የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ራሱን በማክሰም ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ተቀላቅሏል

ከተመሠረተ 11 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በዛሬው ዕለት ባከሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ራሱን በማክሰም ኢዜማን መቀላቀሉን የኢራፓ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ተናግረዋል።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ባወጣው የአቋም መግለጫው ኢትዮጵያ ያለችበትን ችግር ለመፍታትና ከምንጩ ለማድረቅ መንግሥት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መላው የሀገሪቱ ሕዝቦች በመቻቻል፣ በትዕግስትና በአብሮነት መሥራት እንዳለባቸው ገልጿል።

ስለሆነም ጣት መቀሳሰሩን ወደ ጎን በመተው የምክክርና የድርድር መድረኮች ተዘጋጅተው ተቀራርቦ መነጋገር ይገባል ሲል ጥሪ ማቅረቡን ከኢዜማ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤው መገባደጃ ላይ ኢዜማን በመወከል ንግግር ያደረጉት የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢዜማ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ይፈጥሯቸው ከነበሩ ህብረቶች በተለየ መልኩ ራሳቸውን ያከሰሙ ድርጅቶች በምርጫ ወረዳ የተዘረጉ መዋቅሮችን በመቀላቀል እንደአዲስ ፓርቲ የተመሠረተ ፓርቲ መሆኑን አስታውሰዋል።

ትንሽ ፓርቲ ውስጥ ትልቅ ከመሆን ትልቅ ፓርቲ ውስጥ ትንሽ ሰው መሆን ይሻላል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ በመሠረታዊ መርሆች የተስማሙ የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነው ሰፊ ድንኳን ያለው ጠንካራ ድርጅት የማቆምን አስፈላጊነትን አስረድተዋል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.