የአዴፓ መግለጫና የሕዝቡ ሥሜት! እንዳንሳሳት! (ሰርፀ ደስታ)

የዛሬው የአዴፓ መግለጫ ብዙዎችን ጮቤ ሲያስጨፍር ታዝቢያሁ፡፡ እንዲህ በግልጽ አቋም መያዙ ጥሩ እንደሆነ እውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን የዚያን ያህል የሚያስጨፍር ነገር አላየሁም፡፡ ይቺ በትንሽ ነገር በከፈተኛ ደረጃ መጋል ብዙ መዘዝ አምጥታብናለች፡፡ አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ የነበረውን ሥሜት አስታውሱ፡፡ ለነገሮች አጫፋሪ መሆን ልክ አደለም፡፡ ይሄን አይነት ማጫፈሪያ እየሰጡን  እኛ ስንዘናጋ እነሱ በተራ ራሳቸውን እያደላደሉ ይሄው ዛሬ አዴፓ ወረደበት የተባለው ቡድን በፈጠረልን ሥርዓት መቀጠላችንን አትርሱ፡፡ ሕገ-መንግስት፣ ሰንደቅ ዓላማ፣ በብሔር የተከፋፈለች፣ ጸረ-ሽብር፣ ጸረ-ሕዝብ ሕጎች ሁሉ እንዳሉ አሉ፡፡ ዛሬ ባለተራው ኦፒዲ/ኦነግ እነዚህን ሕጎች ሲጠቀምባቸው አስተውሉ፡፡ ሌላ ቀርቶ ሴራና ቁማሩ ሁሉ ከወያኔ የተወረሰ መሆኑን አስተውሉ፡፡ እንደውም አሁን የምናየው ከዛም በከፋ እንደሆነ አስተውሉ፡፡

መግደል መሸነፍ ነው ያለው ሰውዬ ገዳዮችን ቀጥሮ በየቦታው እንዳሰማራ አስተውሉ፡፡ በትግሬ ጭፍን ደጋፊዎች ታጅቦ የነበረው ወያኔ ዛሬ በኦሮሞ ጭፍን እንዴት እየተደገፍ ያለበትን ሁኔታ አስተውሉ፡፡ እንደወረደ ከወያኔ የተወረሰ ብቻም ሳይሆን ወያኔ የረሳቻቸውን ሁሉ እየሆነ እንደሆነ እዩ፡፡

አዴፓ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡ መልካም! ግን በመፈንቅለ መንግስት ሥም የተደረገችዋን ሴራ ግን ትንፍሽ አላለንም፡፡ አሳምነው ፈጸመው ተብሎ ለዛ ሁሉ ጥፋት የዳረገው ሴራ ከአብይና ቡድኑ እንዳለበት ከጊዜ ወደጊዜ የምናያቸው መረጃዎች ጠቋሚዎች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ራሳቸው ያቀናበሩት የሐሰት መረጃ ራሳቸውን እያጋለጠ መጥቷል፡፡ እነሱ መፈንቅለ መንግስት ያሉትን በዋናነት አሳምነው ነው የፈጸመው እያሉ ዋና የሴራው ተባባሪ ዛሬ መግለጫ  አወጣ የተባለለት የአዴፓ አባላት እንደሆኑ ልንዘናጋ አይገባም፡፡ አሁንም በየቦታው ንፁሀንን በማሰርና በማሰቃየት ላይ ናቸው፡፡ ወሮበላ አገር ሊመራ አይችልም፡፡ የምናው ሁሉ የወሮበሎች ሥራ እንደሆነ እያየን በትናንሽ ነገሮች ራሻችንን ባናስፈነድቅ ጥሩ ነው፡፡ አዴፓ ውስጥ ቆራጥ አቋም የያዙ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ሰሞኑን በመፈንቅለ መንግስት ሥም ታላላቅ ሰዎቻችንን ያጣንበት ሴራ ውስጥ ዋና ተዋናዮች እንዳሉበት በአይናችን አይተናል፡፡ አሳምነው ነው የገደለው ለማለት አሳምነውን በተመሳሳይ 11 ሰዓት ላይ አንዱ ገስት ሀውስ ሌላው ከፎቅ ሥር ሆኖ ግደለው እያለ ሲያዝ ሌላው ድምጹን ቀርጬ ይዤ ነበር በማለት በሳምንት ጊዜ ውስጥ ቻይና ተኬዶ የተቀነባበረን ድምጽ ምስክር ሲሆን አይተናል፡፡ ከዛማ እውነትን ተንኮለኞችና ክፉዎች የቱንምያህል ቢጋፏት በራሳቸው እጅ እየወጣ ባለ እነሱ መረጃ በሚሉት እያሳበቀችባቸው ነች፡፡ አሳምነው ብዙ ቤት አለው ይሉናል፡፡ አሳምነው ይሄ የተባለው ሁሉ ቢኖረው እንኳን እነ አብይ አሜሪካ ድረስ ልጆቹንና ሚስቱን ያስቀመጠው እንዴት ነበር? አገር ቤት ያለውን ንብረት እርሱት፡፡ ለነገሩ ስለማያፍሩና እንዲህ በቀላሉ በስሜት ስለምንነዳላቸው የማይታወቁ ይመስላቸው ይሆናል፡፡ ይሄ የመንደር ዱርዬ ሰብስቦ ለሽብር የላከው የአዲስ አበባን ከንትና ነኝ የሚለው ሰውዬ ስንት ቤት ይኖረው ይሆን? ያሳምነው ኮንደሚኒየም አስቂኝ ናት፡፡ አብዛኞቹ ሕንጻ ያላቸው ናቸው፡፡ አትቀልዱ፡፡

