በአዲስ አበባ የአማራ ሴቶች ማኅበር ሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለልን ለማክበር እየተዘጋጀ ነው

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2011 ዓ.ም (አብመድ) የበዓላቱን ታሪካዊ ዳራ፣ እሴቶች እና መገለጫዎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

በውይይቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ኂሩት ካሳው እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር እንዳወቀ አብቴን ጨምሮ ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል፡፡ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ ለአብመድ በሰጡት አስተያዬት የአማራ ክልል ሕዝብ ያለውን ባህል በተደራጀ መልኩ ማስተዋወቁ ትክክለኛው ባህል ለትውልድ እንዲተላለፍ ያስችላል ብለዋል፡፡

ሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለልን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበርም ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡ አከባበሩን በተመለከተም ከነሀሴ 1 እስከ 14/2011 ዓ.ም በየክፍለ ከተሞች ዝግጅት ይኖራል፡፡

ከነሀሴ 15 እስከ 18/2011 ዓ.ም ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች ውይይቱ ይቀጥልና ነሀሴ 19 በሚሊኒየም አዳራሽ ትክክለኛ የበዓላቱን ገጽታ እና መገለጫ በሚያሳዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር መርሀ ግብሩ ያሳያል፡፡ ሻደይ – በዋግኽምራ፣ አሸንድዬ – በላል ይበላ፣ ሶለል ደግሞ በራያ ቆቦ ነው የሚታወቁት፡፡ ዝግጁቱ እስከ 33 ሺህ ሰወች ይታደሙበታል ተብሎ በሚጠበቀው ኤግዚቢሽን ይጠናቀቃል፡፡

ዘጋቢ፦ ጽዮን አበበ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.