የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ በጀኔራል አሳምነው ጽጌ ላይ እየሰራው ያለው ነውረኛ ድራማ ቀጥሏል . .(አቻምየለህ ታምሩ)

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ከነትንሽነቱ የፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ አገዛዝ ታናሽ ወንድም ነው። ፋሽስት ወያኔ በሥልጣን ዘመኑ በሐሳብ የተለዩትን ግለሰቦች ሁሉ እግር በእግር እየተከታተለ ካላሳደደ፣ ካላሰቃዬና ስብዕናቸውን ካላዋረደ ፖለቲካ የሰራና ቁሞ የሚሄድ አይመስለውም ነበር።

የፋሽስት ወያኔ አረመኔነት እግር አውጥቶ ሲሄድ ከታየባቸው ጭካኔዎች አንዱ በብርቱካን ሜዴቅሳ ላይ የሰራው ግፍ ነው። ፋሽስት ወያኔ ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳን አስሮ ቅስሟን ለመስበር፣ አንገቷን ለማስደፋትና ራሷን በራሷ እንድታዋርድ ለማድረግ ያልሰራው የቴሌቭዥን ድራማ አልነበረም። ፋሽስት ወያኔ ብርቱካንን በጨለማ ቤት አስሮ በማሰቃየት ራሷን በራሷ እንታዋርድና ጥፋተኛ ነኝ እንድትል አድርጎ ሞራሏን ለመስበር ቢሞክርም የአረመኔ ክብረ ወሰን መስበሩን ከማሳየቱ በስትቀር ሕዝብ በብርቱካን ላይ ባለው አመለካከት ያደረሰው አንዳች ጉዳት አልነበረም።

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝም ከፋሽስት ወያኔ የቀሰመውን የጭካኔና የነውረኛነት ትምህርቱን ተጠቅሞ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ለማዋረድና ለማሳነስ የግል ጉዳዩን፣ ከሱና ከባለቤቱ በስተቀር መንግሥት ነኝ የሚለውን ክፍል ጨምሮ ማናቸውም አካል ሊይዘው የማይገባውን የጋብቻ ሰርቲፊኬቱን በቴሌቨ ዥን አቅርቦ ተፈረገ የተባለው መፈንቅለ መንግሥት ኢግዚቢት መሆኑን ነገረን። እንዲህ አይነት የተጨማለቀ የነውረኛነት ጥግ በፋሽስት ወያኔ ዘመን እንኳ መደረጉትን እጠራጠራለሁ። የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ የጋብቻ ሰርቲፊኬትን የመፈንቅለ መንግሥት ኢግዚቢት አድርጎ ያቀረበ የመጀመሪያው ነውር የማያውቁ ማጅራት መቺዎች አገዛዝ መሆን አለበት።

እነ ዐቢይ የጀኔራሉን የጋብቻ ሰርቲፊኬት በቴሌቭዥን ያሳዩን የአፓርታይድ አገዛዙ አክቲቪስቶች ላለፉት ሁለት ሳምንታት «በጋብቻ ላይ ጋብቻ ፈጽሟል» እያሉ በአሳምነው ላይ ሲቀቡት የነበረው ጥላሸት እውነትነት መሆኑን ለማሳየት ይመስላል። ሆኖም ግን አሳምነው በአንድ ጊዜ ሁለት የትዳር ሰርቲፊኬት ቢኖረው እንኳ የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ለሚጋቡ ጥንዶች የጋብቻ ሰርቲፊኬት የሚሰው ጥንዶቹ ያላገቡት መሆናቸውን የሚያሳይ መሸኛ ሳያቀርቡ መሆኑንና የዐቢይ ቢሮክራሲ የተሞላው የጋብቻ ሰርቲፊኬትን ያህል ትንሽ ነገር እንኳ ለማንና ምን ቅድመ ሁኔታ ላሟሉ ጥንዶች እንደሚሰጥ በማያውቁ ሞሮኖች [morons] መሆኑን ብቻ ነው የሚያሳየው።

የሆነው ሆኖ ፋሽስት ወያኔ ብርቱካንን ለማዋረድ የሰራው የጭካኔ ድራማ ብርቱካን በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የበለጠ ጀግና ሆና እንድትታይ እንዳደረጋት ሁሉ የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝም ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ለማዋረድ እያሰራው ያለው አስነዋሪ ድራማም ዐቢይ አሕመድ የፋሽስት ወያኔ የጭካኔ አገዛዝ ወራሽና ዲቃላ መሆኑን ከማሳየቱ በስተቀር ጀኔራል አሳምነው ጽጌን የበለጠ ጀግና ያደርገው እንደሆን እንጂ የሚቀንስበት አንዳች ነገር የለም።

5 COMMENTS

 1. አቶ አቻም-የለህ፦ከዘር ማንዘርህ ሲተላለፍ ቆይቶ አሁን በአንተ ላይ ይፋ የወጣው የሰይጣን ልጅነትህ አማካይነት ፦፩/ዘረኛ አማራነትህን ወደህ ኢትዮጵያን በመጥላትህ፣፪/ሕሊናህ ሕቡዕ ሆኖብህ አእምሮህና ልቦናህን በእርኩስ መንፈስ እንዲመራ ፈቅደሀል፣፫/የእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነውና አንተና ፀረ-ኢትዮጵያ ዘር-ማንዘርህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእርግጠኝነት ትከፍላላችሁ።

 2. Achamyele Tamiru is unscrupulous and mindless pig with human form. He is already out of touch and crackbrained. We will see what will be happening to him in the near future. 

