የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትር (መልካም ውጤቶች እንዳሉ ሆነው)ፓርቲዎትን በመርህ፥ ክልሎችን በአንዲት ኢትዮጵያ ጥላ ስር አድርገው እየመሩ ነው ለማለት አንደፍርም

 ክልሎችን የሚመሩ የፓርቲዎ (ኢህአዴግ) ብዙሃን መሪዎች ህዝባችንን ሊያቀራርቡና የመከፋፍል ግንብ ሊያፈርሱ ቀርቶ በጦርነት ላይ ያሉ ጎረቤታማ ሀገራትን የሚመሩ የውሸት ህዝበኛ፣ ስልጣን ዋሻው ሌቦች ሆነዋል።

በክልል መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ የድርጅትዎ አመራሮችም ይሁኑ የየክልሎች የህዝብ እንደራሴዎች የየክልላቸውን ህዝብ መሰረታዊ የልማት ጥያቄን በማረጋግጥና ዘመኑን የሚመጥን አመራር ከመስጠት አልፈው ጎረቤታማ ህዝባቸውና የግንባር ጓድ ድርጅቶች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋሪ መንገድ ጣትን ሲቀስሩ መዋል ግብራቸው ከሆነ ሰነባብቷል። እስካሁን በዲሞክራሲ ማእከላዊነት ሃገሪቱን ካጠፋት በላይ አሁን በግንባሮችና ክልሎች ፍጹም ነጻነት ይባስ ኢትዮልያን እንዳይበትናት እንሰጋለን።


26 አመታት ሙሉ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ብብት ተወሽቆ ሲያጠፋ ኖሮ ኋላም የትግራይን ህዝብ ከቀሪው ጦቢያ ወንድም እህት እህዝብ ልቡን እንዳሸሸው ሁሉ እርሰዎም ኮሽ ባለ ጊዜ ነገሮችን ለማርገብ በብሄርዎ ቆዳ የሚ’ጠቀለሉትና የሚጠቀልሉት አካሄድ ሃገርን ይባስ ይሰነጣጥቃል እንጂ ከቶ አንድ አያደርግም!!

አምናለሁ፥ ለአሁኗ ምስቅልቅል ኢትዮጵያ መሪዎች ብሄርን ያማከለ ህዝባዊ መሰረት ያስፈልጋቸዋል። ይሁን እንጂ ሂደት አልባ፣ ነግቶ መሽቶ መነሻውና መድረሻው ብሄር የሆነ የፖለቲካ ውግንና ልዩነቱ የጊዜ ርዝማኔ እንጂ መጨረሻው የመጀመሪያው የህወሓት መንገድ ነው። እርሰዎ የሚፈልጓትንና የሚያዎሩላትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር በብሄር አይን ብቻና ብቻ የታጠሩ የድርጅትዎ ልጥፍ አመራሮች ከአፍቅሮተ-ክልልና ብሄር ወጥተው የምንናፍቃትን ኢትዮጵያን ከቶ አይገነቡም።

በመሆኑም፥
1) የድርጅትዎን ክልላዊ መግለጫዎች ይመልከቱና መንገድዎን ይገምግሙ!! ድርጅትን ከድርጅት፣ ህዝብን ከህዝብ፣ ህዝብን ከድርጅት የሚያላትሙና መተማመንን የሚያርቁ “የመጡብህ” ልፍለፋ እንዲቆም የየድርጅትዎን ምክርቤቶች ይማጸኑ። እስከሚገባኝ ድረስ ህዝባችን ጥያቄው ፍትህና እኩልነት፥ ሰላምና ብልጽግና ነው። እነዚህን ጥያቄዎች መሰረት አድርጎ የሚታገልና አንድ ትልቅ ሃገር የመገንባት ትልም ያለው ክልላዊ ድርጅታዊ አመራር ይኑራችሁ። የድርጅተዎን አመራሮች አጉል አፍቅሮተ-ብሄር ልጓም ያብጁለት!

2) በፌደራሉ መንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮች ከክልል አመራሮች በእውቀት፣ አመለካከትና ክህሎት መሳለመሳ የሚቆሙ ወይንም የሚልቁ እንዲሆኑ ተግተው ይስሩ! ልጆቻችን የሚሰሩትን አይነት ድራማ የሚሰሩ፣ በትልቅ ትከሻቸው “ሙጫ ጭንቅላት” የተሸከሙ አጓጉሎችን መንግለው ይጣሉ። ይሄንንም ለማድረግ የድርጅተዎን ካድሬ ማሰልጠኛ ተቋማት የቆየ ጭቅቅታቸውን አራግፈው እውነተኛ የአመራሮች አቅም መፍጠሪያ እንዲሆን ዛሬ ነገ ሳይሉ ስራ ይጀምሩበት። የአመራር ማሰልጠኛ ተቋምዎን ሃገር ሃገር፣ ህዝብ ህዝብ የሚሸት ስልጡን ማእከል እንዲሆን በጎ ሰዎችን በውስጡ ያጭቁበት።
—-
የወደቀውን ኢትዮጵያዊነት በወደቀው የህወሓት መንገድ ሊያነሱት አይታክቱ!! የዛሬን ችግሮች በትናንት የስህተት መንገዶች ሊያርሙ ወደ ኋላ አያማትሩ!!

የበለጸገችና ፍትህ የሰፈነባትን ሃገር መገንባት ፍዳው አያል ነው።

ያሲን አህመድ አሊ

1 COMMENT

 1. Abiy Ahmad is a little dictator who wants to be everything and every where .
  when he is having a meeting with doctors, he pretends to be knowing about medicine and health more than the professionals do.
  He calls up teachers to a meeting and he puts himself as a teacher of extra ordinary talent and lectures them about their work.
  When he is with lawyers he pretends there is no one expert in law as he is and tries to humiliate the people he has invited to a meeting.
  When he is with businessmen he lectures to them about how to run a business as if he is the only expert on business management. Etc etc
  That is what a dictator is
  etc.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.