የአማራ ብሔርተኝነትና ነገደ አማራ የለም ለሚለው የአንዳርጋቸው ጽጌ ቧልት የተሰጠ መልስ (ወንድወሰን ተክሉ)

ከእስር ይፈታ ዘንድ ቀን ከለሊት ታላቅ ዘመቻን ሳካሂደለት የቆየሁት አንዳርጋቸው ጽጌ «ትውልድ እንዳይደናገር እኛ እንናገር» የሚለውን አወዘጋቢና አደነጋጋሪ መጽሀፉን ለንባብ ካበቃበት ግዜ ጀምሮ አወዛጋቢነቱና አደነጋጋሪነቱን አጠንክሮ የቀጠለበት ሰው ሆኗል፡፡ ሆኖም በእስሩ ዘመን ያደረኩለትን (ከመላ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር) የይፈታ ዘመቻዬን ስጠቅስ ሰውዬውን የይፈታ ዘመቻን ላደረግንለት ወገኖች ለምን ክህደት ፈጸመ ለማለት እንዳልሆነ ግንዛቤ ይያዝልኝ ዘንድ እያሳሰብኩ የከእስር ይፈታ ዘመቻን ውለታን ለመመለስ አንዳርጋቸው እማያምንበትን ጉዳይ ባለመግለጽ አፉን ለጉሞ ይቀመጥ የማለትም ቅንጣት ታክል ፍላጎትና ሀሳብ እንደሌለኝ ገልጬ እሱ በነጻነት እሚያንሸራሽረውን አቋም እኔም በነጻነት የመተቸትና የመደገፍ መብት ስላለኝ ይህንን ጽሁፉ ለመተየብ መቻሌን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

**1ኛ- ነገደ አማራና የአማራ ብሄርተኝነት የለም የሚለው የአንዳርጋቸውን ትርክት ስንመለከት

ፕ/ር እዝቅኤል ገቢሳ ከፋና ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅና ብሎም በትግራይ መቀሌ ዩንቨርሲቲ ተገኝቶ በገለጸው ገለጻ ላይ «እኔ በዜግነት ፖለቲካ አላምንም» ለሚለው አቋሙና ብሎም «እኔ ውህድ ብሄር በሚባል አገላለጽና ህልውና አላምንም» በማለት ለገለጸው አንዳርጋቸው መልስ በሰጠበት «አማራ የሚባል ነገድና የአማራ ብሄርተኝነት እሚባል የለም» ብሎ ገልጿል፡፡ እንደ አንዳርጋቸው አገላለጽ ይህንን የነገደ አማራን ህልውና የካደበትን እና ብሎም የአማራን ብሄርተኝነትንም አብሮ ጨፍልቆ የለም ያለበትን ጸረ አማራዊ አቋሙን አመክንዮታዊ ለማድረግ ባቀረበው «ታሪክ ተኮር » ገለጻው የዛሬ አማርኛ ቋንቋ እንኳን ጥንታዊውና ታላቁ የአክሱማይት መንግስት ወደ ደቡባዊው የኢትዮጵያ ክፍል ያሰማራቸው የሀረሩ፤ሀደሬ፣ጉራጌ፣አገው፣ቅማንትና ወዘተ ነገድ ተወላጅ ወታደሮቹ የተፈጠረ ቅይጥ ቋንቋ የሆነ ነው ይልና ይህ ቋንቋ ከነገደ አማራ መፈጠር በፊት የተከሰተ በመሆኑ የአማራ ቋንቋ አይደለም ብሎም አማራ የሚባል ነገድም ሆነ የአማራ ብሄርተኝነት የሚባልም የለም ሲል ይገልጻል፡፡

አንዳርጋቸው ጽጌ ይህንን ግኝቱንም እንደ አዳስ በመግለጽ ዛሬ «አማራ ነን የሚሉ የአማራ ተወላጆች ይህንን ታሪካዊ ሀቅ ይወቁ አይወቁ እማውቀው ነገር ባይኖርም ሀቁ ግን ይህ ነው» ሲል ይደመድማል፡፡

