ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል በርስዎ በራስዎ ጥናት መሰረት እንኳን የጥንቱ ቤተ አማራ (የዛሬው ወሎ) እርስዎ የተወለዱበት ወለጋም የኦሮሞ አይደለም! (አቻሜለህ ታምሩ)

ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጊቢሳ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የሚሊንዬም አዳራሽ ወሎን በሚመለከት ባደረጉት ዲስኩር የተለመደውን የኦነግን የፈጠራ ትርክት በማስተጋባት ወሎን የኦሮሞ ምድር አድርገው አቅርበዋል፤ አባ ገዳ ሆነው ወደ ወሎ የሚደረገውን ወረራ ለመምራት እንደተዘጋጁ በሚመስል መልኩም የጦርነት ነጋሪት ጎስመዋል። ሰውዬው ገራሚ ሰው ናቸው!

እውነቱ ግን በታሪክ እንኳን የጥንቱ ቤተ አማራ የዛሬው የወሎ ምድር ይቅርና እሳቸው የተወለዱበት ወለጋም ከኦሮሞ መስፋፋበት በፊት የኦሮሞ አልነበረም። ወለጋ የጥንት ስሙ ቢዛሞ ሲሆን ኦሮሞ ነባር ብሔረሰቦችን አጥፎቶ እንደ ዋርካ የተስፋፋበት ምድር ነው። ይህንን እውነት የሚነግረን ደግሞ ኦነጋውያን ደብታራ የሚሉት የታሪክ ጸሐፊ ሳይሆን ራሳቸው ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጊቢሳ ናቸው።

ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጊቢሳ በ1977 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ሲያጠናቅቁ ያቀረቡት የጥናት ወረቀት ርዕስ “From Animosity to Mutual Understanding: Oromo Relations with the Gumuz of the Didessa Valley” ይሰኛል።

ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል በዚህ የዲግሪ ማሟያ ጥናታቸው ውስጥ ኦሮሞ ወደ ወለጋ ከመምጣቱ በፊት ማኦ፣ ሳኢና ገበጣ የሚባሉ የኢትዮጵያ ነገዶች በጥንቱ ቢዛሞ በዛሬው ወለጋ ምድር ተስፋፍተው ይኖሩበት እንደነበር፤ ኦሮሞ ወለጋን ሲወር ግን እነዚህን ነባር የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች አጥፎቶና ወደ ዴዴሳ ሸለቆ ገፍቶ በማባረር በቢዛሞ ምድር እንደ ዋርካ እንደተስፋፋ ከኦሮሞ አፈ ታሪክ ጭምር አገኘሁት ያሉትን ማስረጃ በማከል ከኦሮሞ ወረራ በፊት የነበሩትን የወለጋ ነባር ነገዶች ታሪክ በጥናታቸው አቅርበዋል።

እንግዲህ! ፕሮፌሰር ሕዝኤል ራሳቸው ለዲግሪ ማሟያ ባጠኑት ጥናት መሰረት የዛሬው ወለጋ ኦሮሞ አካባቢውን ሊወር ከመምጣቱ በፊት ማኦ፣ ሳኢና ገበጣ የተባሉ በመላ ወለጋ ተሰራጭተው ይኖሩ የነበሩበት ምድር እንደነበርና ኦሮሞ እንደ ዋርካ በወለጋ የተንሰራፋው የወለጋን ነባር ብሄረሰቦች አጥፍቶና መሬታቸውን በወረራ ወስዶ መሆኑን የነገሩንን የራሳቸውን ጥናት ባፍጢሙ ደፍተው ነው እንግዲህ ዛሬ ደግሞ ሌላ ትርክት የሚነግሩን።

ባለፈው ጊዜ ለዶክተር ነጋሶ በሰጠሁት መልስ ውስጥ በሳቸው ጥናት መሰረት ኦሮሞ ወለጋን በመውረር ከዋጣቸው ነገዶች መካከል አንዱ የሆነው አማራ ሲሆን ይህ የአማራ ክፍል የሆነው ነገድ በኦሮሞ ከተዋጠ በኋላ ስሙ ቅጥያ ወጥቶለው መጠሪያው አማራ ካንቺ እንደሆነና ይህ አማራ ካንቺ የተባለው የጥንት የወለጋ አማራ ዛሬ ኦሮሞ ሆኖ ዛሬም በወለጋ እንደሚኖር ያወሳሁትን ልብ ይሏል።