  This ugly guy, Ermias Legesse (the chameleon), the stupid Habtamu Ayalew, the rude and crooked Reyot Alemu and the debtraist Menalachew are the worst human being that I have ever seen. Ermias Legesse is a chameleon who changes his face from time to time. He lives only for his belly. He used to serve the TPLF as a member of OPDO with passion. He was one of the faithful servants of the TPLF.  Since he left the club of the TPLF he has been collecting his daily breads from the Ethiopians around DC. This guy can even sell his souls. Now, such poor individuals without integrity are dreaming that they may influence the Ethiopian politics with their poor psychological war against the Oromo people. This shows how they are desperate und hopeless.

 3. አቻምየለህ እና መሰሎቹ ከየት ይሆን የተፈለፈሉት?
  ኢትዮጵያ ውስጥ የአፓርታይድ አገዛዝ አለ ማለቱ የሚያስረዳን አፓርታይድ ምን እንደ ሆነ እንደማያውቅ ነው!
  “አፓርታይድ”ን 10 ጊዜ ደጋግሞታል።
  “ፋሽስት” ን 9 ጊዜ።
  በሁለት ዐረፍተ ነገር ውስጥ “ፋሽስት” እና “አፓርታይድ” ብቻ ከተጠቀመ፣ አሳቡን በስፋት መግለጥ ያዳግተዋል ማለት ነው።
  “እንዲህ አይነት የተጨማለቀ የነውረኛነት ጥግ በፋሽስት ወያኔ ዘመን እንኳ መደረጉን እጠራጠራለሁ” በማለቱ
  የህወሓት ደጋፊነቱን ባቋራጭ አስታውቆናል!
  ሳተናው ላይ አቻምየለህ፣ ሰርፀ፣ ወዘተ የሚጽፉትን ከቁምነገር መቁጠር ጊዜ ማጥፋት ነው።
  ሥራ ፈትቶች ስለሆኑ ውሎአቸው ስም ማጥፋት፣ ጥላቻ መዝራት፣ ድንቁርና ማስፋፋት ነው።
  ደግነቱ ሰው ንቁ ነው።

 4. በኦሆዲድ የሚመራው የጸረ ኢትዮጲያው የኦነግን አላማ የሚያስፈጽመው የአብይ አህመድ መንግስት ከወያኔ በባሰ ፍጥነት ዘረኛ አሰራሩን የሚቃውሙትን ለማጥፋት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም:: በማህበራዊ ሚዲያ አማርኛውን የሚረዱ በአማርኛው መጠቅም የማይፈልጉ ሰሞኑን የእስክንድርን ጋዘጣዊ መግለጫ ከረበሸው የታከለ ገገማ ጀሌ ጀምሮ ጀምሮ እዚህም ‘መነን’ በማለት በሜኒሶታም ያኔ አምርኛውን ዝግጅት የከለከሉ ሁሉ የአማርኛ ጠበብት ሆኑልን:: የረገጡትን የኢትዮጲያ ባንዲራ ያዙልን አጃኢብ ::በሃስት ድራማ ደግሞ ዋና ደራሲው በእርካብ የጀመረውን በስፋት በመቀጠል ላይ ሲሆን ሁነኛ ገዥ ግን አላገኝም አያገኝምም:: የሃገራችን ጉዳይ ግድ የሚለን ግን ባለተረኞቹ ጋር እንካሰላምታ ትተን በህዝባችን ላይ የቀጠለውን በደል መቃወም ማውገዝ ይኖርበናል::ባለፈው በጌዲኦ ወገኖቻችን ላይ ሚልዮን የሚጠጋ ህዝብ በኦነግ ቀጥታ ጣልቃ ገብነት ሲፈናቀል የአብይ አህመድ መንግስት ችላ ብሎ ነጻው ፕሬስ ማጋለጡ ይታወሳል:: ሰሞኑን ደግሞ በአጣዬ መደበቁ በአባ ገዳ ሰንበቶ(DW German Radio) የተመሰከረው የኦነግ ገዳይ ጦርን ለመመከት ጄነራል አሳምነው ያደረገው በሁሉ ክልል ያሚካሄድ የልዩ ሃይል መዋቅረን በአማራ ክልል የማፍረስ ጣልቃ ገብነት ሲመክት ተሰዋ::ይህን አሳምነው ከማድረጉ በፊት አብይ አህመድ “አደገኛው የአማራ ብሄረተኝነት” በማለት ያደረገው ክፉ ቅስቀሳ በህግ የሚያስጠይቀው ሲሆን ሰላማዊ የብእር ታጋዩን እስክንደርን ለአዲስ አበባ የራስን ማስተዳደር መብት በመታገሉ በጦርነት መክሰሱ ጀሌዎቹ በቦሌ ክፍለከተማ የመታወቂያ ካርድ ባህሰት ለኦሮሞ ክልል ተወላጆች የሰጡትን ያጋለጠችውን ሴት ያስፈራሩ የእስክንደርን ጋዜጣዊ መግለጫ መረበሻቸው ታይቷል::የቦሌውን ደባ ያጋለጠች የታከለ ኩማ ጀሌዎች መሰረቅ ስታጋልጥ ዛቻ ያቀረቡባትን መስክራለች::
  የሃገር ወዳዶች ዝምታ ይሰበርና ሃገራችንን በሚቻለን ሁሉ እንታደግ::ከዚህ በተጨማሪም የወቅቱን ግፍ የሚያጋልጡ ጋዜጠኞች የመንግስታዊ ጭምር የህግ ባለሙያዎች በመታሰር በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን አምንስቲ ኢንተርናሽናልና የጋዜጠኞች መብት አሰካብሪው ሲፒ ጄ ዘግበዋል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.