የሰሞኑ የአዴፓ መግለጫ በኦዴፓ ዘንድ “የፅንፈኞች ተፅዕኖ ያረፈበት ነው፣ አክቲቪስቶቹን ለማስደሰት ነው…” እየተባለ ነው።

የኦሮሞ ፅንፈኞች መግለጫውን በመቃወም የመጀመርያዎች ነበሩ። ትህነግ/ሕወሓት የተከተለችው ከዛ በኋላ ነው። ከሰኔ 15 ጀምሮ የተደረጉትን የጅምላ አፈሳዎች አስመልክቶ ትህነግ “ከፌደራል መንግስቱ ጎን ነኝ” ብሎ ነበር። በአንዴ ደም ያደረቁ ያህል የተወዳጁት በአማራ እስር ነው።

ኦዴፓ ከሰኔ 15 በኋላ አማራው ላይ ቢያንስ ሁለት ነገሮችን ጠብቆ ነበር። አንደኛውና ያተርፈኛል ያለው ረብሻ ነበር። በዚህ ረብሻ አስታክኮ ብዙዎችን መምታት ነበር። ክልሉን ለረዥም ጊዜ በጊዜያዊ አዋጅ ስር ማዋል ነበር። ሕዝብ ግን ያሰበውን እንዳያሳካ ጨዋ ሆኖ ሀዘኑን አሳለፈ። ከአማራ ሕዝብ ሌላኛው የተጠበቀው ስሜት ቁዘማ ነበር። አንገቱን ይደፋል፣ ዝም ጭጭ ይላል እንጅ ፌደራል መንግስቱ የሰራውን ቢሰራ ምንም አይልም ተብሎ ነበር። ይህኛውም አልሆነም። ሴራ የሰራው አካል ያላሰበውን ትችት ከአማራ ሕዝብ ገጠመው። ለዚህም ሲባል አማራውን አንገት ማስደፋት የሚቻለው በዚህ ክስተት ብቻ እንዳልሆነ ስምምነት ላይ ተደርሷል። አማራው በዚህ ክስተት ጥንካሬውን ሲያሳይ ለገዥዎች አስደንጋጭ ሆነ። በቀላሉ እናንበረክከዋለን ሲሉ ጨዋነቱ፣ ብርታቱ አስደነገጣቸው። አማራውን አንገት ለማስደፋት ሌላ ኃይል ጋር ግንባር መፍጠርን አሰቡ። ትህነግ/ሕወሓትም “በወንጀል ኖሩበትም አልኖሩበትም በጅምላ ማሰር ነው” አለ በደብረፅዮን በኩል። አማራን አንገት ማስደፋት የሚባለው ፕሮጀክት እነ ጌታቸው አሰፋን እይዛለሁ እያለ አዲስ አበባ ላይ የሚፎክረውንና መቀሌ ሆኖ “አትወስደውም” እያለ የሚደነፋውን አንድ አደረገ።

ኦዴፓ አማራን ኦሮማራ በሚል ማጭበርበሪያ ለመወዳጀት ሲልካቸው የነበሩትን፣ ኦሮማራ ቀልድ መሆኑ ሲታወቅ ኩሽ እያለ በየ ክልሉ ሲንከራተት የከረመውን ህዝቅኤል ጋቢሳ ወደ መቀሌ ላከ። ትህነግ/ሕወሓት አዴፓ ጋር አልሰራም ባለበት መግለጫ ከስር ያለውን ብሏል።

“ህወሓት እንደ ኣንድ ህገ-መንግስታዊና ፌደራላዊ ኃይል ህዝብን እና ሃገርን ኣሁን ካለው እና ከመጪው ችግር ለማዳን ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ህገ-መንግስታዊና ፌደራላዊ ኃይሎች ጋር ሰፊ መድረክ ፈጥሮ እንዲታገልና ወደተግባርም እንዲገባ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጥሪውን ያስተላልፋል”