ሌላው ገራሚው ነገር ወሎን የኦሮሞ ነው የሚሉን ፕሮፌሰር ሕዝኤል ጊቢሳ ሕገ መንግሥት የተባለውን የወያኔ ፕሮግራም ካላከበራችሁ በሕልውናችን እንደመጣችሁ እንቆጥረዋለን ከሚሉ የኦሮሞ ብሔርተኞች መካከል ቀዳሚው ሰው እሳቸው ራሳቸው መሆናቸው ነው። እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ ካላከበራችሁ በሕልውናችን እንደመጣችሁ እንቆጥረዋለን የሚሉን ሕገ መንግሥት ወሎን የአማራ ምድር [ክልል] እንደሆነ ይደነግጋል።

ጤና ይስጥልኝ ፕሮፌሰር ሕዝኤል ጊቢሳ! ካልተከበረና ካላስከበርነው ሞተን እንገኛለን የምትሉት ሕገ መንግሥት የአማራ ያደረገውን ወሎን «የኦሮሞ ነው» ስትሎ ካልተከበረና ካላስከበርነው ሞተን እንገኛለን የምትሉትን ሕገ መንግሥት መጣስ አይደለምን? ነው ሕገ መንግሥት ተብዮውን እንድናከበር የተፈረደብን እኛ ብቻ ነው? ሕገ መንግሥት ይከበር የሚለው እናንተን አይመለከትም ማለት ነውን? እናንተ ራሳችሁ ካልተከበረና ካላስከበርነው የምትሉትን ሕገ መንግሥት አናት በየአደባባዩ እያፈረሳችሁ ሌላውን በአፍራሽነት የመክሰስ የሞራል ልዕልና እንዴት ሊኖራችሁ ይችላል?!

ሕገ መንግሥት የተባለውን የወያኔ ፕሮግራም ካላከበራችሁ በሕልውናችን እንደመጣችሁ እንቆጥረዋለን የሚሉን ፕሮፌሰር ሕዝኤል ጊቢሳ ካላከበራችሁት የሚሉንን ሕገ መንግሥትና የራሳቸውን ጥናት ባፍጢሙ ደፍተው ወሎን የኦሮሞ ለማድረግ ለወረራ እንደተዘጋጁት ሁሉ ለዲግሪ ማሟያነት የጻፉትን ወረቀታቸውን ዋቢ በማድረግ ወለጋ ከኦሮሞ መስፋፋት በፊት ለነበሩትና ኦሮሞ በግፍ መሬታቸውን በወረራ ለቀማቸው ለለማኦ፣ ለሳኢ፣ ለገበጣ፣ ወዘተ ነገዶች ይመለስ ዘንድ በመከራከር የመርህ ሰው መሆናቸውን ማስመስከር አለባቸው።

16 COMMENTS

 1. ይህን የከሰረ ፣ ቅጥረኛ እና ለራሱ ክብር የሌለው በጫት የናወዘን ሙህር ተበዬ እግር ከግር ተከታትሎ ማጋለጥ ተገቢ ነው።
  Thank you Achameleh

 2. አቻም የለህ የታሪክ ጥናት ላይ እንዴት ነህ? እንዲያው በደመነፍስ ነው እንዴ የምትፈራገጠው ወዳጄ?

  በቅድሚያ በአንድ ነገር እንግባባ በኢትዮጵያዊነት ፤ ዳሩ እናንተ ለዚህ ዝግጁ አይደላችሁም ፤በቅርቡ የሆነውም ለዚህ ማሳያ ነው ለካ ፤ እኛ ስለኢትዮጵያዊነት ስንዘምር እናንተ ግን እጥፍ ብላችሁ ደራ ግዛቴ በረራ ሕይወቴ ዓይነት ዘፈን ከማላዘንም በላይ ያው የፈረደበትን 1ሜ ስፋት በ2ሜትር ርዝመት ያለው ባነር አሸክማችሁ የመሬት ወረራ ናፍቆት ዘመቻ ወጣችሁ ምንም እንኳ ሁሉ እንደፈቃዳችሁ ባይሆንም ስለዚህ ኢትዮጵያዊነትን እናንተ እንደ ጭንብል እንጂ እንደ ማንነት ስለማትቀበሉ ኢትዮጵያዊነት ምላሳችሁ ላይ ቀርታለች ምን አልባት ወደ ልባችሁ እስኪወርድ ጥቂት ታዝጉን ይሆናል።

  ወደ ጉዳዩ ልመለስና አቻምየለህ አንባቢ ትመስለኝ ነበር፤ ለካ በበሬ ወለድ የውሸት ትርክት ተሞልተህ እንደ ናፍጣ ወፍጮ የምትንበቀበቅ ገራሚ ሰው ነህ ፤ ጉድኮ ነው ሰው አፉን አስፍቶ በከፈተ መጠን ውስጠ ነገሩ ተገላልጦ ይታያልና አንተንም እንዲሁ አየንህ ውስጠ ወይራ የመሰልከኝ ሰው የተቀጠቀጠን መቃ (ሸንበቆ)ያህል እንኳ ጥንካሬ የሌለህ ልምሾ መሆንህንም ሳይ አዘንኩልህ ።