ይህንን የአንዳርጋቸውን ጥሬ ቃል እንኳን ብንመለከት እርሰበርሱ የሚቃረንና የሚጣረስ መሆኑን ለማወቅ ብዙም ልፋት አይጠይቀንም፡፡ «የአማርኛ ቋንቋ ከአማራ ነገድ መፈጠር በፊት የተፈጠረ ነው» የልና ቀጠል አድርጎ «አማራ የሚባል ብሄር የለም» የሚለንን አባባሉን ብቻ ስንመለከት እርሰበርሱ የተጣረሰና የተቃረነ መሆኑን እናያለን፡፡ አማራ የሚባል ነገድ የለም ያለ ሰው እንዴት ነው መለስ ብሎ ደግሞ አማርኛ ቋንቋ ከአማራ ነገድ መፈጠር በፊት የተፈጠረ ነው ብሎ ሊናገር የቻለው ብለን ማየት ይገባናል፡፡

ሰውዬው የአማርኛን ቋንቋ ባለቤትነትን ለጥንታዊውና ለገናናው አክሱማይት መንግስት ለመስጠት ሲል በገለጸበት አንደበቱ የአማራን ህዝብ እንደነገድ መፈጠሩን «አማርኛ ቋንቋ የአማራ ነገድ ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረ ጥርቅም ቋንቋ ነው » ሲል ይገልጻል፡፡
እናም አገላለጹ በራሱ የተቃረነ መሆኑን እናያለን ማለት ነው፡፡

2ኛ-አማራ የሚባል ነገድ የለም የሚለው ትርክታዊ አፈጣጠር

አማራ የሚባል ነገድ የለም የሚለውን ትርክት ለመጀመሪያ ግዜ ይዞ ወደ አደባባይ ብቅ ያለው ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም ሲሆን እሱም አማራ የሚባል ተራራ እንጂ ህዝብ የለም በማለት በአደባባይ ለመግለጽ የተገደደው «የአማራው ገዢ መንግስት የሆነውን ደርግ » እያለች ስትገልጽ የነበረችውን የህወሃትን ወደ አዲስ አበባ ግስጋሴ ያሰጋውና ያስጨነቀው መንግስቱ እኔ የምመራው መምግስት የአማራ ገዢ ኃይል አይደለም ለማለት አማራ የሚባል ነገድ የለም እስከማለት ወታደራዊ ምርምሩን ተጠቅም የገለጸበት ሲሆን ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ በ1984 እና በ1985 ላይ ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ብቅ ብለው አማራ የሚባል ነገድ የለም ያሉበት ወቅትን እናስታውሳለን፡፡

የኮ/ል መንግስቱ የአማራ ነገድ እሚባል የለም የሚለው ክህደታዊ ትርክት ዋና አፍላቂ ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ፕሮፌሰሩ ለደርግ ባቀረቡት «ጥናታዊ »በተባለ ግን Politically Motivated በሆነ ሁኔታ የህወሃትን የምንዋጋው የአማራውን አገዛዝ ነው የሚለውን ፕሮፖጋንዳዋን ዋጋ ለማሳጣትና ብሎም የደርግ መንግስት የአማራ መንግስት አለመሆኑን ለማሳየት ሲባል አማራ እሚባል ነገድ የለም በሚል ግብታዊ ትንተናን ሊያስተጋቡ እንደቻሉ መረዳት ይኖርብናል፡፡

በፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ፖለቲካዊ ምክር የተጠቀመው ደርግ ትናንት የህወሃትን «ደርግ የአማራ መንግስት ነውን» ክስና አሉባልታን ለመከላከል «አም ሃራ ማለት በተራራ ላይ የሚኖር ህዝብ እንጂ አማራ የሚባል ነገድ የለም » እስከማለት እንደደረሰው የደርግ መንግስት ዛሬም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሚያቀነቅኑት የዜግነት ፖለቲካ እንቅፋት ሆኖናል ብለው ለሚገልጹት የአማራን ብሄርተኝነትን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ለማገድና ብሎም ለማሳገድ እንደመፍትሄ ያቀረቡት የአማራ ብሄርተኝነት እሚባል የለም ማለትን ሲሆን ለዚህም ህልውናዊ ክህደታቸው ልክ የደርጉ መንግስት ኮ/ል መንግስቱ የደርግ መንግስት የአማራ መንግስት አይደለም ለማለት «ታሪክን አጥንቼ እንዳገኘሁት አማራ የሚባል ተራራ ቢኖር እንጂ አማራ የሚባል ነገድ የለም» በማለት እንደተናገሩት ሁሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም ይህንን የአማራ ብሄርተኝነትን ለመምታትና ለማስመታት «አማራ የሚባል ነገድ የለም፤ የአማርኛ ቋንቋም የአማራ ሳይሆን የብሄር ብሄረሰቦች ድብልቅ የሆነ የአክሱማይት መንግስት ቋንቋ ነው » ሲሉ እንደገለጹ መረዳት ይቻላል፡፡