ፌደራሊዊና ሕገ መንግስታዊ የሚባለው “ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ” የሚለውን ኃይል ነው ማለት ነው። በቅርቡ ትህነግ/ሕወሓትም ትግራይ ለመገንጠል እንደምትገደድ አሳውቆ ነበር። ኦነግና ትህነግ በ1970ዎቹ የአማራ ሀገር ነው ካሉት ኢትዮጵያ ለመገንጠል፣ እንዲሁም ከ1983 ዓም በኋላ አማራ ወደ ስልጣን እንዳይመጣ ጊዜያዊ ውል እንደተዋዋሉት ዛሬም የአማራው ጉዳይ አንድ ያደርገናል እያሉ ነው። የኦሮሞ ኃይሎች ትህነግ/ህወሓትን ሕገ መንግስት የሰጠን ነው እያሉ ባመለኩበት ወቅት በአንድነቱ ጎራ ሲቃወማቸው የነበረውን ሁሉ እንኳ አማራ ብለው ሲያሸማቅቁ ነበር። በተቃዋሚው ጎራ የነበሩት የኦሮሞ ኃይሎች እንኳን ከሌላ ወገን የሆነውን የአንድነት ኃይል ሳይቀር አማራ ብለው ሲፈርጁ ኖረዋል። የሀሰት ትርክትን ቀን ከሌት ያላመነዠከን ኦሮሞ ተቃዋሚም “ነፍጠኛ፣ ጎበና” እያሉ ከትህነግ ጋር ቃላትን ተጋርተው ሲያሸማቅቁ ኖረዋል። ዛሬ ደግሞ የአማራ ብሔርተኝነት ሲጠናከር ሌላ ሳይከሱ አማራውና አማራው ላይ አንድ የሚያደርጋቸውን አጀንዳ አግኝተዋል!

ከትናንቱ የትህነግ/ሕወሓት መግለጫ በኋላ ምኒልክ ጡት ቆራጭ ነው፣ አማራ ጨቋኝ ነው………እያሉ የሚዘልፉት የሀሰት ተራኪዎች መቀሌ ተገኝተው “ኦሮማራ ሞቷል” ብለዋል። ኦሮማራ መቀለጃ መሆኑን አማራው ቀድሞ የነገራቸው ቢሆንም ከትህነግ ጋር ለመተቃቀፍ በአደባባይ ተናግረውታል።

የቀን ጅብ ብለው ስም ያወጡት ሰዎች የቀን ጅቦች መነሃሪያ ነው ወዳሉት አቅንተው እያወሩ ነው። እነዚህ ኃይሎች ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ ለግላቸው ሲስገበገቡ ያጋለጣቸው አማራውና ከተሜው ነው። ትህነግ/ሕወሓት ሲስገበገብ የኦሮሞ ወጣቶችን እግር ቆርጧል። የኦሮሞ ፅንፈኞች ትናንት እግራቸው ተቆርጦ ታዝለው የወጡትን ወጣቶች ሳይሆን የሀሰቱን የምኒልክ ጡት ቆራጭነት ትርክት ማመንዠክ ይቀናቸዋል። ስግብግብነታቸው፣ አማራ ጠልነታቸው በወንድሞቻቸው ላይ የተፈፀመውን፣ የቀን ጅብ ሲሏቸው የነበሩትንም እንዲረሱ አድርጓል።

ኦዴፓ ሲስገበገብ ያጋለጠው አማራውና ከተሜው ነው። ሆኖም ስልጣን ያጣው ትህነግ/ሕወሓት የአዲስ አበባ ጉዳይ ምኑም ነው። ለኦዴፓ ደግሞ የፖለቲካ እስትንፋስ ተደርጋ ተወስዳለች። ትህነግ/ሕወሓት አዲስ አበባ ላይ ልክ እንደ ነቀምት ንግድ ካሳደደና ገንዘብ ካካበተ በቂው ነው። ለህዳጣኑ ትህነግ አዲስ አበባ እንደማንኛውም ከተማ ሰርቶ መኖርያ ከሆነች በቂ ነው። ኦዴፓ ቢጠቀልላት ችግር የለበትም። ለኦዴፓ ጌታቸውን አስረዋለሁ እያለ መፎከር ብቻ በቂ ነው። ፉከራ ደግሞ አያጣላቸውም። ጌታቸው አሰፋ እያለ ሌሎች ንፁሃንን በተለይ አማራውን ማሰር ደግሞ ያስተቃቅፋቸዋል።