  ይሁንና ወሎ ማለት ምን ማለት እንደሁ ታውቀው ይሆን??? ግድ የለም እኔው ልንገርህ አሁን የምድሪቱ እና የህዝቡ (ነገዱ) መጠሪያ የሆነው ይህ ስም ቀድሞ “” ከኦሮሞ ጎሳዎች መካከል የአንድ ንዑስ ጎሣ መጠሪያ ሲሆን አንድም የግለሰብ መጠሪያ ነው”” ። ምንጭ (የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች በታቦር ዋሚ ገጽ 270)

  ወሎ ለአባቱ 2ኛ ልጅ ሲሆን እርሱ ደግሞ 7 ልጆች ወልዷል እኒህ እየበዙና እየተባዙ በአባታቸው ሥም ወሎ ተብለዋል ፤ ብዙ ጊዜ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ አማራዊነትን ጎላ አድርገው ማቀንቀን የሚሹ ወገኖች ታሪክን ከጌታቸው ኃይሌና መሰሎቻቸው ብቻ መቅዳት ስለሚሹ ከችግር ላይ ወድቀው ሲፍገመገሙ እናያለን ጌታቸው ኃይሌ ኦሮሞን በመጥላት ረገድ ተወዳዳሪ የሌላቸው ለመሆን የሚተጉ፥ ብዙ ጊዜም ያልተጻፈ የሚተረጉሙ ገራሚ ተርጓሚም ናቸው ፤ የአባ ባሕርይ ድርሰት ትርጉማቸውን ለጊዜው እንተውና የደቂቀ እስጢፋኖስ ትርጉማቸውን ብናይና በአማን ነጸረ “ወልታ ጽድቅ ” በተሰኘ መጽሐፉ የገላለጠባቸውን ገመናቸውም ስናል ሰውየው አለ አቅማቸው የተርጓሚነት ካባ ለብሰው ወገን ለማሳሳት ከሰይጣን ጋር ውል የተጋቡ ልምሾ ሆነው እናገኛቸዋለን ፤

  ይህንኑ እኩይ ግብራቸውን ታቦር ዋሚ የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች በሚል መጽሐፋቸው ገጽ 251 ላይ እንዲህ ይገልጹታል
  :—- ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ “የአባ ባሕርይ ድርሰቶች ፣ ኦሮሞዎችን ሚመለከቱ ሌልች ድርሰቶች ጋራ “የሚለውን መጽሐፍ ሲያቀርቡ በጥቅሱ ሀተታ ውስጥ እንዲህ ይላል ። ስለ ኦሮሞዎች… የምጽፈው ለሕዝብና ለወጣት የታሪክ ተመራማሪዎች የሀገር ውስጥ ሰነዶችን ለማቅረብ ነው የሚል ስለነበረ በእውነት ጠቃሚ ጉዳዮችን የያዘ ይመስል ነበር ። ነገር ግን ተረጎምኩ በማለት ከ ፕ/ር ታደሰ ታምራት ጋር እየተረዳዱ ያቀረቡት መጽሐፍ ከጤናማ አእምሮ መጠበቅ በማይቻል ደረጃ የዘቀጠና ለዘመናት የገዥዎችን እርኩስ ዓላማ ተቋቁመው በመከባበርና በመፈቃቀር አብረው የኖሩትንና አሁንም በመኖር ላይ የሚገኙትን ሕዝቦች የሚበታትን ነው ። አንዴ የአውሬ ምሥል ፣ በሌላ ቦታ ደግሞ የፈሪ ምሥል በመሣል በአንድ ሕዝብ ላይ ያውም በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጅምላ ፍረጃ የሚያስተላልፍ ምሁር ከፕ/ር ጌታቸውና ከጥቂት መሰሎቻቸው በስተቀር ማግኘት አይቻልም ። ፕ/ር ጌታቸው ምንም ዓይነት ታሪካዊ መረጃዎችን ሣያቀርቡ ተረቶችን ሰብስበው የኦሮሞ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ነው ብለው ከማቅረባቸውም በላይ ለኅሊና የሚቀፉ ተራ ስድቦችንም እንዳለ አቅርበዋል ። ሲሉ ታቦር ዋሚ ይቀጥላሉ ታቦር ዋሚን እጅግ አርገን እናመሰግናለን ፤

  ስለዚህ ይህን ሰው እንደ ምሁር ቆጥራችሁ የእርሱን ተረታ ተረቶች በማመንና ዋቢም በማድረግ የምትጽፉ ቀልጣችኋልና ወደ ልባችሁ ተመለሱ ፤ ሲሆን መጻፍም ካለባችሁ ታሪክን ከእውነተኛው ምንጭ ቅዱ ፤ ጌታቸው ልጡ ተርሶ ጉድጓዱ ተምሦ ዊልቸር ላይ ተቀምጦ እንኳ ያልነቃ ራሱን በንስሃ ያላጠበ እንደቆሸሸ ሞቱን የሚጠባበቅ እንዲህም ሆኖ መንግሥቱ ኃ/ማርያም በጥይት ተደብድቦ መገደል አለበት ብሎ የሚፈርድ ታሪከኛ ሰው ነው ፤ ታድያ ከዚህ ሰው ትውልድ ምን ይማራል?

