እኛ፡በብሔራዊ መረጃና ድሕንነት አገልግሎት ባልደረቦች ከስራ ገበታችን በግፍና በ-ኢሰሠብአዊ መንገድም ተባረናል

ቀን፡5/11/2011 ዓ/ም

                  ለሚመለከተው አካል

እኛ፡በብሔራዊ መረጃና ድሕንነት አገልግሎት ባልደረቦች በመሆን ያገለገልን ኢትዮጵያውያን ነን።ከ 2010 ዓ/ም በፊት ከስራ ገበታችን በግፍና በ-ኢሰሠብአዊ መንገድም ተባረናል።ሰብአዊና ደሞክራስያዊ መብታችንን አጥተናል።ስራ ላይ እንዳንሠማራም ታግደናል።ምንምኳ አቤቱታ ብታቀርብም ማንም የሚሰማህና የሚያስተናግድህ ሰው ይሁን አካል ከቶ አይገኝም ነበረ። እስከ አሁን ቢሆንም ከለውጡ ማግሥት ምንም መፍትሄና ትኩረት ልናገኝ ፍጹም አልቻልንም።

በአቶ ጌታቸው አሰፋ አስተዳደደር ጊዜ፡በፖለቲካ እምነታችን፣በያዝነው አቋም፣ሀሳቦቻችንና አስተያየታችን መሠረት በማድረግ ለብዙ መከራና እንግልትን ተዳርገናል።አንዳንዱም በብሔሩና በያዘው አመለካከት ተፈርጆ ለመሰል ችግሮች ተዳርገዋል።የስራ ልምዳች በተመለከተም ሊሰጠን አላተቻለም።ለዓመታት ለሰራንበት ማንኛውም ምስክር ወረቀት እንድናጣ ሆነናል።

‘ሕገ-መንግሥት እናስከብራለን፥ዘብ እንቆምለት አለን’ ብሎ የሚደሰክሩ ሁሉ፡ሕገ-መንግሥታዊ ዋስትናችን ሙሉ በሙሉ አጥተን።ሰብአዊና ደሞክራስያዊ መብታችን በሚገርምና በሚያዛዝን ሁኔታ ተረግጠዋል።”በሕገ-አምላክ!!” በሚል የአስተሳሰብ ልእልና የሚያመላክት፡ለፈጣሪና ለሕልና የሚገዛ የነበረ ሕዝብና መንግሥት፣ሕግ-አምላክ የማትልበት ደረጃ ደርሰናል!! ያ በትልቅ መሥዋእት የተገኘ የሚባለው ሕገ-መንግሥትም፡የበላይ ሕግ መሆኑም ቀርቶ፡የጨቋኞች መሳርያና ማገልገያ ሲሆን ባይናችን አይተናል።እኛም ጋ የደረሰውን ግፍና በደል ሕያው ምስክር ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ መራር ተጋድሎና በእግዚአብሔር ድጋፍም ታክሎበት፡በ 2010 ዓ/ም ጥገናዊ ለውጥ እንዲመጣ ተችለዋል።ከ 2010 ዓ/ም ጀምሮ የተደረገ የአመራር ለውጥ፡መሠረት በማድረግ ብዙ ተስፋና እምነት እንድናደርግ አስችሎን ነበር።በተለይ ጀነራል አደም መሐመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ፡የዶ/ር አቢይ አህመድ ፈለግን ተከትለው፡ብዙ ተስፋ የተጣለበት ድስኩር በማድረጋቸው፥እኛም ፍትህና እልባት እናገኛለን የሚል ከፍ ያለ ተስፋ ጥለን ነበር።

ቢሆንም ጀነራል አደም ብዙ ዲስኩርና ተስፋ ቢሰጡን በተጨባጭ ምንም ሲደረግ አላየንም፤አልሠማንንም።በሕገ ወጥ መንገድ ከተባረሩ የቀድሞ ባልደረቦቻችን፡የተወሰኑ ለቃለ-መጠይቅ የተጠሩ ቢሆንም ያለተጠሩም እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።ከተጠሩትም መሀኸል የተለያዩ መሠናክሎች የደረሰባቸውና የሴራ ፖለቲካ የሚመስል ሥራዎችም ሲሰራባቸው ተስተውለዋል።ይህም በማወቅ ይሁን ባለማወቅ ተደርግርዋል።የድሮ ሰዎች በጓሮ ወይም በእጃ ዙር ፖለቲካ ጫናም ሊኖርባቸው እንደሚችል ጥርጣሬ አለን።ምክንያቱም ድርጅታዊ አሰራር ባግባቡ ይሰራ እንደሆነ ግራ ያጋባል!!

