አቶ ልደቱ አያሌዉ አቶ ሌንጮ ለታን አንገት የሚያስደፋ ንግግር አደረጉ

አቶ ልደቱ አያሌዉ አቶ ሌንጮ ለታን አንገት የሚያስደፋ ንግግር አደረጉ

\\

3 COMMENTS

  1. አቶ ልደቱ አያሌው በሃገራችን የፓለቲካ መድረክ ላይ ጎልተው ከሚታዪት ሰዎች አንድ ናቸው። አንደበተ ርቱዕና ሁለገብ እይታ ያላቸው አቶ ልደቱ በአማች የፓለቲካ ሰዎች ለዘመናት የሌላቸውን ስም ሲሰጡ፤ ጭቃ ሲቀቡ፤ ሲሰደቡ እና አልፎ ተርፎም ሲያስፈሯሯቸው እንደነበር እና እንዳሉ መረጃዎች ያመለክታሉ። መቼም የሃገራችን ፓለቲካ ስሙኝ እንጂ ልስማህን አያውቅም። እኔ አቶ ልደቱን በግል አላውቃቸውም። የማውቃቸው በጭልፋ ከሚተላለፈው የዜና አውታር ከሚገኘው መረጃ ብቻ ነው። አቶ ልደቱ የሃገራችን የፓለቲካ ሸረባ አጥብቀው ከተረዱት ወገኖች አንድ ናቸው። በሳልና የጠለቀ እይታቸው ለሃገራችን የጎጥ ጎራ አራማጆች የጎን ውጋት ከሆነ ውሎ አድሯል። በመቀሌ ባደረጉት ንግግር እንዲህ በለው ነበር። “ይብቃቹሁ መሪነቱን ለአዲሱ ትውልድ አስረክቡ” ራቅ ያለውን ስናወሳ ደግሞ ጠ/ሚ መለስንና በዙሪያቸው ያሉትን በመረጃ ሲያፋጥጡ ከነበሩት ጥቂት የምክር ቤት አባሎች መካከል አቶ ልደቱ ቀዳሚው ናቸው። ዛሬም ቢሆን ሰለቸኝ ሳይሉ እውነትን በየመድረኩ በረጋ መንፈስ ሲናገሩ መስማት ሆያ ሆዬ ለሞላበት የአስረሽ ምቺው የሃገራችን ፓለቲካ የአቶ ልደቱ ሃሳብና እይታ ንጽህ አየርን ያነፍስበታል። አቶ ሌንጮን አንገት የሚስደፋ ምንም ነገር አቶ ልደቱ አልተናገሩም። ሃሳብን በሃሳብ ሞገቱ እንጂ። አቶ ሌንጮም አንገት የሚያስደፋ ሃሳብ አላቀረቡም። ግን የሸር ፓለቲካ ሁልጊዜ የሚያነፈንፈው የገማ ነገርን ብቻ ነው። ለፈጠራ ዜናው፤ ሃተታው፤ ሽኩቻው፤ ቀረርቶውና በሆነ ባልሆነው ያዘው ጥለፈው ለሚለው የፓለቲካ ጊዜ የምናጠፋውን ለቁም ነገር ብናውለው ህዝባችንና ሃገራችን የት በደረሱ ነበር። በመሰረቱ አፍሪቃዊው ህይወት ከራሱ ጥላ ጋር የተጣላ ነው። ለምሳሌ ከሰሞኑ በሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተደርጎ ከሸፈ የሚል ሳነብ ሳቄ መጣ። ፈንቃይን ፈንቃይ ሊተካው ሲከጅል። ለዛውም ወራት ያልቆጠረ መንግሥትን። እንዲህ ነው ሃገር ማረጋጋት። ችግሩ ግን በሱዳናዊያን ብቻ የመነጨ አይደለም። ግብጽ፤ ቱርክ፤ የባህረሰላጤው የነዳጅ ባለሃብት ሃገሮች በሳውዲ መሪነት እና የኢራናውያን እጅም አለበት። እነዚህ ደግሞ በሁለት ወገን ተከፍለው ሃገርን ያምሳሉ። የቱርክ በሶማሊያ የወታደራዊ ካምፕ መመስረት ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው። አሁን በዛልአምበሳ በኩል በስደት ስም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡትም ሶማሊያውያን ያለውን የህዝቦች ስብጥርና እምነት የሚያዛባ ስለሚሆን የወደፊቱ የሃገሪቱ ፓለቲካ ልክ እንደ ሊባኖስ እንደሚሆን ከአሁኑ መገመት አያዳግትም። በመጨረሻም የአማራ፤ የኦሮሞ፤ የሲዳማ፤ የሃረሬ የትግራይ ወዘተ ተወላጅ መሆን በምርጫ የመጣ አይደለም። አንድ የአንድን እምነትና ባህል ካላደነቀለት የብቻ ብሄር ብሄረሰብ ነኝ ባይ አንድ እጣትን ለጭብጨባ እንደመጋበዝ ይቆጠራል። ህይወት የሚጥመው ሲጋሩት ነው። እይታ የሚሰፋው ከመንደር ወጣ ሲባል ነው። ያ ካልሆነ ሁልጊዜ የዛገ ሃሳብ ተሸክመን እኔን ብቻ ስሙኝ ስንል መሽቶ ይነጋል። በዚህ የአስረሽ ምቺው ፓለቲካ እንደ አቶ ልደቱ አያሌው፤ እንደ ዶ/ር መራራ፤ እንደ ፕ/ር መስፍን ያሉትን አክብረን ሃሳባቸውን በመረዳት ማገዝ አለዚያም መስመር የያዘ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው። እንዲሁ ግን መሳደብ፤ የፈጠራ ወሬ በሰዎች ላይ ማስወራት፤ እየደወሉ ማስፈራራት የኋላ ቀርነት ነው። በእኔ እምነት አቶ ልደቱ አያሌው ለሃገራችን ፓለቲካ ኮረሪማ ናቸው። ይበርቱ እንላለን!