  አቻምየለህ ሆይ አስተውል ፤ ከቻልክ ኢትዮጵያዊ ሁን አልያም ጭንብልህን አውልቅ ለምድህንም ግፈፍና በአማራነትህ ተሟገት ግን የታሪክ መሠረት ይኑርህ ታሪክ ምን ጥላሸት ብትቀባት እንደ እንቁ እያበራች በጊዜዋ ትገለጣለች ፤ ብዙ ማለት ባልሻም እንኳንስ ወሎ የዛሬ 600 ዓመት ገደማ ስሟ የተለወጠው ደብረ ብርሃን ኢባ እንደምትባል እንኳን እኔ ጌታቸውም አይደብቅህም እዚያው የአባ ባሕርይ ትርክቱ ላይ ጽፎልሃል ኢባ በ አማራኛ ምንም ማለት እንደሆን አንድ ቀን ታብራራልኝ ይሆን?

  እግዚአብሔር ሀገራችንን ይጠብቅልን

  እኛንም በቸር ያቆየን !!!

 3. Achamyeleh,

  You will never behave as an academician.

  The politics of dummy emotion and the history of falsehood will not have place in the future of the Ethiopian political landscapes. The times of the political ideologies of the Debteraists are already over. No more room for nonsense assertion and empty noises.

  You are a subhuman and mentally retarded ane handicapped person. Your usual empty AKAKI SEREF will bring you the final nightmare to you and those like you! Watch out! Before you open your filthy mouth try to settle first your political problems with the Agewo, Qimanti and many others within the regional state of Amahara.

  The main problem is your mentality and the culture in which you grew up. The mentality and the culture of the dark era of Minilik, Haile Selassie and Derg which are still influencing and confusing you. You need redemption. But it is better if you reconcile yourself with the reality of this time. You cannot turn back the wheel of history. The empty akakii zeref will not help you. The ghost of Minilik also cannot help you. It is better if you accept the realities of your time and work on the democratic principles so that you will embrace with dignity and respect the future multinational democratic Ethiopia without suffering under inferiority complex. Don’t forget also you and your ancestors having been suffering a lot as Gojames and Gonderes under those inhuma systems of that empire state. From those systems you have inherited only pseudo prides, bad mentality and cultures under which you are still in custody. I wish that you will become free from that mentality as a good cultured human being.

  Finfinne is the main part of Oromia. Nobody can change it. The debteric essay which you consider as a history can’t change this reality. Therefore, whether you like it or not Finfinne will be ruled under the Oromia regional state. All the residents of Finfinne will have equal rights with the Oromo. Oromo individuals will not have special privileges. All the residents of Finfinne will have equal rights like all the residents of Asela, Adama, Jimma and Goba.

  THE TRUTH SHALL PREVAIL!

 4. እኔ ለአማራ ክልልና ምሁራን የምመከረው ነገረ ቢኖር ከኦነጎች ጋር መዳናቆር አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ይልቅስ ልክ የኦሮሚያ ክልል በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን ስም ነፍጠኞች ስለቀየሩብን በማለት ደብረዘይትን ቢሾፍቱ፤ ናዝሬትን አዳማ፤ ወዘተ በማለት በመመሪያና በፖሊሲ ቀይሯቸዋል፡፡ የእኛ ጉዶች የብአዴን ሰዎች ደግሞ ምን እንደሚሰሩ አይገባኝም፡፡ ስለዚህ የአማራ ክልል መንግስት ወሎና የተለያዩ የአማራ ርዕስቶቸን ወደ ጥንት (በ14ኛውና በ15ኛው ክ/ዘመን) ወደ ነበሩበት የአማራ ስም መቀየር ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ የስም ለውጥ ዛሬ አርሲ ባሌ የሚባሉትንም ሊያጠቃልል ይገባል፡፡ ባለጌ ልኩን ካልነገርከው አናትህ ላይ ነው ላህጩን የሚያዝረከርከው፡፡