ስለሆነም አዴፓም ሆንክ ሌላው ከዚህ በኋላ በምንም መልኩ በማስመሰል ልታልፉት የምትችሉት ነገር የለም፡፡ አዴፓ እንደመግለጫው እሆናለሁ ከአለ በተግባር ያሳየን፡፡ በግፍ የአብይ ቡድን እያሰራቸው ያሉትን ዜጎች የተራ ውንብድናና ኢትዮጵያ ውስጥ ራሱ ያሰማራቸውን የሰለጠኑ ገዳዮችን ገዳዮች ሰልጥነው ትልከውብናል እያለ የሚያምታታውን ሰውዬ፣ ሌሎች ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ፈር በማስያዝ ያሳየን፡፡ ፖሊሲን የተመረኮዘ ለውጥ እንጂ የማንንም ድንፋታና ቀረረቶ በመስማት ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ማጥፋት አይገባም፡፡ በቅኝ ገዥዎች ለባንዳዎች በተላለፈ የአማራ ጠል ፖለቲካ 50 ዓመት ተጉዘናል፡፡ ዛሬ ሁሉም ምንና ማን እንደሆነ እያየን ነው፡፡ ያጣናቸውን ትልልቅ ሰዎች ቢያሳዝነንም ክስተቱ ብዙ ነገር እንድንታዘብ አድርጎናል፡፡ አማራ ጠል የፖለቲካ ስትራቴጂ ከጌቶቻቸው የወረሱት ባንዳዎችና የባሪያ አስተሳሰብ ያላቸው ወርጆች የት ድረስ እንደሄዱ ታዝበናል፡፡ ለዚህ ዋና ተባባሪያቸው ደግሞ አማራ ነን የሚሉ ከሂሊና የጎደሉ ሆዳሞች እንደሆኑ ታዝበናል፡፡ ስለ አገርና ሕዝብ ባለው ፍቅር በአማራ እየተደገፉ እድል ያገኙ ሁሉ እንደ ጦር የሚፈሩት አማራን ሳያንሰራራ ማጥቃት በሚል መርህ ነው እየተጋገዙ ያሉት፡፡ አብይን ዛሬ ያለበት ቦታ አረጋግቶ ያስቀመጠው ዛሬ ገዳዮችንና ወሮበሎችን አሰማርቶ የሚያጠቃው አማራ እንጂ ኦሮሞ አልነበረም፡፡ ኦሮሞማ አብይ እንዴት ኢትዮጵያ ኢትጵያ ይላል ብሎ ዋና ተቃዋሚው ነበር፡፡ 50 ዓመት በአማራ ጠል አስተሳሰብ ባርነት ሥር ያደረጉት ትውልድ ዛሬ ደስታው የአማራ መጎዳት እንጂ ከባርነት መውጣት አደለም፡፡ ይሄን ልናስተባብለው አይገባም፡፡ ስለዚህ በማይረቡ ነገሮች ጮቤ እየረገጥን መዘናጋት የለብንም፡፡ ኢትዮጵያ የምታስፈልገው ለአማራ ብቻ ከሆነ ሁሉም ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖረው ጊዜ ሲመጣ ዋጋውን ያገኛል፡፡ የአማራ ጠላት የሆነበት ዋና ምክነያት አማራ እያለ ኢትዮጵያን መዳፈር አይቻልም ተብሎ በኮሎኒያሊስቶች የተነገራቸው ትርክት ሲሆን ዛሬ ባንዳዎች እያደረጉ ያሉት የኮሎኒያሊስቶችን ምክር ነው፡፡ አማራን እንደሕዝብ ጠላት በማድረግ ላይ የተመሰረተ አስተሳሰባቸውን ከማሰራጨታቸውምሌላ ለኢትዮጵያ ታላላቅ ሥራን የሰሩና እንደ ምልክት የምናያቸውንም ምልክቶቻችንን ጀግኖች አባቶቻችንን ታሪክ እንዲሁ እንዲጠላ ነው፡፡ እርግጥም ኢትዮጵያ የእነዚህ አባቶች ልዕልና ከተነገረባት በወኔ የተሞላ አገሩን ወዳድ ትውልድ ስለሚቀርላት ማንም ወሮበላ እንደፈለገው ለመሆን አይችምና፡፡ ከእነዚህ ታላላቅ አባቶችም መካከል ታላቁ ጎበና ዳጬ አንዱ ሲሆን ዛሬ የወራዶች ባሪያ የሆነው ትውልድ የጎበና ሥምማስፈራሪያ ሆኖታል፡፡ እርግጥ ነው ዛሬም ጎበና ያስበረግጋቸዋል፡፡ የጀግና መንፈስ ነውና፡፡

