ሶስቱ የአማራ ነቀርሳዎች – አቻሜለህ ታምሩ

ሶስቱ የአማራ ነቀርሳዎች

እነዚህ የምትመለክቷቸው ሶስት የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ቤተኞች መላው አማራ አልቆ ቢያድር የማይበርዳቸውና የማይሞቃቸው የአማራ ነቀርሳዎች ናቸው። ሶስቱም የዐቢይ አሕመድን ተልዕኮ ለመፈጸም እንወክለዋለን የሚሉትን አማራ ሸጠው የበሉ ይሁዳዎች ናቸው።

ዳግማዊት ሞገስ የታከለ ኡማ የስልጣን ተጋሪ ሆና ምክትል ከንቲባ ተደርጋ ተሹማ ነበር። ታከለ ኡማ ኦሕዴድን ወክሎ በአዲሱ አረጋ ቋንቋ «የኦሮምያን ልዩ ተጠቃሚነት በአዲስ አበባ ለማስጠበቅ» የከተማውን ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ከሕወሓት ዘመን በከፋና በፈጠነ መልኩ በአንድ ዘውግ ሰዎች ሲሞላው፣ ከአዲስ አበባ ኗሪዎች መካከል የአማራ ማንነት ያላቸው እየታዬ ቤታቸው ሲፈርስ፣ ስራ አጥ የአዲስ አበባ ወጣቶች ተቀምጠው የኦሮሞን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከከተማ አስተዳደሩ ውጪ የመጡ ወጣቶች መታወቂያ እየታደላቸው በጥቃቅንና አነስተኛ ሲደራጁና ሌሎች ወንጀሎች በከተማ አስተዳደሩ ሲሰሩ ብአዴንን ወክላ ምክትል ከንቲባ የሆነችው ዳግማዊት ግን በእነ ታከለ ልክ እወክለዋለሁ ለምትለው አማራ ልትሰራ ይቅርና እነ ታከለ የሚፈጽሙትን ወንጀል «ሚስጥር ነው» እያለች ደብቃ መያዝን ዋና ስራዋ ያደረገች ጉድ ነበረች።

በአለም ባንክ ጥናት መሰረት ከኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ የመጨረሻ ድሀና በመንገድ፣ በውሀ፣ በኤሌክትሪክና በሌሎች የኢኮኖሚና ማኅበራዊት መሰረተ ልማቶች ጭራ መሆኑ የተነገረለት ብአዴን የሚገዘግዘው የአማራ ክልል የሚባለው የሕወሓት የጠላት ቀጠና ነው። ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከመሆኗ በፊት በመጨረሻው የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ ዘመን
በአገዛዙ ሊተገበሩ ከተያዙ 41 የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል ሁለቱ ብቻ አማራ ክልል ለሚባለው እንደተመደበለት ተነግሮን ነበር።

በዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖር ሚኒስቴርነት ዘመን ዘንድሮ ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተያዙ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ዝቅተኛ የመንገድ ሽፋን ላለው የአማራ ክልል ለሚባለው አካባቢ የተያዘለት አንድ ፕሮጀክት ብቻ ነው። ለማ መገርሳ በየትም እርከን ላይ ብንመደብ የምንሰራው ኦሮሞን ወክለን ነው ብሎ ነበር። በኦሕዴድ/ኦነግ ዘመን አማራን ወክላ የትራንስፖርት ሚኒስትር የሆነችዋ ዳግማዊት ሞገስ ግን ሚኒስቴር ሆና በተሾመችበት ዘመን በመንገድ መሰረተ ልማት ጭራ ለሆነው የአማራ ክልል ለሚባለው አካባቢ ፋሽስት ወያኔ እንኳ ይመድብለት ከነበረው ሁለት ፕሮጀክቶች አንዱን ቀንሳ ኦሮምያ ክልል ወደሚባለው የኦሕዴድ ኦነግ ግዛት አዛውራዋለች።