 5. እንዲህ ነው አለቃ እየተከታተልክ እንዲህ እርምት ካልሰጠህበት መሬቱን ብቻ ሳይሆን አንተንም ኦሮሞ ያደርጉሀል። ቀደም ባለው ጊዜ እንደ ቀልድ የታለፈውን ተረት ዛሬ ታሪክ አድርገው አቅርበውታል። ፕሮፌሰሩን በተመለከተ ሲናገር የምሁር ባህሪይ ሳይሆን ዱላ የሚከጅለው ከምክንያታዊነት ይልቅ ተረትና ሰማሁ የሚሉትን ትርክት የሚወድ ቄሮ ነገር ነው። አልሆንለት አለ እንጅ ምስክር የተመታ አጠና ተሸክሞ ካደራጃቸው ጀሌዎቹ ጋር ቢደባደብ ብዙም ውብ አይሰጠውም።

  ጥናታዊ ጽሁፉ ጫትን በተመለከተ ሁኖ ለጫት ትልቅ አክብሮት እንዳለው LTV በተባለው ፕሮግራም ቀርቦ ሲያስረዳ ተስተውሏል። ግለሰብ ምሁራዊ ብቃቱ የአሜሪካ ተማሪዎችን ሊያረካ ባለመቻሉ እስከ እውቀቱ ሳይሆን እስከ አስቀደመው ማእረግ ለስራ ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል የትኛው የመንግስት ተቋም ውስጥ በብቃት እንደሚሰራ ማወቅ ይከብዳል ። ጽሁፍ አይሆንሉትም ንግግሩ ተረትና ሰማሁ ነው የተሻለው ነገር የቄሮ ሚኒስተር ተቋቁሞ እሱ የወለጋን የበላይነት ጁዋርና መሀመድ ሀሰን የባሌ እስላማዊ አስተዳደርን ቢያስቀጥሉ ጥሩ ምርጫ ይመስለኛል። በዮሀን ክፍት ትምህርት ታመስን እኮ። ለማንኛውም ማብረጃውን ይስጣቸው ልብ ይስጣቸው ኡይባል ተላልፏቸዋል።

 6. Achamyeleh obviously is incapable of responding intelligibly to Prof. Hizkiel’s statements. So he has resorted to the dirty diversion of name-calling. Probably he is not aware of what libel is. Reading Achamyeleh’s writings I have often wondered what school he attended that produced such an inferior and vindictive mode of thinking. He has identified himself as Amhara and “independent researcher.” But he hardly has what it takes to do research! All that is left if him the Amhara label.

 7. Thanks so much our chatismatic Professor Yiskel for you brought the hidden factual history about the enormous nation of Africa(OROMO) to the world!

 8. The writer of this comment truly deserves for his couragous and powerfully straight – forward criticism with regard to the very crazy but dangerous political and intellectual personality of the so called Professor Ezekiel of OLF and some other dangerously extreme Oromo nationalists who stupidly beleive that they can have greater Oromia by killing Ethiopia and Ethiopiawinet .
  This guy is a guy who badly spoilt his reasoning power and tries to spread his dangerous political poison not only in Oromia but across Ethiopia . His poisonous political personality or mind must not be allowed go without being challenged and rejected with a strong sense of both political and moral concern .
  Those who welcomed and hired him as a professor of a university should know that they are inviting a very horrible poisonous factor that could kill the generation without firing a fire arm and put tha country in a very risk of falling apart . I do not know how it makes sense to those who invited and hired him are okay to go with this kind of killing a generation by poisoning the young generation using education institutions .
  So sad !!!

 9. This guy and his friends have been suffering with the mentality of racism like some of the former white south Africans who grew up in the culture of Apartheid. They write always here and their  an anti-Oromo thesis in order to justify their hatred regarding the Oromo nation and their anti-Oromo sentiments. But it cannot help them. Their “golden” time of discriminating, discrediting and uprooting the Oromo is up. Besides that they also try to promote the political ideologies of the organizations with anti-multinationality programs in order to sustain old thinking and backward political ideologies. 

  They are not ready to accept unity in diversity. They try to preach against the multinational politics by labeling it as “clan politics”  in order to promote their hegemony in Oromia and elsewhere. But the current Ethiopian multinational politics hat nothing to do with a clan politics. None of the Oromo political organization had been promoting about clan politics. They have been promoting the political and human rights of the great Oromo nation.  

  Every small and big ethnic groups in Ethiopia have been still demanding their own self rule against such backward and ever uncivilized mentalities.  Their  persistent stubbornness will help even more as a fuel in strengthening and seeding up the de-Amaharaization of the whole Ethiopian politics in order to substitute it with the politics of a true multinationalism. Watch out! We will have at least the following additional federal languages soon: afaan Oromoo, afaan Sidamaa , afaan Somalee and Tigrenga.

 10. Achamyeleh!!!! U are always write and think what is good for nothing! take urself as u are an insect!!!!u are illiterate!You are going to die tomorrow! think only about this! You are a guest! You have nothing from this earth!