ጀነራል አደም መሐመድ አምና በክረምት ወቅት፡በኢትቪ/ኢቢሲ መስኮት ቀርበው ብዙ ከተናገሩና ዲስኩርም ቢደሰክሩም የሚጨበጥ ሥራ ሲሰሩና ሲያሰሩ አልተስተዋለም፤በተጨባጭ ያከናወኑት ሥራ ልናይና ልንገነዘብ አልቻልንም።ካለም ሊገለጥልን ወይም ከጊዜ አንጻር በሂደት፡ የሚታይ ይሆናል የሚል እምነት አለን።ጀነራሉ ምን እየሰሩ ነው ብለንም ለአንድ አመት የሚያክል በትእግሥትና ራሳችንን በመግታት ብንጠብቅም፣ ተስፋችን እየተማጠጠ ባለበት ጊዜ ድንገት በሚመስል አኳሀን ሥልጣናቸው እንደለቀቁ በዜና አውታሮች ሰምተናል።የጀመሩት ነገር ካለ ምን መቋጫ ወይም ምን ላይ ደረጃ እንደደረሰ ሳናውቅና አንድ ቀን ቢሆንም ሳያነጋግሩን መስርያ ቤቱን መለቀቃቸው ግራ ገብቶናል።አስተዛዝቦናልንም!!

ያጋጠሙን ችግሮችና መሰናክሎች እጅግ ብዙና የተወሳሰቡ ናቸው ቢሆንም ባጭሩ ይህንን ይመስላል።በጌታቸው አሠፋ አመራር ጊዜ እጅግ ብዙ የሚዘገንኑና የሚያዛዝኑ ችግሮችና አፈናዎችን አልፈናል።በተከሰተው የጥገና ለውጥም ተስፋ በማድረግ በትእግስት ብንጠባበቅም፣ለውጡም በየቀኑ እየጨለመብን ነው።መሰንበት ደግ ነው!!

መድረክ እንዲዘጋጅልን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ችግር ሰሚ የሚባል ሰው ይሁን አካል ከቶ የለም።ለሌሎች መሰል መስራቤቶችና የሚኒስተር መስራቤቶች በየደረጃቻው የፖለቲካ መድረክ አግኝተዋል።በትንሹም አተንፍሰዋል።እኛ ግን አሁንም ታፍነናል።አሁንም ያገኘነው መፍትሄና እልባት ከቶ የለም።የመዋቅር ለውጥ እየተደረገ መሆኑን እንደ ሕዝባችን በሚድያ ከመስማት  ባለፈ፡በቀጥታ ተጎጅዎች እንደመሆናችን ያነጋገረን ፍጹም የለም።

ባለፈው 15 ወራቶች እጅግ ብዙ ስራና ለውጥ ለማየት ጓግተን እየጠበቅን ነበር።ቢሆንም ግን መሬት የነካ ለውጥና ስራ እየተሰሩ ናቸው የሚል እምነት እንዳናሳድር ዳርጎናል።አሁንም ቢሆን መብታችን እንጠይቃለን።ለቃለ-መጠይቅ፡ያልተጠራን የቀድሞ ባለደረቦች ተጠርተን ምርመራና ጥየቃ እንዲደረግልን እንጠይቃለን።ለቃለ-መጠይቅ ተጠርተን የነበርን ሰዎችም መፍትሔ እንዲበጀልን እንጠይቃለን።አዲሱ ጀነራል ዳይረክተር አቶ ደም-መለሽ ገብረሚካኤል እንኳን ወደ ቦታው መጡ እያልን።እርሶ፡የሰውን ችግር ትኩረት ሰጥተው እንደሚያዳምጡ ከቀድሞ ባልደረቦቻቹ ሰምተናል።ስለዚ፡ፍትሕና መፍትሔ ባፋጣኝ እንሻለን።እናመሰግናለን!                                                                                                 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቃት!!                                                                                                      

ከቀድሞ ባልደረባዎች

 

