“ዶ/ር አብይ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ የሚመስል ቃል በነግራችሁ እንኳን ፖለቲከኛ መሆኑን አትርሱ ” ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ

Getachew Shiferaw

~”ዶ/ር ዐቢይ የመፅሐፍ ቅዱስ የሚመስል ጥቅስ ቢነግራችሁ እንኳን ፖለቲከኛ መሆኑን አትርሱ።”

~”በጣም ትልቁ ችግራችን መሪ እንከተላለን እንጅ መርህ አንከተልም!”

የትነበርሽ ንጉሴ

…………………………………

“ዶ/ር ዐቢይ የመፅሐፍ ቅዱስ የሚመስል ጥቅስ ቢነግራችሁ እንኳን ፖለቲከኛ መሆኑን አትርሱ። ከቤታቸው ብቻ የተፈናቀሉ አይደሉም፣ እነሱ የቆጠሩት ከቤታቸው የተፈናቀሉትን ነው። እኔ ደግሞ የሚያሳስበኝ ከሙያቸው የተፈናቀሉ ብዙ ተፈናቃዮች አሉ። በጣም ትልቁ ችግራችን መሪ እንከተላለን እንጅ መርህ አንከተልም። መሪ ደግሞ ይሄዳል። ይመጣል። ነግሬያችኋለሁ፣ እናንተም አይታችሁታል። መሪው ሀጥያት ሲሰራ ሀጥያት ሰራህ አንልም። ምክንያቱን መሪ ነዋ! ስለ መርህ አንጨነቅም።

……………በፊት ከዚህ ሀገር ታስረው ለነበሩት ጋዜጠኞች ነፃ ሆኖ የመጠበቅ መብታቸው እንዲከበር ስንከራከር የነበርን ሰዎች ዛሬ ደግሞ ለተጠረጠሩ ሰዎች ያ መብት ተጠብቆላቸዋል ወይ ብለን አንከራከርም። እኛ መሪውን እንጅ መርሁን አናነሳውም።”

1 COMMENT

  1. ሎሬት የትነበርሽ ስለብሩህ አእምሮና የዘወተር ምክርሽ ላመሰግንሽ እወዳለሁ:: ይህ በድለላ ቃላት የሰው ልብ እያነሆለለ የአማራውን ህዝብና የደቡብ ወገኖችን ችግሮች ሆን ብሎ የሚያባብብስ በሚገባ ግልጸሽዋል:: አብይ የኦነግ ነፍሰገዳዮችን ፊትለፊት በሜንጫ (በካራ) እናርዳለን ያሉ ለፍቶ ቤት የሰራውን ህዝብ ከተረከበ ደም እናፈሳለን የሚሉና በቡራዩ በሻሸመኔ ዘግናኝ ግድያ የፈጸሙትን በማቀፍ ቤት በመሸለም ሰላማዊ ታጋዮች የከተማቸው መብት በነዋሪዎቹ ይወሰን ያሉትን ጦረኛ ብሎ የሚከስ አብይን ሴራ በሚገባ ገልጸሻል:: ተረቱም” የጠመጠመ ሁሉ ቄስ አይደለም” ይላል መጽሃፍ ቅዱስ የጠቀሰ ሁሉ ክርስቲያን ኣይደለም:: መጽሃፍ ቅዱስ ጠቀሰው ሰውን ባርያ ቅኝ ተገዥ ያደርጉ ድሮ ነበሩ ዛሬ ደግሞ መጽሃፍ ቁስን በመጥቀስ ህዝብ የሚያታልሉ አብይና መሰሎቹ ናቸው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.