 11. Roman እና ጥሩነህ በመጀመሪያ ደረጃ እንወክለዋለን ለምትሉት ነገድ ተቀራራቢ ስም ብትወስዱ መልካም ነበር እናንተ ያላከበራችሁትን ሌላው እንዲያከብርላችሁ አትፈልጉ።
  አቻምየለህን ለማጣጥልና ሞራል ለመግደል ዳግም እንዳይጽፍ የምታደርጉት የሞኝ ብልጠት አቻምየለህን በጣም ያስቀዋል እንደውም በውጊያው ይጠነክርበታል ግለሰቡ የእውቀት ደሀ አይደለም አንድ ለብዙ ነው።
  በተረፈ ህብር ራዲዮ ኢትዮጵያዊውን አቻምየለህን ኩሻዊዉን አቶ ህዝቅኤል ጋቢሳን አቅርቦ ስላወያየ ጎግሎ ማየት ነው። የሀስብ ጥራትና ብስለት፣ የነገር አወራረድ፣የማዳመጥ ችሎታ፣ማስረጃን ማስደገፍ ተቃዋሚን ማክበር የት እንዳለ ታገኙታላችሁ ለእውነት ከታደላችሁ።
  ለነገሩ ለናንተ የሚመቻችሁ ያስተዋለ ሳይሆን ያነበነበ ነው። ብትሳደቡም ጽሁፉ አይለፋችሁ አንብቡት ጥቅሙ ብዙ ነው።

 12. While I was searching for Prof. Ezekiel’ scholarly papers, if there are any, I landed into his student ratings at the Rate My Professors.com. Not only are his ratings bad (which is okay for a foreign-born teacher) but I found one of his American students’ comment as interesting. He said something like, “the professor feels he is currently being oppressed”. It looks like he has a serious inferiority complex that grew with him and pushes him to make outrageous and outlandish statements in order to gain recognition. I know from history that people who feel inferiority complex are very dangerous if they accidentally gain power. E.g. Joseph Stalin.

 13. የአንዳንድ ኦሮሞ ልሂቃን ሩጫ የዛሬ 400 አመት ካቆምንበት እንጀምር እያሰኘ ነው!
  የኦሮሞ መስፋፋት ታሪክ ማስረጃ በአገርኛውም ሆነ በውጪዎቹ ቋንቋዎች በገፍ የሚገኝ በመሆኑ ምንም የሚያከራክር ርዕስ አይደለም። የአማራ ፈጠራና ተረትም አይደለም። የግራኝ የጦርነት ውሎ ዘጋቢ ለምሳሌ በምን ሒሳብ ውሸትን ከአማራ ወግኖ ይጽፋል? ብዙ ፈረንጆችስ ተባብረው እንደተመካከረ ሰው ሐሰት ጽፈው ሞያቸውን ህሊናና ስማቸውን ለምን ያጎድፋሉ? አባ ባሕሪ የተባሉት የሐይማኖት አባትስ የአይን ምስክር ሆነው ስለኦሮሞ መስፋፋት ሲከትቡ በሐሰት አትመስክር፣ አትዋሽ የሚል የአምላክን ሕግ በድፍረት ጥሰው ልበወለድን እውነት አስመስለው ሊያሳምኑን እንደምን ደፈሩ? ደግሞ ትግሬ ናቸውም ይባላል።
  የሆነው ሆኖ፦
  1. እናርያ–የዛሬዋ ኤሉአባቦር እና ጅማ አካባቢዎች በመስፋፋቱ ተውጠዋል።
  2. ባሌ/ባሊ–በፍፁም በሸዋው ማእከላዊ መንግሥት ስር ነበር። ኦሮሞ አልነበረም። ከሽምብራ ኩሬ ጦርነት በኋላ በግራኝ የተነጠቀ የመጀመርያው የማእከላዊ መንግሥት አካል ነው። ገላውዴዎስ ቢያስመልሰውም ኋላ በኦሮሞ ሀይል ተወስዷል።
  3. ዳሞት–ከአባይ በስተደቡብ ከፊል ቤዛሚን (ወለጋን) ጨምሮ እስከ ሙገር የሚደርስ አካባባቢ ሲሆን በኦሮሞ ተስፋፊዎች ተውጧል።
  4. ደዋሮ–ሐረርጌ ሲሆን እንዲሁ በሶማሌ ዝርያዎች የተመሠረተው ሥርወመንግሥት ተውጦ ኦሮሞ የተደረገ የሶማሌ ጎሣ ነው። ሐረሪዎች የኦሮሞን የሞጋሣ እና የጉዲፈቻ የማንነት ማጥፊያ የገዳ አሠራርን ተቋቁመው እስከዛሬ የዘለቁበት ሚስጥር ጥልቅ ጥናት የሚያስፈልገው ነው።
  4. ፈጠጋር–ቀደም የጉራጌዎች እስላማዊ አስተዳደር ነበረው። ኋላ በአምደጽዮን ወደ ሸዋ ማዕከላዊ መንግሥት ተጠቃሎ ፈጠጋር እየተባለ ይጠራ ነበር። በመስፋፋት በኦሮሞዎች እጅ ከወደቀ በኋላ አርሲ ተብሎ ተሰየመ።
  4. ላኮሞልዛ–የአማራውን ይዞታም እንዲሁ ከደብረዘይት ጀምሮ እየተቆጣጠሩ የገቡት የግራኝን እግር ተከትለው ነው። አስከ ወሎ የአካባቢ ስሞችን እየቀየሩ ሠፍረዋል። ወሎ ላኮሞልዛ ነበር። ወሎ ብለው ከሰየሙት በኋላ የተለያዩ ቀበሌዎችንም ከቀደመ ስያሜው እያወጡ የራሳቸውን ሰሞች ሰጥተዋቸዋል። አሁን የቀደመ ስማቸውን የመጠቀም ግዴታ በክልሉ መወሰኑ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ ነው።
  ምክንያቱም እንደ እነሕዝቅኤል ጋቢሳ ያሉ የኦሮሞ ምሁር ተብዬዎች ጦርቱን የዛሬ 400(300) አመት ከቆመበት ማስቀጠል አምሯቸዋል! በረራን( አዲስ አበባን) የኦሮሞ ናት ማለት ታሪክን፣ ሕገመንግሥትን፣ እና ተጨባጭ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ የኬኛ የራስ ወዳድነት የሥነልቦና ቀውስ ምልክት ወይም ፈረንጆቹ Mine Syndrome የሚሉት የልጆች በሽታ ነው አያልናቸው Wallon keenyaa ይሉናል። የአማራውን ልሂቅ በአዲስ አበባ ጉዳይ ስለተሟገታቸው provoke ሊያደርጉት።

