ከሕግ ውጪ የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎችን የያዘው የደቡብ ክልል ፍፃሜ በምን መንገድ ይቋጭ ይሆን? | ልዩ ታሪካዊ ዘገባ

ባልደራስ ሚዲያ
በትናንትናው ዕለት ሐምሌ9፣ 2011ዓ.ም የሲዳማ ዞንን የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን በአምስት ወራት ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወስኗል። ከፍተኛ ወታደራዊ ሀይሉን ያሰማራው መንግስትም የምርጫ ቦርድ ሀሳብ እንዲከበር ካልሆነ በጉልበት ነገሮችን ለማብረድ የፈለገ ይመስላል። ለዚህም ሲባል ብዙ ቁጥር ያለው ሰራዊት ደቡብ ክልልን ወሮ ትዕዛዝ እየጠበቀ ይገኛል። በሌላ በኩል የሲዳማ ኤጀቶዎች ከነገ ሐምሌ 11 ማለፍ የለበትም፤ ነገ ክልል መሆናችን እናረጋግጣለን እያሉ ይገኛል። ወላይታና ሌሎች ቀሪ ክልል ጥያቄ ብሔሮችም የፌደራል መንግስት ነገ ለሲዳማ የሚሰጠውን መልስ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛል። ነገ ምን ይፈጠር ይሆን? ቀጣዩ ዘገባም በከባዱ ትንቅንቅ ዋዜማ በደቡብ ክልል ዙሪያ እስካሁን ያልሰማችሁትንና ከህገወጥ ምስረታው ጀምሮ ይዞት እስከመጣው ጣጣና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ይዟል።

3 COMMENTS

  1. The Sidama people have the right to have their own regional state as guaranteed in the cosntitution of the country. The would be Sidama regional state can then resolve the issue of the Hawassa city through negotiations. Histroriaccly the Sidamas have lost territory to the Arsi Oromos of Bale and Aarsi. The good and postive jesture of the Oromo nationalists can not overshadow or forestall these claims. These territorial issues can also be taken up and resolved through negotiations.

  2. የወላይታ ብሔር ራስን በራስ የማስተዳደር በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት መሠረት ያለተገደበ መብት ሆኖ ሳለ እና በአሁኑ ሰኣት ደኢህዴንና ፈዴራል መንግሥት የህዝቡን ህገ መንግሥታዊ መብቱን በኃይል ለማዳፈን የሚያደርገው ጥረት ሀገርቷን ለከፋ ብጥብጠ የሚያዳርግ ስለሆነ ከድርጊቱ እንድቆጠብ እናሳስባለን ። ህገ መንግሥታዊ ጥያቄን በመከላከያ ኃይል ማፈን ተገቢነት የለውም ።

  3. የዎላይታ የነፃነት ጥያቄ የማይቀለበስ ህገ መንግሥታዊ መብታችን ነዉ እኛ አንበረከክም ትግሉ ይቀጥላል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.