ትህነግ/ሕወሓት የኦሮሞ ፅንፈኞች ላይ የሚቀልደውን ያህል ማንም ላይ ቀልዶ አያውቅም። ኦነግ ነው እያለ አዲስ አበባ ላይ ፈንጅ እያፈነዳ የኦሮሞ ወጣቶችን ሲያስርና ሲያኮላሽ፣ እግራቸውን ሲቆርጥ፣ ሴቶቹን ሲደፍር እንዳልኖረ የኦነግ ጦር ሲገባ የጭካኔው አባት ስብሃት ነጋ የኦነግን ባንዲራ ይዞ ተቀበላቸው። በኦነግ ስም ሲያርድ የነበረ አካል፣ በፀረ ሽብር የተፈረጁት ድርጅቶች ፍረጃቸው መነሳት የለበትም ብሎ ሲያለቅስ የነበረ ድርጅት ድግስ ደግሶ ሲጠብቀው ኦነግ ደስ ብሎት አዳራሽ ውስጥ ተቀመጠ። በኦሮሞ ፅንፈኞች ላይ ትህነግ/ሕወሓት የቀለደውን ያህል ማንም ቀልዶባቸው አያውቅም። ዛሬም “የቀን ጅብ” እያሉ ድንጋይ ሲወረውሩበት ወደነበረው ትህነግ/ሕወሓት አንገታቸውን እያሰገጉ ነው። ስለ አማራ ክፉ ክፉ ከተናገረላቸው ሌላ ለሌላ ማሞኛ ስንቅ የሚሆነውን ፈንጠዝያ ይዘው ይመለሳሉ። አያ ጅቦም የሚያደርገውን ያውቃል። ነገ ደግሞ ኑ ትህነግ/ሕወሓትን እንርገመው ብለው ይመጣሉ!

አያ ጅቦ እና የኦሮሞ ፅንፈኞች እፍ ክንፍ ሲሉ ጊዜ መርህ የሚቀይር ካለ የዋህ ነው። ይሸነፋል! ለእነዚህ አካላት መርህን ማጥበቅ የመሰለ ነገር የለም። እነሱ በፀረ አማራነት ይስማማሉ። እነሱ ኢትዮጵያን ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ተጠቅመው እንደ ፔስታል ለመጣል ተመሳሳይ ናቸው። ይህ ደግሞ መርህን ለያዘ አካል ሊሆን አይችልም። እንዲያውም እነዚህ ኃይሎች ለይቶላቸው ጥግ ቢይዙ መልካም ነበር። የቀን ጅብ ነው ብሎ ድንጋይ የሚወረውርና የቀን ጅብ በደንብ ሲቀራረቡ ነው የሚሻለው! ውጤቱን በደንብ ተቀራረብን ሲሉ የምናየው ይሆናል። ሁለቱ ስግብግቦች ፊት ለፊት መገናኘት ስለማይችሉ በመሃል መጫወቻ ማድረግ ይፈልጉ የነበረው አማራውን ነው። ከ1983 በኋላ ፊት ለፉት ተገናኝተው ተፋጅተዋል። ትህነግ በብልጠት ኦነግን ማርካዋለች። እስካዛሬ ባለው በተለይ ደግሞ ባለፉት ወራት አማራው መሃል ላይ ነበር። ዛሬ ግንባር ለግንባር እንገናኛለን እያሉ ነው። ሁለቱ ስግብግብ ኃይሎች (ትህነግና ኦነግ) ፊት ለፊት ሲገናኙ ምን እንደሚፈጠር የምናየው ይሆናል። የሚያስፈልገው ጥሩ ተመልካች መሆን ነው!

2 COMMENTS

 1. ጥሩ ግንዛቤ አስጨብጠኸናል ትላንት እንደዛ መቀለጃ ያደረጋቸውን ትግሬ ጉልበት ስመው ማረን ለማለት ወደ መቀሌ ከሄዱ የኦሮሞ ወንድሞቻችንን ከገቡበት ድንቁርና ማላቀቅ የዜጎች ሀላፊነት ነውና
  ይሄ ህዝቅኤል ጋቢሳ ማለት እንደው ትንሽ እንኳን ምሁር ምሁር አይሸትም?ንግግሩ ተረት እውቀቱ ባዶ ተግባሩ ሁሉ ፖለቲካ ሳይሆን ስራ ፍለጋ ይመስላል።
  በተረፈ ማህደሩ ተፈልፍሎ የተገኘው ስለ ጫት ብቻ ነው አሁንም የጫትን ውለታ የረሳ አይመስልም።