ስለዝህ ይቺን የጊዜዊ ስልት ልትሆን የምትችልን ሞቅታ የተሞላባት መግለጫን ከመቀበላችን በፊት መሠረታዊ እርምጃዎችን እንፈልጋለን፡፡ ተረኛው የባንዳ አስተሳሰብ አስቀጣዩ ቡድን ስርዓት እንዲይዝ፣ የታሰሩ ንጹኀን ዜጎች  እንዲለቀቁ ይቺ መፈንቅለ መንግስት የተባለች ሴራ ጥርት ብላ እንድትወጣና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀረቡ፡፡ ከዚህ ውጭ መግለጫው የሕዝብን ትኩረት ለማስቀየርም ሊሆን ይችላል፡፡ መጀመሪያ ይቺ አንድ ምስክር ያጣች  ከላይ ባለቤቷ ብቻ የቆመላትን እውነትን እመኑ! ምን ብታቀነባብሩት ምን ገንዘብ ብታፈሱበት የሰውን አእምሮ የሚያዘው ኃያሉ አምላክ እያለ አትችሉም! በያንዳንዷ መረጃ በምትሏት ማንነታችሁን ከማጋለጣችሁ በቀር፡፡ ይሄው ለማስመሰል መግደል መሸነፍ ነው ያለው ዛሬ ይት ጋር እንደሆነ እያየን ነው፡፡ አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የለንም ያለው ሰውዬ ዛሬ እንዴት እኔ የምዋሸውን ውሸት ታጋልጣላችሁ በሚል እያሰረ ነው፡፡ ይህ ብቻም አይበቃም በየቦታው ተራ የውንብድና ሥራ የሚፈጽሙለትን ሳይቀር አሰማርቶ እናየዋለን፡፡ በድጋፍና በሆያሆየ መላዕክ ነኝ ለማለት የቃጣው እውነተኛ የሰው ማንነት የሚገለጥበት ቦታ ሲደርስ ማን እንደሆነ እያየን ነው፡፡ ሕዝቤ ሆይ በተራ ዲስኩር አትፈንድቅ፡፡ 50 ዓመት የደለበ ሴራ ነው እየቆመረብህ ያለው፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮፕያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

3 COMMENTS

  1. አቶ ሰርፀ ይህ የእርስዎ አስተያየት ለእኔ የቀኑ ምርጥ ሃሳብ ብየዋለሁ፡፡ እነዚህ የአጋንንት ስብስቦች ኢህአዴግ ማለቴ ነው ምንም አይነት ሞራልም ሆነ ፍርሃ እግዝአብሄር የሌላቸው ምን አልባትም ተንኮላቸው ከሳጥናኤል ቢበልጥ እንጂ የማያንስ ነው፡፡ እኔ እንደ እርስዎ የአዴፓ መግለጫ የድራማው አንዱ ተውኔት ነው፡፡ እንግዲህ ምንአልባት ወያኔ ያን የመሰለ መግለጫ በመጃመሪያ እንድትሰጥና ሰዎች የንዴት መንፈስ እንዴፈጠርባቸው በማድረግ አዴፓ ደግሞ ልክ ዘራፍ በሎ ለዚያ እውነተኛ የሚመስልና ህዝቡ የሚያስበውን መግለጫ በመስጠት በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም ደግሞ የአማራን ህዝብ እንቅለፍ ውስጥ እንዲቆይ ማድረግ ነው፡፡ አዴፓ በሚባለው አህያና ቱልቱላ ድርጅት በሚታዳደረው ክልል ውስጥ እየሆነ ያለው በተቃራኒው ምርጥ ምርጥ የነቁ የአማራ ልጆችን እየለቀሙ በገፍ በማሰር ላይ ይገኛሉ፡፡ ለጊዜው የተሳካላቸው ይመስላቸው ይሆናል፡፡ መጨረሻው ግን ምናልባትም ኢህአዴግ የሚባለው የአጋንንትና የመርገመት ስብስብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከዚች ሀገር እንደጎርፍ ተጠራረጎ ይሄዳል፤ ታሪክም ይሆናል፡፡

  2. “እየፈጩ ጥሬ”የሆነው የሀገራችን ፖለቲካ አሁን አሁንስ እጅ እጅ እያለኝ ነው። እግዜሩም ጨከነ፤ ሰውም ለይቶለት ሠየጠነ። ግራ አጋቢ ሁኔታ ተፈጥሮ ግራ ተጋባን። ለማንኛውም የሠርፀ ትንተና ግሩም ነው፤ልብ መባል አለበት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.