 14. ታሪክ በታሪክነቱ ብለው ያስተማሩን ፕሮፌሰር አለሜ ለስደት በቅተው ያረፉት በዚህ ወርቅማ መርህ ነበር::ሌሎቹ ማፈሪያዎች ግን በየጊዜው የሚጽፉት ከየወቅቱ ገዥዎችና ፖለትካ ጋር የሚገጥመውን ወይም ለራሳቸው ምረቃ በሚያደርጉት ጥድፊያ ይሁንታ ለማገኘት ነው:: አቻሜየለህ ነገሮችን የመፈልፈል ችሎታውን ሳደንቅ የኦሮሞና የሌሎች ኩሽቲክ ህዝቦች በሃገራችን ኢትዮጲያ ቀዳሚ ነዋሪ መሆናቸውን ቢክድም የአፋር ተረፈቅርስ ሉሲ ህያው ምስክር ነች:: አፋር ኩሽቲኩ ከሌላው ኩሽቲክ ተለይቶ አይታይም ኦሮሞም ከነባር ቀዳሚ ህዝቦች አንዱ መሆኑን መቀበል የግድ ነው:: ሆኖም ግን የሃገራችን ጥንታዊ ነገዶች ነገስታት ሴማዊ ብቻ ሳይሆኑ ኩሽቲክ ኦሞቲክ ናይሎቲክ መሆናቸውን ከስነህዝብ ምርምር መረዳት ይቻላል:: ንግስት ሳባ ራሷ ኬጡራ ከምትባል የሳባ ነገድ የተገነት ኩሽቲክ ነች:: ወደህዝቅኤል የወቅቱ ወሎ ኦሮሞም ነው የሚል ከፋፋይ ፕሮፕጋንዳ አልስማማም ልክ እንደብዙሃኑ ህዝባችን ወሎ የድብልቆች ክፍለሃገር ነው:: ራያ ቃሉ ኦሮሞም ቢሆንም ሁሉንም ብሄሮች ትግሬን ኦሮሞን አማራን ባቀፈው መልኩ ወሎም የሁሉም ክፍለሃገር ነው የተደባለቀውን ህዝብ ብብሄርና በዘር መለያየት አይቻልም::በትክክል ያኔ ለመመረቂያ ስለወለጋ ሳይቀር እንዲ ጽፎ ከሆነ ዛሬ አቋሙን ሲቀይር ይፋ ማስተባበያ መስጠት ይኖርበታል:: ምናልባት የዶክተር ላጲሶ ተማሪ ከሆነ ግን እሳቸው ተገለባባጭ አንዴ አሃዳዊ ደጋፊ ሌላ ጊዜ ፌደራላዊ አድናቊ ስለሆኑ ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ መሆኑ ነው::

