ፕሮፊሰር ጫት ወደ መቀሌ ጎራ ብሎ ፣ መርቅኖ፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀ መድረክ ይችን ብሏል

“ከእንግዲህ በኋላ ወደ አሃዳዊነት ልንመለስ አንችልም። አሁን ያሉት ክልላዊ መንግስታት ሀገር ለመሆን አንድ ነገር ብቻ ነው የሚቀራቸው። የውጭ ሀገራት እውቅና። እጨፈልቃለሁ ብትል ሀገር እንዲሆኑ ፈቀድክ ማለት ነው።”

አንደኛ – አሃዳዊ አስተዳደር ይኖር ብሎ፣ ብዙም እየተከራከረ ያለ ሰው ያለ አይመስለኝም። አብዛኛው ማሀበረሰብ፣ እኔንም ጨምሮ፣ ፊዴራላዊ ስርዓት ጠቃሚ ነው ብለን ነው የምናምነው። የቀድሞዎቹ ቅንጅት፣ አንድነት፣ ሰማያዊና ኢዴፓ ..በፕሮግራሞቻቸውን በፌዴራል ስርአት እንደሚያምኑ አስቀምጠው ነበር። አሁንም መኢአድና ኢዜማም እንደዚሁ። አሃዳዊ ስርዓትን እያቀነቀነ ያለ ቡድን ወይንም ድርጅት በሌለበት፣ ይሄ ጽንፈኛ የኦሮሞ ልሂቅ ነኝ ባይ፣ ከየት አምጥቶ ስለ አሃዳዊ ስርዓት እንደሚያወራ ሊገባኝ አልቻለም።

ሁለተኛ – ድርጅቶች አሃዳዊ ስርዓት ያስፈለጋል ብለው አምነው በዚያ ዙሪያ መንቀሳቀስ ፈለጉ ብንል እንኳን፣ ያንን የማድረግ መብት አላቸው። ከፌዴራል ስርዓት አሃዳዊ ስርዓት ያስፈለጋል ብለው ህዝብን ካሳመኑና ህዝብ ከደገፈቸው ፣ አሃዳዊ ስርዓት የማይተገበረበት ምክንያት የለም። አሃዳዊ ስርዓት ያላቸው ግን ዴሞክራቲክ የሆኑ ብዙ አገራት አሉ። ፈርንሳይን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ዋናው የሕዝብ ፍላጎት ነው። በኔ እምነት አሃዳዊ ስርዓት ብዙ የሕዝብ ድጋፍ አለው ብዬ አላስብም። ስለዚህ የፕሮፌሰር ሕዝቄል ጋቢሳ ማስፈራራት መሰረት የለሽ ነው።

ሶስተኛ – አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እየተቃወመ ያለው ፌዴራሊዝምን ሳይሆን አሁን ያለውን የጎሳና የዘር ፌዴራሊዝምን ነው። የደቡብ ክልል አሁን ባለበት መቀጠል የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል ብዬ አላስብም። የኦሮሞያና የአማራ ክልል ፈረሰው አነስ ያሉ ለአስተዳደር አመች የሆኑ ፌዴራል መስተዳድሮች መመስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.