  2. ሌንጮ አንገቱን የደፋው ምንልካዊዉ አቶ ልደቱ በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ክልሎች ለተበተኑት የነፍጠኞች ልጆች ብቻ ተጨንቆ ሲቀባጥር ሃፍረት ተሰምቶት እንጂ ምን ቁም ነገር ተናገረና?? የምሁራንን ምክክርን እንደሴተኛ አዳሪዎች ንትርክ የምትረዱ እናንተው ናችሁ አንገት መድፋት ያለባችሁ!

  3. “ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ” የሚል የሃገራችን ብሂል ልደቱና ሌንጮን ዋቢ ለሚያደርጉ ከንቱዎች ጥሩ ማብራሪያ ነው:: ልደቱ ህዝባችን በጥሩ በወላዋይነቱ ተንሸራታች በሃሰተኛነቱ ክህደቱ የሚል መለያ የሰጠው ሰው ነው:: ከመጀምሪያው በወያኔ ለታማኝ ተቃውሚነት ከኬንያ ተመልምሎ መምጣቱን የ1997 ምርጫ አጣሪ አባል ፓስተር ከበደ ደጉ በዚያው ሰሞን በዩቱብ ያጋለጡት ጉድ ነው:: የእሱ ተከታዮችም እነ ኣብዱራህማንና ሙሼ እንዲሁ የፓርላማ ወንበር ሲያሞቁ የድሃ ግብር ከፋዪን ህዝባችንን ብር በከንቱ ስሊፉ ቆይተው አብዱራህማን ጡረታ ወጣሁ ብሎ በፓርልማ ሳለ ስለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን አንድም ቀን ተንከር ያለ ተቃውሞ ሳይሰማ በሚኖርበት ሰፈር ኮተቤ የጅቦች ጩህት አሰቸገረ ብሎ ለምቾቱ ብቻ የሚለፍፍ ነው:: ልደቱ ክህደቱ ወደመቀሌ በመሸጉት ጌቶቹ ሰፈር ሄዶ ራሱ ወያኔ ህወአት ብሎ የሰጠውን ስም ወያኔ ብዬ ኣለጠራቸውም በማለት የሰየሙትን መጠሪያ ሊሰርዝ የሚፈልግ ከንቱ ሲሆን የህዝቡን ድምጽ ተከትሎ የነበረው ቅንጅቱን በማፈራረስ ዋና ተዋናይ ሲሆን ያ ሁሉ ህዝብ በወያኔ ነፍሰገዳዮች ተጨፍጭፎ ሳለ የመለስ ዜናዊን ምገሳ በማግኘት ፓርልማ በመሳተፉ ዲሞክራሲ አለ ብሎ የሁሴን ኦባማ መንግስት ይቀበለው ዘንድ የወያኔን ምኞት ያስፈጸመ ከሃዲ ዛሬ ስለህዝባን ሊናገር አንዳች ብቃት የለውም::ሌንጮ ለታ ከነባሮ ቱምሳ ጋር በወጣትነቱ ለኦሮሞ መብት ያደረገውን ክብር በመስጠት ወደለየለት የኢትዮጲያ ጥላቻ ገብቶ ከብዙ ስደት በኋላ በወያኔ ማባበያ ገብቶ የዘባረቀ ሲሆን የወይኔ ጋሪ ሆኖ ላዋቀረው ሀገወጥ ህገመንግስት አብሮ አደጉ ነጋሶ ጊዳዳ ይቅርታ ሲጠይቅ ዛሬም የሚከራከርለት ማስተዋል የጎደለው አዛውንት ነው:: ሌንጮ ድሮ የትንሹ ኦርሚያ ፕሬዚዳንት ከመሆን የትልቋ ኢትዮጲያ ሚስንትርነት ይሻለናል ያለና የአውሮፓ ብርድ ከሚያንገበግበኝ ወደሞቃቱ ሃግሬ ብገባ ይሻሻለናል ያለ ትግሉን ከራሱ ምጪትና ስልጣን ጋር የሚቀምር ደካማ ነው ::በዚህ ሰአት የአባቱን የቄስ ለታን የጥንት ምክር ሰምቶ ልክ እእንደአብሮ ኣደጉ ነጋሶ በክብር ይሸሸኝ ዘንድ እመኛለሁ:: ሚዲያዎች ግን በህይወት መርህ በጎ ምስክርነት ያላቸውን ብታቀርቡ ከመገመት ትድናላችሁ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.