ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝግብ ያቀረበውን የ14 ቀናት ጥያቄ ውድቅ አደረገ

የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 13 ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው መርማሪ ፖሊስ በእነ ብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝግብ ያቀረበውን የ14 ቀናት ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

ሰኔ 15 ቀን 2011 በባህር ዳር ከተማ በክልሉ የስራ ሃላፊዎች እና በፌደራል መከላከያ ሰራዊት የስራ ሃላፊዎች ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር በተያያዘ መርማሪ ፖሊስ በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ላይ የ28 የቃል ምስክሮችን፣ የቴክኒክ እና የሰነድ ማስረጃዎችን አሰባስቦ ለፍድር ቤቱ አቅርቧል።

ሌሎች የቃል ምስክሮችን፣ የቴክኒክና የሰነድ ማስረጃዎችን እንዲሁም የፎረንሲክ እና የኢትዮ ቴሌኮም የስልክ መረጃዎን ለማሰባሰብ የ14 ቀናት የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ከላይ የተጠቀሱት 28 የቃል ምስክሮች የቴክኒክና የሰነድ መስረጃዎች በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረቡ እንጂ በእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝገብ ላይ ያለመቅረባቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል።

የተጠየቀው የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርማራ ጊዜም ምንም መረጃ ባለተያዘበት ሁኔታ ደንበኞቻችን የሚጉላላ ነው ብለዋል።

ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ማርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ ምርማራ ጊዜ አሳማኝ አለመሆኑን በመግለጽ ከልክሏል፡፡

እስከ ነሃሴ 13 ቀን 2011 ድረስም ክስ እንዲሰመርት ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ/ (ኤፍ.ቢ.ሲ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.