ያ ማለት የሶስቱም የነገደ አማራን ህልውናን ከሃዲ ሰዎች ማለትም ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም፣ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያምና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ነገደ አማራ የሚባል ህዝብ የለም ብለው የገለጹበት ወቅትና ዘመን ቢለያይም ምክንያታቸው ግን አንድና አንድ የሆነ Politically Motivated ሆኖ ለፖለቲካዊ ፍጆታና ትርፍ ታስቦ የተነገረና ብሎ ዛሬም እየተነገረ ያለ ጸረ አማራዊ ክህደት መሆኑን እንረዳለን፡፡

**3ኛ- አማራ፣የአማራ ብሄርተኝነት፣የአማርኛ ቋንቋና የአንዳርጋቸው ትርክት

እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ አባባል ይህ የአማርኛ ቋንቋ ባለቤት ጥንታዊው የአክሱማይት መንግስት የተለያዩ ብሄርብሄረሰቦች የፈጠሩት ቋንቋ ነው የሚለውን Shallow እና መሀይማዊ ትርክት እንደ አዲስ ግኝት አድርጎ ለማቅረብ ቢዳዳውም ፈጽሞ አዲስ እንዳልሆነና አንዳርጋቸውም ይህንን ትርክት በማቅረብ የመጀመሪያ ሰው እንዳልሆነ እሱ ቢክድም ማስረጃ አለና የመጀመሪያ ሰው እንዳልሆነ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡

እንዲያውም የአቶ አንዳርጋቸው የአማርኛ ቋንቋ የነገደ አማራ አይደለም ትርክት የዶ/ር ሀብተማሪያም አሰፋ ትርክት እንደሆነ መግለጹም ተገቢ ሆኖ ይገኛል፡፡ ህወሃት አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ሁለተኛ ዓመት ላይ ማለትም በ1985አከባቢ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የኢህአዴግ ሹመኛ ሆነው በአዲስ አበባ መስተዳድር ውስጥ በሚያገለግሉበት ወቅት አንድ ዶ/ር ሀብተማሪያም አሰፋ የሚባል አፍቃሬ ህወሃትና ካድሬ ከስድስት መቶ በላይ ገጽ ያለውን መጽሀፍ በ«የኢትዮጵያ ነገዶች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አመጣጥ» በሚል ርእስ ስር አሳትሞ እንደነበረ እማልዘነጋው እውነታ ነው፡፡

ዶ/ር ሀብተማሪያም አሰፋ በዚህ ከላይ በገለጽኩት ድልብ መጽሀፉ ላይ የአማርኛን ቋንቋ የጥንታዊው አክሱማይት መንግስት ወታደሮች የፈጠሩት ቋንቋ ነው ሲል ይገልጸዋል፡፡ እንደ ዶ/ር ሀብተማሪያም አሰፋ አገላለጽ ታላቁ የአክሱማይት መንግስት ወታደሮች ወደ ደቡባዊቷ የኢትዮጵያ ክፍል ሸዋ፣ሲዳሞ፣ሀረርና…ወዘተ ዘምተው ብዙ ዓመታት በመቆየታቸው ከአከባባዊ ነዋሪዎች ጋር ለመግባባት ሲሉ የፈጠሩት ቅይጥ የወታደሮች ቋንቋ ነው ይለንና በዚህም ምክንያት ይላል ዶ/ር ሀብተማሪያም አሰፋ «ዛሬ እኔ በአማርኛ ቋንቋ በመናገሬ የሚከፉ የትግራይ ተወላጆች እምመልሰው አማርኛ የተሰባበረ የትግሪኛና ግእዝኛ ቋንቋ ውጤት የሆነ የአክሱማይት ወታደሮች ቋንቋ የሆነ በመሆኑ የትግሬ ቋንቋ ነው እያልኩ ነው እየገለጽኩላቸው የምገኘው » ሲል እዚያው መጽሀፉ ላይ አስፍሮ ይገኛል፡፡ ይህ ማለት አማርኛ ቋንቋ በአክሱማይት ወታደሮች የተፈጠረ የወታደር ቋንቋ ወይም የብሄር ብሄረሰቦች ቅይጥ ቋንቋዎች የፈጠሩት ቋንቋ ነው ማለት ነው፡፡

