ኢንጂነር ታከለ ኡማ ያልመረጣቸውን ሕዝብ ለሌላ አንድ አመት እንዲያስተዳድሩ ተወሰነ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ ለሚቀጥለው አመት በምክትል ከንቲባነት ማእረግ ፣ ያልመረጣቸውን የአዲስ አበባ ሕዝብ እንዲያስተዳድሩ ፓርላማው ወሰነ። የባላደራው ምክር ቤት ሊቀመንበር፣ ጋዜጠኛና አክቲቪስት ፣ እስክንድር ነጋ” አቶ ታከለ ኡማ  ለአንድ አመት እንዲሰሩ ነው የተመደቡት፣ አመት ስለሆናቸው ሕግ ወጥ ናቸው” የሚል አስተያየት ሰጥተው የነበረ ሲሆን፣  በፓርላማው አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ እንዲራዘም ተወስኗል።

በሁለቱ ከተሞች ምርጫ መራዘም ዙሪያ ቢቢሲ የሚከተለውን ዘግቧል

የአዲስ አበባና እና የድሬዳዋ ምክር ቤቶች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባደረገው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ወስኗል።

ወደ 2011 ዓ.ም እንዲራዘም የተደረገውን የሁለቱን ምክር ቤቶች ምርጫ በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማካሄድ እንደማይችል ምርጫ ቦርድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 4/2011ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ የሁለቱን ምክር ቤት ምርጫ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ማካሄድ እንደማይቻል ጠቅሷል።

ለዚህም እንደ ምክንያትነት ያቀረበው ምርጫ አስፈፃሚዎችን ለመመልመል፣ ለማደራጀት እና ለስልጠና የቀረው የዓመቱ ጊዜ አጭር በመሆኑ ነው። በውሳኔውም መሰረት በሥራ ላይ ያሉት ምክር ቤቶች ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ሥራቸውን እያከናወኑ ይቀጥላሉ።

በ2010 መካሄድ የነበረበት የሁለቱ ምክር ቤቶች ምርጫ ሃገሪቱ ውስጥ በነበረው አለመረጋጋትን ተከትሎ በዚህ ዓመት እንዲካሄድ መራዘሙ የሚታወስ ነው።

ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ በሃገሪቱ ከሚካሄዱ ብሔራዊ ምርጫዎች ጋር የሚካሄድ የነበረ ሲሆን፤ አወዛጋቢውን የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ ከተማዋ በባለአደራ አስተዳደር ስር ቆይታ ምርጫ በመደረጉ የምርጫው ጊዜ ከሌሎቹ ክልሎች የተለየ እንዲሆን ምክንያት ሆኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.