የብአዴን አማሮች አማራን ጠላት ያደረጉት ኃይሎች ለፍላጎታቸው ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ አማራ ክልል በሚባለው አካባቢ የተከሏቸውን የልማት አውታሮች ሳይቀር ሎሌ ላደረጋቸው የአማራ ጠላት ነቅለው የሚሰጡ ጉዶች ናቸው። አዲሱ ለገሰ የሚባለው የአማራ ባለደም «አማራ ክልል» የሚባለው አካባቢ ፕሬዝደንት ሳለ የነበሩ የልማት መዋቅሮችን አስነቅሎ ወደ ትግራይ እንዲጓዙ ያደረገው በኢትዮጵያ መንግሥት የተሰሩትን ብቻ ሳይሆን የፋሽስት ወያኔ የመንፈስ አባት የሆነው ፋሽስት ጥሊያን በጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋና ጎንደር የሰራቸውን የልማት መዋቅሮች ጭምር ነው። የአዲሱ የመንፈስ ልጅ ዳግማዊትም እነሆ የአማራን ጠላት ያደረገው ፋሽስት ወያኔ የአማራ ክልል ለሚባለው አካባቢ ይፈቅድለት ከነበራቸው ሁለት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱን ቀንሳ ጌቶቿ ለሚገዙት የኦሕዴድ/ኦነግ ክልል ሰጥታለች። የብአዴን አማሮች እንዲህ ናቸው! የብአዴን ወኪሎች እንወክለዋለን ከሚሉት ከአማራ ጉዳይ ይልቅ ሎሌ ላደረጋቸው ጌቶቻቸው ማደር ይበልጥባቸዋል።

ሌለኛው የአማራ ነቀርሳ ንጉሡ ጥላሁን የሚባለው የዐቢይ አሕመድ አፈቀላጤ ነው። ስለዚህ ጉድ ባለፉት ዓመታት የጻፍሁትን ወደኋላ መለስ ብሎ ማየት ይቻላል።

ሶስተኛው የአማራ ነቀርሳ ብናልፍ አንዷለም የሚባለው በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ ተደርጎ የተጎለተው ጉድ ነው። የብአዴን የማዕከላዊ ኮምቴ አባል የሆነው ብናልፍ አንዷለም «ነጻ ያወጡን ሕወሓቶች አይደለም ወልቃይትና ጠገዴን የተወለድሁበትን ጎጃም ደጋ ዳሞትን እንኳ ቢወስዱ ሲያንሳቸው ነው» ብሎ የሚያምንና «ሕወሓት በሕዝባዊ አመጽም ሆነ ሆነ በትጥቅ ትግል ከስልጣኑ ቢወገድ፤ ሕወሓትን መልሼ ወደ ሥልጣን ለማምጣት አብሬያቸው ደደቢት እንደገና እወርዳለሁ» የሚል ወደር የማይገኝለት ባንዳ ነው። የብናልፍ አንዷለም የሙሉ ጊዜ ስራ ወይም በዐቢይ አሕመድ የተሰጠው ተልዕኮ የአማራውን እንቅስቃሴ ማክሰምና የኦሕዴድ/ኦነግ ቅጣ ያጣ የበላይነት ማንበር ነው።

ብናልፍ ከሁለት ሳምንት በፊት ባሕር ዳር ውስጥ በሚስጥር ያሰለጥናቸው ለነበሩ የብአዴን ካድሬዎች «ፌዴራል መንግሥት ከብአዴን የሚጠብቀው የፖለቲካ ተግባር ከምርጫው በኋላ እንደ ኢሕአዴግ መንግሥት ለመሆን አብንን ከጥቅም ውጭ አድርገን ማጥፋትና በአማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረው መስራት ነው» ሲል ስምሪት ሰጥቷል። ኦሮምያ በሚባለው ክልል ኦነግ ማደፋፈሪያ ስለተሰጠውና የዐቢይ ፓርቲ ምናልባትም ሊሸነፍ ስለሚችል ኦሕዴድ መንግሥት መሆን የሚችለው ብአዴን የአማራን ድርሻ ከአብን እንዲጫረት በማድረግ ብቻ ነው። ብናልፍ በአሁኑ ወቅት እየሰራ ያለው ይህንን የዐቢይ አሕመድ ፕሮጀክት ነው።