ይህ እንግዲህ በ1985 እና በ1986አከባቢ በኢህአዴግና በተለይም በህወሃት ውስጥ በስፋት ሲስተጋባ የነበረ ትርክት ሲሆን ሀሳቡ ቅቡልነትን ተነፍጎ ሲቀበር ከሁለት ዓስርተ ዓመታት ቆይታ በኃላ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከተቀበረበት ተቆፍሮ በመውጣት እንደ አዲስ የቀረበ ምውት ትርክት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

**4ኛ- እውነታው ምንድነው?

ገናናው የአክሱማይት መንግስት ህልውና ከመከሰቱ በፊት ነገደ አማራ እንደ ህዝብ የተከሰተ መሆኑን ከታሪክ መዛግብት መረዳት ተችሏል፡፡ ታላቁ አክሱማይት የንጉስ ቀዳማዊ ምንሊክ አራተኛ ልጅ ሲሆን ይህ ማለት ከክርስቶስ ልደት 880ዓ ዓ በፊት የነገሰ ሲሆን ከክርስቶስ ልደት 1000ዓ ዓ በፊት በ19ዓመቱ የነገሰው የንግስት ሳባ ልጅ ቀዳማዊው ምንሊክ የስም አወጣጡ እራሱ እንደሚገልጸው የአማርኛ ቋንቋ መሆኑን እና አማሮች በዘመኑ መከሰታቸውን ያሳየናል፡፡ ምንሊክ ማለት ከእስራኤላዊው አባቱ ንጉስ ሰለሞን የተወለደ በመሆኑ «አባትህ ቢያይህ ምን ይልክ ይሆን » በሚል አነጋገር «ምንሊክ » እንደተባለ ታሪክ ይገልጻል፡፡

ይህው የሰለሞናዊውን ስርወ መንግስትን ከክርስቶስ ልደት 1000ዓመት በፊት የመሰረተው ቀዳማዊው ምንሊክ እንደነገሰ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቋንቋን በይፋ ግእዝ በማድረግ እስከ አስራ ሶስተኛው ክፍለዘመን ድረስ በ1257 የነገሰው ንጉስ ይኩኑ አምላክ የሀገሪቱን ብሄራዊ ቋንቋ ከግእዝነት ወደ አማርኛነት እስከቀየረው ድረስ ለ2257ዓመታት የሀገሪቷ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል፡፡

በዶ/ር ሀብተማሪያም አሰፋ አማርኛ ቋንቋ የጥንታዊውና የገናናው አክሱማይት መንግስት የወታደሮች ቋንቋ እንደሆነ ተገልጾ የአክሱማይት መንግስት ደግሞ እንደ የትግሬ መንግስት አድርጎ በማቅረብ አማርኛን የተሰባበረ ትግሪኛና ብሎ የተሰባበረ ግእዝኛ አድርጎ በመግለጽ የትግሬ ቋንቋ ነው ብሎ ማሰቡና መግለጹም ታላቅ ስህተት እንደሆነ እንረዳለን፡፡

ሲጀመር ገናናው የአክሱማይት መንግስት በዛሬው ትግራይ የተመሰረተና የተገነባ ቢሆንም ገንቢዎቹና ባለቤቶቹ ከዛሬዎቹ ትግራዋዮች ጋር በፍጹም እማይገናኙ መሆኑን ያጢኑአል፡፡

የትግራይ ህዝብ እንደ ነገድ ከመከሰቱ 600ዓመት በፊት የታላቁ አክሱማይት ስልጣኔና መንግስት መመስረቱን ልብ ካልን በኃላ ታላቁ አክሱማይት እራሱ የቀዳማዊ ምንሊክ አራተኛ ልጅ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ትግሬ የሚባለው ነገድ እንደህዝብ የተከሰተው ከክርስቶስ ልደት 200ዓመት ቀደም ብሎ እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ይገልጻሉ፡፡

**5ኛ- መደምደሚያዬ

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ኢዜማ የግንቦት ሰባት ሌላኛው ስም ከመሆኑ አኳያ በመላው አማራ ህዝብ ዘንድ እንደ ተመጠጠ የሸንኮራ አገዳ የተጣለና ስፍራም ያጣ ከመሆኑ አንጻር የፕ/ር ህዝቅኤል ገቢሳ «እኔ በዜግነት ፖለቲካ እሚባል አላምንም» የሚል አቋም ሲስተጋባ የሚታገልለትን ድርጅት ህልውናን ለማቆየት እንቅፋት ባላቸው ላይ ማጥቃትን የመሰንዘር ተግባር ሆኖ እናያለን፡፡

