም ክልል በላይ እሳቱ የሚነደው አንተ በከለልከው አካባቢ ነው ኑረህ ለማየት እድሜ ከሰጠህ።

  ባጠቃላይ በወንጀል የተገኘ ሀብትና ንብረት ወደ ባለቤቱ ባለቤቱ ከጠፋ ደግሞ ወደ ማእከላዊ መንግስት ካዝና ይገባል እንጅ ለወንጀለኞች ተላልፎ ይሰጥ ብለው የሚጠይቁት ወንጀለኞቸና ግብረ አበሮቻቸው መሰሉኝ።

  ከዚህ አንጻር ንብረቱ ተላልፎ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሰጥ ጠንክረህ ታገል ካልሆነ ግን በማፊያ ሃላፊዎች መቀመጡ ከአንተ ሃሳብ በላይ የሚሆን አይመስላኝም።

  በተረፈ ቁማር አትጫወት ወይ ጥርት ያለ ኢትዮጵያዊ ወይ ጥርት ያለ ትግሬ ሁነህ የምትላቸውን ሰዎች ተደባለቃቸው አይንህ ካረፈበት ንብረት ትንሽ ያዘግኑሀል። ይገርማል ከዛ አካባቢ ሰው አጣን ማለት ነው?
  ታመህ ማን እንደደረሰልህ የምትዘነጋው አልመሰለኝም እኛው ነን።
  በተረፈ በቀሪው ዘመንህ ቀና ቀናውን ያስመልክትህ አዛውንቱንም ሀጢያታችሁን ተናዛችሁ በእጃችሁ ያለውን በደም የጨቀየ ሀብት ለድሀ ለግሱት በላቸው ይህን ስልህ አእምሮህ የሚስለው የትግሬ አካል ጉዳተኞችን ነው እኛ ግን እነሱን የምናየው እንደ አስካሪስ ኢትዮጵያ ላይ እንደተኮሱ ባንዳዎች ነው።
  በተረፈ በሌላ ትግሬ ተበደለ ትያትር እስክንገናኝ ደህና ሁን።

 2. አቶ አሰግድ ገ/ስላሴ ከልብ አከብረዎታለሁ አንዲት አስተያየት ብቻ ለመስጠት መጀመሪያ መልካም ፍቃደወትን እጠይቃለሁ ።የህውሀትን ሴራ በደንብ ጠንቅቀው ያውቃሉ እናም የኢፈርት ገንዘብ የብአዲንም እናም የሌሎችም ድርጅቶች በአንድ ተደምሮ ለኢትዩጵያ ህዝብ ቢሆን ይመረጣል ለምን ቢባል ለአንድነታችን ሲባል ።ገንዘቡ ቢቀርም ምንም አይደል ለአንድነታችን ስለሀገራችን ብናስብ ይሻላል ፍቅራችንን አመከኑት መፍትሄ ከእደናንተ አይነት ሰው ነው የምናስበው እባክዎትን ይቅር ተባብለን አንድ እንሁን እላለሁ

 3. Ato Asseged, have you ever asked where all that money comes from to build effort from scratch and do you realy know the depth of their financial dept these companies are in? Money in billions were taken from development bank of Ethiopia and other banks too, the money that should have been paid back to the financial institutions and as we all know it never came. So dear Ato Asseged how do you dear to claim that effort belongs to one ethnic group when in fact money that helps the companies thrive is laterally robbed by few Weyannes. Now when the rope is tighte around weyannes nack, suddenly effort is transferred to the region of Tigrai with out any kind of consultation with debtor’s in this case all Ethiopians.
  WHEN WILL THESE GUYS STOP PLAYING SMART ? INSTEAD ASK FOR FORGIVENESS AND JOIN THE MASSES AND THAT IS THE ONLY WAY OUT.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.