1 COMMENT

  1. ወገኖቼ ሃገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ ናት። ወያኔና የአማራው ክልል ተፋጠዋል። በዛላበሳ በኩል የሱማሌ ስደተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ ገቡ የሚለውን ሳነብ ሃገሪቱ ለመውጣት ወደ ማትችልበት ማጥ ውስጥ እየገባች እንደሆነ ያለአንዳችት ማቅማማት ያመላክታል። የዓረብ አለሙ ስዊዘርላንድ እየተባለች የምትጠራው ሊባኖስን ዛሬ ላለችበት የፈራረስና የሃገሪቱን ክርስቲያኖች ከምድራቸው ጠራጎ ያባረረው የያሲር አረፋት ቡድን በምድሪቱ ዘልቆ በመግባቱ ነው። ያ ቡድን ዛሬ በተለያየ ስም በሃገሪቱ ውስጥ ከኢራን ጋር በመዛመድ ምድሪቱን ተቆጣጥሯል። በአዲስ አበባ አፈናውና እስሩ ቀጥሏል። ማሰር ካልቻሉ የመገልገያ መኪናዎችን ይቀማሉ፤ ስብሰባ ይረብሻሉ፤ በሆነና ባልሆነው በስልክ ያስፈራራሉ። ሴቶችን ይደፍራሉ፤ በጠራራ ጸሃይ ሰውን በሞተርና በእግር ሰርቀው ይሰወራሉ። ባጭሩ ስርአት አልባ ሁኔታ ቀንና ማታ የሚታይባት ከተማ ሆናለች። በየትኛውም ሃገር ቢሆን የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር የሚሰረቅበት ምድር የለም። በሃበሻ ምድር ግን ይሰረቃል። ዞሮ ተመልሶ ደግሞ መብራት ሃይልን ይከሳል።
    በትግራይ ለዘመናት ሲያፈርሰውና እንደ ቦይ ውሃ እንደፈለገ ሲቀይሰው የነበረውን ህገ መንግሥት አልተከበረም በማለት የችግሩ ሁሉ ምንጭ አማራ ነው ብሎ ያሽካካል። በአማራው ክልል ደግሞ የበፊትም ሆነ የአሁን ችግራችን ምንጭ ወያኔ ነው በማለት ይጎሽማል። እናስብ እንዲህ ባለ የለበጣና የጠለፋ ፓለቲካ በሞላበት ሃገር እንዴት ነው ለሃገርና ለዜጎች ድህንነት መንግሥት የሚቆመው? የክልል ፓለቲካ ማንን ጠቅሞ ማንን ይጎዳል? እስከ ዛሬ ድረስ በዚህ ሸፋፋ የፓለቲካ መስመር ያተረፉስ ወደፊት ማትረፍ ይችሉ ይሆን? ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚሉት ሃይሎች እነርሱ ናቸው አፍራሽ ሥራ የሚሰሩት ያሉት። የለየላቸውም እንገንጠል እያሉን ነው። የዶ/ር አብይ መንግሥት ወያኔን መስመር ካላስገባ በሌሎች አካባቢዎች የሚያደርገው እስራትና ገፈፋ ከማንም ልብ አይገባም። የሃገሪቱ ችግር ያለው መቀሌ ነው። ጠ/ሚሩ ወያኔ ወደ ስልጣኑ ለመመለስ በሰሜን አሜሪካና በሌሎች ሃገሮች በክፍያ ላቢ እንዲያደርጉ ያስቀመጣቸው ሰዎች እንዳሉ? የቀድሞ የብሄራዊ መረጃ ባልደረቦችን የምመከረው ሥራ ፈጣሪው መንግሥት ብቻ አይደለም። እናንተም ተደራችታችሁ በሃገሪቱ ልዮ ልዪ ጉዳዮች ላይ የጠለቀ መረጃን በመሰብሰብ ለጋዜጦች፤ ለቴሌቪዝንና ለመንግስት መሸጥ ትችላላችሁ። ዋናው ነገር የመረጃ አሰባሰባችሁና እውነታነት ነው የሚወስነው። የወሬ ገቢያ ከወርቅ ገቢያ በላቀበት በዚህ ዘመን እናንተም የቀድሞና የአሁን ልምዳቹሁን በመመርኮዝ ዜናን የመኖሪያ ብልሃት ማድረግ ትችላላቹሁ። ወደ መንግሥት መጮሁ ምንም ፋይዳ አያመጣም። ህጋዊ የሆነ ድርጅት ፈጥራቹሁ ወይም በህቡዕ በመረጃ የተጠናከረ የግለሰቦች ወንጀል፤ በሃገር ላይ የሚቃጣ ችግር፤ የዘራፊዎችንና የዘር ተሰላፊዎችን ገመና በማጋለጥ የምርመራ ስራቹሁን በመሸጥ የመኖሪያ ብልሃት መፍጠር ትችላላችሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.