በመሰረቱ ፕ/ር ህዝቅኤል ገቢሳ «በዜግነት ፖለቲካ አላምንም» የሚለው አቋም ባይስተጋባ ኖሮ አቶ አንዳርጋቸው ፕሮፌሰሩን በመቃወም መልስ ይሰጣል ብሎ ማሰቡ የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የአንዳርጋቸው አካሄድ በሙሉ ፖለቲካዊ ትርፍን ፍለጋ እየተደረገ ያለ መኳተን በመሆኑ ላንሰማው ባንችልም የአማራን ብሄርተኝነትን ግን ከዓመት በፊት ስለተመለከተው ይህንን ኃይል ለመበትን፣ለመምታትና ብሎም ለማስመታት በተፈጠረው ብሄርተኝነት ላይ ብቻ ከማነጣጠር ወደ ኃላ ተጉዞ በ1985 በአንድ የህወሃት ካድሬ የተጻፈና የተቀበረን ጸረ አማራዊ ህልውናን መጽሀፍ ከተቀበረበት ቆፍሮ በማውጣት አማራ እሚባል ነገድ የለም፤ አማርኛም የአማራው ሳይሆን የሌሎች ብሄርብሄረሰቦች ጥርቅምቅም ቋንቋ ነው እስከማለት እንዳደረሰው መረዳት ያስፈልጋል፡፡

የአንድን ህዝብ ማንነት በመግፈፍና እንዳልተፈጠረ በመቁጠር የተፈጠረውንና ያንን እንዳልተፈጠረ እየተገለጸ ያለውን ህዝብ እየመራና እያታገለ ያለውን ብሄርተኝነትንም ማጥፋትና ብሎም ማፈራረስ እንደማይቻል አቶ አንዳርጋቸውና እሚሟሟትለት ኢዜማና ድርጅትና አመራሮቹ ሊያውቁ ይገባል፡፡፡

13 COMMENTS

 1. Dear Wondwossen,
  I don’t believe you have grasped the art of public discourse. You need to first fairly summarize statements of your interlocutors. You may then proceed to not only state why you disagree but also clearly present your side of the issue. You have to the trust the reader is mature enough to make up their mind. What you, Sertse, Achamyeleh, Girma, etc are doing is flood the pages with verbiage and name-calling that ultimately ends up undermining your cause, if you happen to have figured one yet! In other words, you don’t represent Amhara people at all!

  You mentioned how you fought for Andargachew’s release from prison. You must have done that on ethnic, not humanitarian grounds; because he was Amhara! You are now offended because unlike you Andargachew does not believe in ethnic supermacy. Because you have not thought through what you were about to write you effectively revealed your hate mongering secret. Hurry up and change your zeraf mentality. I can see you are Wond Worsen and it is difficult to change. But I will urge to try. After all, we are Ethiopian and we belong together.

 2. ውድ ወንድወሰን ተክሉ እርግጥ አማራ የሚባል ነገድ የለም ያሉት ፕሮፍ መስፍን እና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ብቻ አይደሉም ፤

  የኢትዮጵያ የአለሙ መፋረጃና ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ወዘተ …መጽሐፍት ደራሲ ንቡረ ዕድ ኤርሚያስ ወልደየሱም ይህንኑ በስፋት በመጽሐፋቸው ገልጸዋል ፤ ባጭር ቃል አማራ የሚባል ነገድ የለም ፤

  የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረው ኢንጂኒየር ይልቃል ጌትነትም ይህንኑ ያጠናክርና የአማራ ብሄርተኞችን ጽንፈኞች ሲል ይገልጻል ፤ የሚገርመው አሁን ይልቃል ከአብን አባላት ጋር ይታይ ይዟል ምን አልባት ወደፖለቲካው መግቢያ ስላጣ አብንን እንደ መግቢያ ተጠቅሞ ይሆን እንጃ?

