ኤጄቶ ኦነግ ነው፤ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ግንኙነት የለውም! (አቶ መኮንን ዶያሞ)

ኢትዮጵያን ለማዳን የሚፈልግ ሰው አማራ የጀመረውን ትግል መደገፍና አጋርነቱን ማሳየት አለበት። የሲዳማ ህዝብ አጋርነቱን ለማሳየት ዝግጁ ነው፤ የወላይታ ዝህብም አጋርነቱን እንደገለፀ መረጃው አለኝ፤ የጋሞጎፋ ህዝብ ለአማራ ህዝብ ያለው ድጋፍ የተለየ ነው፤ የከፋውም የጉራጌውም እንዲሁ! አሁንም ቢሆን ከአማራ ጎን ተሰልፈን ነው ኢትዮጵያን ማዳን የምንፈልገው። አማራ ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ጣሊያን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከነደፈው ስትራቴጂ የተቀዱ ናቸው፤ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለማጥፋት አማራን ማጥፋት የሚል አቋም ነበረው፤ ዛሬም ኢትዬጵያን ለማፍረስ የሚሞክሩ ሃይሎች የጣሊያንን አካሄድ ነው የኮረጁት። ኢትዮጵያን ለማዳን አማራን ማዳን ይገባል፤ ምክንያቱም አማራ ላይ የሚያነጣጥር ጥቃት በመላው ሃገሪቱ ተሰራጭቶ የሚኖረውን ከተማ መስራችና የስልጣኔ ምንጭ የሆነውን ህዝብ ለማጥፋት ስለሆነ ነው። እኔ ጫካ ውስጥ ነው የተወለድኩት፤ ከጫካ ወጥተን ከተማ ውስጥ መኖር የጀመርነው፣ ሀ ሁ ተምረን ማንበብና መፃፍ የጀመርነው፣ .. ሃገር መስራቹ የአማራ ህዝብ በመሰረተው ከተማ ውስጥ ነው፤ ዛሬ ካሉት ከተማዎች ውስጥ አማራ ያልመሰረታቸው ከተሞች የሉም። የአማራ ህዝብ ቁጥር አሁን የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራው ክልል ውስጥ ከሚኖረው የአማራ ቁጥር ይበልጣል፤ ይህም ብቻ አይደለም አጠቃላይ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ከአማራ ክልል ውጪ ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ቁጥርም ያንሳል።

ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ይበልጣል ተብሎ እንዲታሰብ የተደረገው የወያኔ ስራ ሲሆን ፈፅሞ ውሽት ነው፤ ሸዋ ውስጥ ስንመጣ የምናገኘው ሰላሌ ብቻ ነበር። ወሎ ስንሄድ አንድ ወረዳ ነበር፤ ከዛ ውጪ በመላ ሃገሪቱ ብንመለከት የአማራ ህዝብ በየከተማ በየገጠሩ majority ነው። ለምን የኦሮምያ ክልል እንደሚባል አላውቅም፤ ኦሮምያ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ብናይ እኮ ናዝሬት ብዙሃኑ አማራ ነው፤ ደብረ ዘይት አማራ ነው፤ ወለጋን ብናይ የጃም ክፍለ ሃገር አካል የነበረ ነው፤ አርሲና ባሌ አብዛኛው ነዋሪ አማራና ሰፊው ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው የሚኖርበት፤ ይህ ክልል በፍፁም የኦሮምያ ክልል መባል የለበትም ነበር።#ኤጄቶ የሚባለው ቡድን ከሲዳማ ህዝብና ባህል ውጪ ነው፤ ኦነግ ሲዳማን ለመጠቅለል ሲፈልግ ያሰለጠነው ጋጠወጥ ቡድን ነው፤ እቅዱ የኦነግን ፀረ አማራ እንቅስቃሴ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ለማነካካት ነበር፤ የተፈጠረውን ችግርም ስንመለከት በአብዛኛው አማራንና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ኢላማ ውስጥ ያስገባ ነው፤ ግን የሲዳማ ህዝብ አልተባበረም፤ ምክንያቱም የሲዳማ ህዝብ ከአማራ ህዝብ ጋር ቤተሰብ ነን ብሎ ስለሚያስብ ነው። #Ejetto የሲዳምኛ ቃል አይደለም፤ በሲዳምኛ ትክክለኛ ቃሉ አጋቶ ሲሆን ትክክለኛ ስሙም #መርገጫ ማለት ነው። ይህ ቡድን ከስሙ ጀምሮ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።

9 COMMENTS

 1. ይህን ደነዝ ደግሞ ከዬት አገኛችሁት?? ምነው ጤነኛ ምሁር አለቀባችሁ?? ገንዘብ ሰጥታችሁ ቢታስለፈልፉትና ህዝብን ቢታሰድቡ ዕዉነት አይቀይር!! የከሰራችሁ!

 2. ኣይመጥነንም ሆነ ወይ በፍራቻ ዳር ቆማችሁ የምትታዘቡ የየክልሉ ምሁራን ወደ ፊት መውጣታችሁ እዚህም እዚያ እየታዬ ስለሆነ የሚበራታታ ነው ።በርቱ ።ሀገራችን ኣይናችን እያየ ቅጥረኛ ከሀዲ ምሁራን ተብዬዋች እርስ በርስ ሊያባሉን ቀን ቀሌት ሲተጉ ዝም ልንላቸው ኣይገባም። እውነተኛ የህዝብ ሙህራን ጊዜው ሳይመሽ ሀላፊነታችሁን ተወጡ፣ የባዶ በርሜል ጩኽት ኣያስደግጣችሁ ።
  ወጣቱን ኣስተምሩት !!
  እናንተ ወደ ከፍታ ስትወጡ ፣ እነርሱ ደግሞ የኣፍረት ማቅ ለብሰው ወደ ታች ይወርዳሉ።Time will tell.
  ምስጋናዬ ይድረስዎት፣ ቀጣይ ጽሁፎን እጠብቃለሁ።
  ኣባ ጫላ ኣይን ይብላህ !