 15. Comment:የአንዳንድ ኦሮሞ ልሂቃን ሩጫ የዛሬ 400 አመት ካቆምንበት እንጀምር እያሰኘ ነው!
  የኦሮሞ መስፋፋት ታሪክ ማስረጃ በአገርኛውም ሆነ በውጪዎቹ ቋንቋዎች በገፍ የሚገኝ በመሆኑ ምንም የሚያከራክር ርዕስ አይደለም። የአማራ ፈጠራና ተረትም አይደለም። የግራኝ የጦርነት ውሎ ዘጋቢ ለምሳሌ በምን ሒሳብ ውሸትን ከአማራ ወግኖ ይጽፋል? ብዙ ፈረንጆችስ ተባብረው እንደተመካከረ ሰው ሐሰት ጽፈው ሞያቸውን ህሊናና ስማቸውን ለምን ያጎድፋሉ? አባ ባሕሪ የተባሉት የሐይማኖት አባትስ የአይን ምስክር ሆነው ስለኦሮሞ መስፋፋት ሲከትቡ በሐሰት አትመስክር፣ አትዋሽ የሚል የአምላክን ሕግ በድፍረት ጥሰው ልበወለድን እውነት አስመስለው ሊያሳምኑን እንደምን ደፈሩ? ደግሞ ትግሬ ናቸውም ይባላል።
  የሆነው ሆኖ፦
  1. እናርያ–የዛሬዋ ኤሉአባቦር እና ጅማ አካባቢዎች በመስፋፋቱ ተውጠዋል።
  2. ባሌ/ባሊ–በፍፁም በሸዋው ማእከላዊ መንግሥት ስር ነበር። ኦሮሞ አልነበረም። ከሽምብራ ኩሬ ጦርነት በኋላ በግራኝ የተነጠቀ የመጀመርያው የማእከላዊ መንግሥት አካል ነው። ገላውዴዎስ ቢያስመልሰውም ኋላ በኦሮሞ ሀይል ተወስዷል።
  3. ዳሞት–ከአባይ በስተደቡብ ከፊል ቢዛሚን (ወለጋን) ጨምሮ እስከ ሙገር የሚደርስ አካባባቢ ሲሆን በኦሮሞ ተስፋፊዎች ተውጧል።
  4. ደዋሮ–ሐረርጌ ሲሆን እንዲሁ በሶማሌ ዝርያዎች የተመሠረተው ሥርወመንግሥት ተውጦ ኦሮሞ የተደረገ የሶማሌ ጎሣ ነው። ሐረሪዎች የኦሮሞን የሞጋሣ እና የጉዲፈቻ የማንነት ማጥፊያ የገዳ አሠራርን ተቋቁመው እስከዛሬ የዘለቁበት ሚስጥር ጥልቅ ጥናት የሚያስፈልገው ነው።
  4. ፈጠጋር–ቀደም የጉራጌዎች እስላማዊ አስተዳደር ነበረው። ኋላ በአምደጽዮን ወደ ሸዋ ማዕከላዊ መንግሥት ተጠቃሎ ፈጠጋር እየተባለ ይጠራ ነበር። በመስፋፋት በኦሮሞዎች እጅ ከወደቀ በኋላ አርሲ ተብሎ ተሰየመ።
  4. ላኮሞልዛ–የአማራውን ይዞታም እንዲሁ ከደብረዘይት ጀምሮ እየተቆጣጠሩ የገቡት የግራኝን እግር ተከትለው ነው። አስከ ወሎ የአካባቢ ስሞችን እየቀየሩ ሠፍረዋል። ወሎ ላኮሞልዛ ነበር። ወሎ ብለው ከሰየሙት በኋላ የተለያዩ ቀበሌዎችንም ከቀደመ ስያሜው እያወጡ የራሳቸውን ሰሞች ሰጥተዋቸዋል። አሁን የቀደመ ስማቸውን የመጠቀም ግዴታ በክልሉ መወሰኑ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ ነው።
  ምክንያቱም እንደ እነሕዝቅኤል ጋቢሳ ያሉ የኦሮሞ ምሁር ተብዬዎች ጦርቱን የዛሬ 400(300) አመት ከቆመበት ማስቀጠል አምሯቸዋል! በረራን( አዲስ አበባን) የኦሮሞ ናት ማለት ታሪክን፣ ሕገመንግሥትን፣ እና ተጨባጭ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ የኬኛ የራስ ወዳድነት የሥነልቦና ቀውስ ምልክት ወይም ፈረንጆቹ Mine Syndrome የሚሉት የልጆች በሽታ ነው አያልናቸው Wallon keenyaa ይሉናል። የአማራውን ልሂቅ በአዲስ አበባ ጉዳይ ስለተሟገታቸው provoke ሊያደርጉት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.