የአባቶቹን ታሪክ ክዶ በበታችነት ስሜት እውነትን የካደ ዋጋ ይከፍላል!  (ሰርፀ ደስታ)

ከዚህ በታች እንደው ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ ለማሳያነት ነው ይሄን ቪዲዮ የምጋብዛችሁ፡፡ እውን በኦሮሞ ዘንድ ምሁር የለም? ሁሉም ኢትዮጵያውያን አሁን በኦሮሞ ላይ ያለው አመለካከት ጥሩ እየሆነ አደለም፡፡ ኦሮሞ ሁሉ እንደዚህ እንዳልሆነ ቢታወቅም በሠፊው እየተሰራ ያለውና በሚዲያዎችም እየታየ ያለው ነገር ሁሉም ኦሮሞን እንዲጠላ እየጋበዘ ያለ ነው፡፡ አሁን ለውጥ አመጣሁ ብሎ ዛሬ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ማን እንደሆነ የተነቃበት ቡድን ከመጣ ጀምሮ 50 ዓመት በኦነጋውያን ከሆነው በላይ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ በብዙ እጥፍ ሆኖ ፈጥቶ ወጥቷል፡፡ የኦሮሞ ምሁር ነን የሚሉ በብዛት የዚሁ ችግር ሰለባ በመሆናቸው ሕዝብን ወደነበረበት ልዕልናው ለመመለስ ይቅርና ራሳቸውንም ከገቡበት በራሳቸው ጊዜ የፈጠሩት የበታችነት ስሜት፣ ጥላቻና ዘረኝነት ለመውጣት እየተቻላቸው አይመስም፡፡ በዚህ አንድ አመት ውስጥ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ነን ሲሉ የነበሩ ሳይቀር በውስጥ ደብቀውት የነበረው ዘረኝነትና ጥላቻ ጊዜው የእኛ ነው በሚል ፈንድቶ ወጥቷል፡፡

ለማንኛውም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ ታስፈልገዋለች እንጂ ካልፈለገ ኢትዮጵያ አትፈልገውም፡፡ ለመሆኑ የቀደሙ አባቶችን የምታስቡ ከኦሮሞ የሆናሁ ምሁር ወይም ትልቅ ሰው አላችሁ? የተስፋዬ ገብረ አብና፣ ጀዋር አስተሳሰብ ይሄን ያህል ኦሮሞን በሙሉ በሚያስብል ሁኔታ የአስተሳሰብ ባሪያ አድርጎት እያያችሁ ዝምታችሁ ያሳዝናል ከአላችሁ ማለቴ ነው፡፡ ይሄ ጉዳይ ቆይቶ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ከወዲሁ ማሰብ ካልተቻለ በኋላ የተባለ ዋጋ ሁሉ ተከፍሎ ላይመለስ እንደሚችል እሰጋለሁ፡፡ ምን እንደሚሆን እኔ ነብይ ሆኜ ሳይሆን ግን ከሁኔታዎች የማየው ይሄንን ነው፡፡ ዛሬ ላይ የኦሮሞ ሲንድሮም እስከማለት የደረሱ ሰዎች አሉ፡፡ እንደተባለውም ችግሩ እንደዛ ይመስላል፡፡ በኦሮሞ ፖለቲካ ተቀባይነት ለማግኘት ሌላውን መጥላት መሠረታዊ መርህ፣ የውሸት ትርክት እየፈጠሩ እንደልብ ማውራት ሌሎችም፡፡ እውነቱ ግን ሌሎች እውነትና ውሸቱን የሚያስተምሩ አሏቸው፡፡ ኦሮሞ ግን በውሸት ትርክቶች ከማንነቱ እየወጣ ለሁሉም ጠላት እየሆነ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ በጣም የከፋ ስግብግብነትና ስብዕና ያጣ በወሮበሎች የሚመራ እየሆነ ነው፡፡ ሰክን ብሎ ሕዝብን መገሰፅ ይቅርና ሕዝብን የአስተሳሰብ ውድቀት ከሚያመቱ ንግግር መታቀብ አልተፈለገም፡፡

በዚህ ቪዲዮ የኦሮሞው ተወካይ እንደምትመለከተለው የሌለ ትርክት ሲያወሩ ተመልከቱ ፡፡ ከሚኒሊክ በፊት ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸው መንግስትና ባንዲራ ነበራቸው ይሉናል፡፡ እንዲህ ሌለ ትርክት በጥላቻና የበታችነት ስሜት ኖረው ዛሬ ጊዜውን የያዙት ስለመሰላቸው መረን የወጣ ንግግራቸውን በሰፊው እያሰራጩ ነው፡፡ ትውልድን እያጠፉ እንደሆነ ማስተዋል አልቻሉም፡፡ የታላላቅ አባቶቹን ታሪክ አስጥለው ባዶውን የቀረ የባዘነ መሆኑ ሳያንስ ቀጣይ ከሌሎች ጋር ለመኖር የማያስችለው ሁኔታ እየፈጠሩለት ነው፡፡ የኦሮሞው ተናጋሪ ንግግር አስቂኝነቱ ቢያይልም እኔ እየሆነ ያለውን ሳሰብ ግን አያስቅም፡፡ ከዚሁ ተናጋሪ ቀጥሎ በሰከነና በአስተውሎት የሚናገሩትን የሱማሌ ምሁር አድምጡ፡፡ ልዩነቱን ተመልከቱ፡

https://streamable.com/1x5wg

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

1 COMMENT

  1. “ሁሉም ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ ታስፈልገዋለች እንጂ ካልፈለገ ኢትዮጵያ አትፈልገውም” ይላል ሰርፀ ደስታ! እስቲ ጨርቅ ለመጣል ምን ያህል ቀረህ?? ሃገር ማለት ህዝብ ማለት እኮ ነው፣ ሰርፀ! ሁሉም ኢትዮጵያን ካልፈለገ የሃገሩ ስም፣ ባንዲራ፣ ህገ መንግስት ወዘተ ይቀየራሉ እንጂ ህዝቡ እና መሬቱ የትም አይሄዱም። ሰውየዉም ያለው ይሄንኑን ሃቅ ነው። ሃቅ ካልተዋጠልህ ችግሩ አንተው ነህ!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.