8 COMMENTS

 1. The main enemies of the Amahara people are the ultranationalist Achamyele Tamiru, the Milisha Dawit Woldegiogies and the abnormal Eskinder Nega. They had erfulled their wishes by campaigning for the assassination of Abachew, Ezazi and Migbaru and supporting it. Now the blood of these gentlemen om their hands.

  Now they have started the same campaigning against the above mentioned 3 persons.

  Achamyele don’t worry, you will face soon justice.

 2. ዝምብለህ በደመ ነፍስ የምትነዳ ፀሀፊ ነህ:: ትንሽ ቆም ብለህ ብታገናዝብ ሰዎችን ጥላሸት ከመቀባትህ በፊት ለምትፅፈው ሀላፊነት መሸከም የማትችል ቀሽም ነህ:: አንተ ለአማራ የበለጠ የምትጨነቅ መሆንህን በዬትኛው ምርጫ የአማራ ህዝብ ድምፅ ሰጠህ? ትናትናም ያንተ ቢጤዎች ናቸው ደመቀ መኮንን ለሱዳን የአማራን መሬት ሸጠ ብላችሁ ስታናፉ የነበረው:: አማራውን እየገዘገዛችሁ መሪ አልባ ህዝብ እያደረጋችሁት ነው:: ከኦሮሞዎች ጋር ለመደበሪያ የምታድርገውን ብሽሽቅ እዚያው ጨርሰው:: ለህዝብ ተግተው የሚሰሩትን ጭቃ ከመቀባት አንተ እራስህ ምን የሚረባ ነገር ለአማራ ሰራህ?

 3. እንግዲህ ቢቆጠቁጥም አቻምየለህ ተናግሯል ዝም ብለህ መስማት ነው እሱ እንደ እናንተ አቶ ህዝቅኡል ሰማሁ ሳይሆን ሰነድ አስደግፎ ነው። ባይሆን ከድንቁርና በመፈወሱ ምስጋና ይገባዋል እንጅ ኢትዮጵያዊ ባልሆነ ስነምግባር ይስተናገዳል? ግለሰቡ የእውቀትና የማገናዘብ ደሀ አይደለም በነካኸው መጠን ምርምሩ ይቀጥላል በሗላ የሚያስጥልህ የለም ውርድ ከራስ። ደመቀና አለም ይገባኛል ተጎድታችሗል በጽሁፉ የእናንተ ጥፋት አይደለም የወከሏችሁ ሰዎች እንጅ ።
  ባይሆን የጻፈውን ደጋግሞ ማየት ነው እንጅ መልካም ዜጎችን እያነሱ ማብጠልጠል ምን የሚሉት ባንዳነት ነው? እንማርበት መድረኩን አታቆሺሹት።ግርማ፣ሰርጸ፣አቻምየለህ በህዝብ ጸሎት የቆሙትን ሰማእታት እንዲህ መነካካት ቅስፈትና የኦነግን ድርጅት መቅኖ የሚያሳጣ ያልታሰበበት የዘለፋ አስተያየት መሰለኝ ለማንኛዋም ድከም ብሎኝ እንጅ የምታስበው በተሰጠህ ልክ ነው።

 4. ግርማ ሠርጸ አቻምየለህ ጨለማውን የሚያበሩ የሕዝብ ልጆች በርቱ

 5. ወንድወሰን፦ አቅመቢስ አንባቢ ሁሉን ነገር በዘር መነጽር ይመለከታል ፣ ውሻ ካላጥንት ድመትም ካለወተት እንደማይታያቸው ሁሉ። ዘመዶችህ የካሮትን ዋጋ ቢሰቅሉትም ትንሽ ግዛና ብላ፣ ዐይንህ ቢጠራልህ፣

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.