ብአዴኖች በጎጥም ሆነ በመንደር ቢታመሱ ስለሆዳቸው እንጂ በአማራ ጉዳይ አይደለም

በብአዴን የውስጥ ችግር ምክንያት አማራው ፈጽሞ ሊበጠበጥ አይገባም። ብአዴኖች በጎጥም ሆነ በመንደር ቢታመሱ ስለሆዳቸው እንጂ በአማራ ጉዳይ አይደለም። ስለዚህ የብአዴኖች መጠበብ ከሆድ አያልፍምና የነሱ ችግር ፈጽሞ የአማራ ችግር ሊደረግ አይገባውም። ብአዴን እንደ በላተኛ ስብስብ የተፈጠረው የአማራን ጉዳይ ቀብሮ በየዘመኑ ቀና የሚሉ አማሮችን እንደ ፋሲካ ዶሮ እያሳረደ ሞግዚት ያደረጉትን ጌቶች ዓላማ ለማሳካት ነው።

ከሰሞኑ በግፍ የታሠሩ የአማራ ልጆችን ለመጠየቅ ወደ ዐቢይ አሕመድ የአማራ ማጎሪያ ጣቢያ ያቀኑ የአማራ ልጆች ሁሉ እንደ በግ ከመንገድ እየተጎተቱ እየታሠሩ ያሉት ያለ ብአዴን/አዴፓ ይሁንታ አይደለም። ክርስቲያን ታደለ የተከሠሠው «የአማራ [ክልል] ወጣቶችን ታስታጥቃለህ» ተብሎ ነው። መቼም ብአዴን በሚያስተዳድረው «የአማራ ክልል» ውስጥ ክርስቲያን ታደለን «የአማራ [ክልል] ወጣቶችን ታስታጥቃለህ» ብሎ የሚከስ ከብአዴን ውጭ ያለ አካል አለ ብሎ ራሱን የሚያሞኝ የዋህ ያለ አይመስለኝም። ባጭሩ ክርስቲያን ታደለ የታሠረውና የተከሠሠው በብአዴን/አዴፓ ነው።

የአማራ ድርጅታዊ ችግሮች ሊሆኑ የሚችሉት የአማራ ፍዳና መከራ አምጦ የወለዳቸው የቀድሞውን መዐሕድንና የአሁኑን አብንን ያጋጠሟቸውና እያጋሟቸው ያሉ ችግሮች ብቻ ናቸው። ተወደደም ተጠላም የአማራ የሕልውና አደጋ አምጦ የወለዳቸው ድርጅቶች ቢኖሩ የእጀ መድኀኒቱ ሐኪም የፕሮፌሰር ዐሥራት ወልደየስ ድርጅት መዐሕድና የአማራ የህልውና ተጋድሎ ውጤት የሆነው አብን ብቻ ናቸው። የበላተኞች ድርጅት ብአዴን የሚታወክበትን የጎጥም ሆነ የመንደር ሽኩቻ የአማራ ችግር አድርገው የሚያላዝኑ አራሙቻዎች ቢኖሩ የመብሉ ተክፋዮች የሆኑት የብአዴን የቀድሞና አዳዲስ ካድሬዎች እንዲሁም በአማራው ላይ የተጋረጠው የኅልውና አደጋ ምን እንደሆነ ጥደው ቢያበስሏቸው የማይሰማቸው የአሞራ ስጋዎች ብቻ ናቸው።

ይኼው ነው!

አቻምየለህ ታምሩ

1 COMMENT

  1. አርቆ ወርዋሪው አቻምየለህ ታምሩ ተናግሯል ጆሮ ያለህ ስማ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ተበዳይ ወገን ስለተዞረበት ማሰብ ተስኖታል አማራው ለጥፋቱ ሌት ተቀን ለሚሰሩት እንደ ኢሳት ላሉት ሚዲያ አንስቶ ሀያ ሚልዮን ይሸልማል ዋናው ያማራ ጠላት በግዛቱ ሲመጣ እንደዛ በሚያዋርድ ተዋራጅነት አቀባበል ያደርጋል። ትግሬ የጠየቀውን መሬት ያህል ሸልሞታል ታድያ አቻም የለህ ብአዴንን መምከሩ ምን ስህተት አለው? እነሱ ለምክር አልታዱሉም እንጅ አቦ ብእርህና አእምሮህ ይሳል ተመችተኸኛል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.