 3. የኢትዮጵያን ህዝብ ለዚህ አይነት ውጥንቅጥ የዳረገው እንዲህ አይነት እኔ እበልጣለሁ የሚል አስተሳሰብ ነወ። እባካችሁ ስንናገርም ሆነ ስንጽፍ ኃላፊነት ይሰማን እንዲህ በስሜት መነዳት አይበጀንም።

 4. This stupid writer graduate cummerntly from the school of Demteralog (destroying facts).

  Those mentally retarded and culturally corrupted individuals like the this writer cannot understand true democracy. They cannot adjust their mentalities with the principles of win win approaches.  They are just human INBOCH and parasites like tapeworms! 

 5. This mentally slave guy is one of those who grew up and shaped with the self denial behaviors. The theory of this guy cannot change historical facts. He is lmentally slave like his brother  the so called Larebo. Anti-unity and toxic are those like them and their mentors like Getachew Haile. They don’t believe in unity with diversity.

  One of his mentors Befekadu Degefe has mentioned some months ago in his statement at the conference of the Amhara elites in Bahir Dar about some kids from southern Ethiopia go to school to become Amhara. Most probably his reference is Larebo and Efrem Madebo, and this guy. 

  Befakadu Degefe is an economist by training. But still he thinks with his Debteric mentality. He said shamefull Amaharaism is spirit. The main burden of Ethiopia is such poor individuals with backward and uncivilized mentalities

  No one knows better than Befekadu Degefe how the life hard is in his birth place for the ordinary families. In general, the people from Wallo, Gojam and Gonder were misused by the greedy Neftengas of Shewa during the eras of Menilik, Haile Selasien and Mengistu who promoted their objectives  in the name of those innocent human beings. Thus, don’t forget that your families having been still suffering a lot as Walloye, Gojames and Gonderes under those inhuma systems of that empire state. From all these systems you have inherited only pseudo prides, bad mentality and cultures under which you are still in custody. 

 6. ሰውየው ከመነሻው ስሜት አዘል አስተያየት ስለመስጠቱ የጠላውን ጨፈላልቆ የወደደውን ለመካብ የዳዳው ፅሁፉ ይገልጣል ፡፡ የጠቀሳቸው ቦታዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ ብዙ አማራዎች ይኖራሉ ፤ ነገር ግን ምሁሩ መኮንን ዶያሞ ያልነገረን/ ያልሰማው / ምን ያህሉ የህብረተሰብ ክፍል ነው በሀገራችን ውስጥ የከተማ ነዋሪ ? እነዚህንስ ቢሆን በትክክል ቆጠራ አካሂዶ ነው እከሌ ይበዛል እከሌ ያንሳል ብሎ ያለው ? ተቆጥሮ የተሰነደን ሰነድ ውድቅ ለማድረግ ሌላ ቆጠራ ስለማስፈለጉ ምሁሩ እንዴት መረዳት አቃታቸው ? እንደ ድሮው እንደ ጥንቱ ግምታዊ ሂስ እየሰጡ ምሁር መባል አይከብድም ? ይልቅስ ከእርስዎ እንጠብቅ የነበረው ፤ ቀደም ሲል የነበረው የህዝብ ቆጠራ ይሄ ይሄ ችግሮች ነበሩበት ፤ አሁን በቀጣይ የሚደረገው ቆጠራ ግን በዚህ በዚህ መንገድ በንፅህና ተሰርቶ ትክክለኛ የህዝብ ቁጥር መገለፅ አለበት ፤ እያሉ አሳማኝና ምክንያታዊ አስተያየቶችን መስጠት ነበረብዎ ብዬ አስባለሁ ፡፡

 7. This mentally slave guy is one of those who grew up and shaped with the self denial behaviors. The theory of this guy cannot change historical facts. He is lmentally slave like his brother  the so called Larebo. Anti-unity and toxic are those like them and their mentors like Getachew Haile. They don’t believe in unity with diversity.

  One of his mentors Befekadu Degefe has mentioned some months ago in his statement at the conference of the Amhara elites in Bahir Dar about some kids from southern Ethiopia go to school to become Amhara. Most probably his reference is Larebo and Efrem Madebo, and this guy. 

  Befakadu Degefe is an economist by training. But still he thinks with his Debteric mentality. He said shamefull Amaharaism is spirit. The main burden of Ethiopia is such poor individuals with backward and uncivilized mentalities

  No one knows better than Befekadu Degefe how the life hard is in his birth place for the ordinary families. In general, the people from Wallo, Gojam and Gonder were misused by the greedy Neftengas of Shewa during the eras of Menilik, Haile Selasien and Mengistu who promoted their objectives  in the name of those innocent human beings. Thus, don’t forget that your families having been still suffering a lot as Walloye, Gojames and Gonderes under those inhuma systems of that empire state. From all these systems you have inherited only pseudo prides, bad mentality and cultures under which you are still in custody. 

 8. አሸናፊ ከበላይ፣ አንተ ተከፍሎህ ነው ጥያቄ የምትጠይቀው? ህሊና የሚባል ነገር የለህም? ሁለቴ የተደረጉትን የህዝብ ቆጠራ ከምንም ሳይቆጥር የራሱን ግምት የሚለፍፍ፣ በማይመለከተው ገብቶ የሌሎችን ዐላማ የሚያራምድ ቅጥረኛ እንጂ ታዲያ ምሁር ሊባል ነውን??

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.