 2. ውድ ሳተናው አዘጋጅ፣
  “ፕሮፊሰር ጫት ወደ መቀሌ ጎራ ብሎ ፣ መርቅኖ፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀ መድረክ ይችን ብሏል” የሚል ጽሑፍ ለጥፋችኋል። ይኸ አስነዋሪና ከጋዜጠኛነት ምግባር የወረደ ተግባር ነው። እንዲነሳ እጠይቃለሁ። ፕሮፌሰሩ ከላይ ስሙንና ፎቶውን የለጠፋችሁት ሕዝቅኤል ገቢሳ ነው። እኔም ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል የሚያራምደውን ገንጣይ ጥላቻ አልቀበልም። በአንጻሩ፣ እንደ እርሱ ጥላቻን በጥላቻ በመመለስ አልሳተፍም። የታሪክ ምሁር መሆኑን፣ ስሙንና ማዕረጉን ግን መካድ ወይም መከልከል አልችልም። በግንፍልነት ወደ ስምምነት መድረስ አንችልም። ከላይ የጻፋችሁት እጅግ ጥላቻና ውሸት የበዛበት ነው። አገራችንን ከወደድን፣ አንድን ኦሮሞ ግለሰብ ለማጥላላት ኦሮሞን ሁሉ “ጽንፈኛ” ማለት የትም አያደርሰንም። የትግራይ ተወላጅ ጥላቻን በአማራ ተወላጅ ጥላቻ መመከት የትም አያደርሰንም።

  ሳተናው የጥላቻ ማከፋፈያ መሆን የለበትም። ሰው አክባሪ፣ አሳብ ተደራዳሪ መጽሔት እንዲሆን የአታሚዎቹን ብቃትና ቁርጠኛነት ይጠይቃል!!
  ለምሳሌ እስቲ ሰመረ ከላይ የጻፈውን እንመልከት፦ “… ትላንት እንደዛ መቀለጃ ያደረጋቸውን ትግሬ ጉልበት ስመው ማረን ለማለት ወደ መቀሌ ከሄዱ የኦሮሞ ወንድሞቻችንን ከገቡበት ድንቁርና ማላቀቅ የዜጎች ሀላፊነት ነውና ይሄ ህዝቅኤል ጋቢሳ ማለት እንደው ትንሽ እንኳን ምሁር ምሁር አይሸትም? ንግግሩ ተረት እውቀቱ ባዶ ተግባሩ ሁሉ ፖለቲካ ሳይሆን ስራ ፍለጋ ይመስላል። በተረፈ ማህደሩ ተፈልፍሎ የተገኘው ስለ ጫት ብቻ ነው አሁንም የጫትን ውለታ የረሳ አይመስልም።” በሰመረ አስተያየት ውስጥ አንዲት እውነት የለችበትም! “ትግሬ ጉልበት ስመው ማረን ለማለት ወደ መቀሌ ሄዱ?” በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር እንደ መሆኑ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ጥናቱን ሊያካፍል ነው የሄደው፣ ኦሮሞን በመላ አይወክልም። ሰመረ ከሦስት ኣመት በፊት የተካሄደውን ታሪክ ማስታወስ እንኳ አልቻለም። ለ24 ኣመት በኢንቬስትመንት አሳብቦ ኗሪውን ኦሮሞ ከመሬቱ ላይ አፈናቅሎ ለራሱ ንግድ ሲያካሄድበት የነበረው ህወሓት አልነበረም? ቢሾፍቱ ኣመታዊ ክብረ በኣል ላይ ከስድስት መቶ በላይ ኦሮሞ ወጣት የፈጀው ህወሓት አልነበረም? ኦሮሞ ወጣት እምቢኝ ብሎ ሲያምጽ እንደ ጠላት በሄሊኮጵጠርና በአጋዚ ጦር የረፈረፈው ህወሓት አልነበረም? ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ይህን ረስቶ ጉልበት ይስማል ብለህ ታስባለህ? ይልቅ ህወሓት ስለጠበበበት አማራን ከኦሮሞ ለማናቆርና መሓል ላይ እንደገና ዘው ብሎ መግቢያ እየፈለገ ነው!! ይቺን ታክል እንዳታስብ የበዛው ጥላቻ አሳውሮናል! የግለሰቦችን አስተያየት የአገር ሁሉ ባናደርገው አሁን ምናለበት?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.