  የሆነው አማራ ተብለው የተጠረነፉትን ነገዶች ዘርዝረን ስናይ አማራ ሆይ የት ነህ? ማንስ ነህ? እንድንል መገደዳችን አይቀርም
  እንደ ፕሮፍ መስፍን ትንተና 28 ሚሊየን ተብሎ በአማራነት የተጠረነፈውን ሲተነትኑ
  አገው 8 ሚሊየን
  ቅማንት 6ሚሊየን
  አርጎባ 3ሚሊየን
  ወይጦ 2.8 ሚሊየን
  ሺናሻ 2.7 ሚሊየን
  የወሎ ኦሮሞ 3ሚሊየን እና
  ሌሎች 2.5
  ድምር 28 ሚሊየን ይሆናል ምን አልባት ሌሎች የተባሉት በዘመነ ወያኔ ጠፉ የተባሉት ይሆኑ እንጃ?

  እንግዲህ እኒህ ተጠርንፈው ነው አማራ የሚል ወፍራም ካባ የለበሱት እንጂ አማራ የሚባል ነገድ የለም ነው ምሁራኑ የሚሉት ታድያ አማራ ማን ነው? የትስ ነው?

  አንዳንዶች ደግሞ ነገሩን ገፋ አድርገው አማራ ነኝ የሚለው ቡድን የሚሸልልባቸው አጼ ቴዎድሮስ ቅማንት ሲሆኑ በላይ ዘለቀም ኦሮሞ ናቸውና እንደ አማራ ታሪክ ያለው አንድ ሰው ይጠቀስ በሚል ከሞገቱ በኋላ አማራ ሊባሉ የሚገባቸው ወገንን ከወገን የሚያናክሱ ትምክህተኞች እና የትምክህት ለሃጫቸውን እና ልጋጋቸውን እየተፉ ኢትዮጵያውያን ተስማምተው በፍቅር እንዳይኖሩ ነገር ሲሸርቡ የሚያድሩ እንደነ:-
  ጌታቸው ሽፈራው
  ግርማ ካሳ
  ሃብታሙ አያሌው
  ኤርሚያስ ለገሰ
  ርዕዮት ዓለሙ
  ኢየሩሳሌም …
  ዘመድኩን በቀለ
  አያሌው መንበር
  እስክንድር ነጋ
  ሄኖክ የሺጥላ
  ፕሮፌሰርጭጌታቸው ኃይሌ
  ወዘተ…. ዓይነቶቹ ናቸው ምእንያቱም እንደነዚህ ዓይነት ነቀርሳዎች አገውም ፣ ቅማንትም ፣ አርጎባም ፣ ወይጦም ፣ ሺናሻም አይደሉምና ሲሉ ይሞግታሉ፤ እንዲያውም በአቶ ዓለምነው መኮንን ባንድ ወቅት የትምክህት ለሃጫቸው ሊገታ ይገባል ተብለው የተወረፉት እንደነዚህ ዓይነት ከንቱዎች ናቸው ሲሉ መከራከሪያ ያቀርባሉ እናም ወዳጄ አንተስ ማነህ???

 3. ወንድሜ ወንደወስን እግዚአብሄር ይባርክህ በደንብ እውቀትና ትህትና በተሞላበት መንገድ ነው የአቶ አንዳርጋቸውን የደንቆሮ ትርክት አፍር ድሜ ያበላኸው፡፡ አንድ አባባል አለ፤ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅም ይባላል፡፡እኒህ ሰውዬ ከታላቋ ብሪታንያ በሚከፈላቸው ድጎማና ምጽዋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ባለፉት 40 ዓመታት ከወያኔ እና ከሻብያ ጋር ጫካ በመግባት አማራ ጨቋኝ ናት ብለው ማኒፌስቶና ፕሮገራም ቀርጸው ሲባክኑ የኖሩ ሰው ናቸው፡፡ የሩቁን ትተን አሁን በወያኔ ታስሬ ነብር በሚሉት ድራማ ወያኔ ኮምፒዩተርና የገንዘብ ድጋፍ በማደረግ አንድ ድንቁርናቸውን በደንብ የሚገልጽ መጽሃፍ አሳትመዋል፡፡ የእርሳቸው እስር ድራማ ነበር የምልበት ዋናው ምክኒያት አያድርገውና በዚያን ወቅት ሌላ አንድ ኢትዮጵያዊ ከሌላ ማህበረሰብ በተመሳሳይ ወንጀል ቢያዝ ኖሮ እንኳን መጽሃፍ መጻፍ አይደለም ከነ ሕይወቱ ነበር ወያኔ ቆዳውን የምተገፈው፡፡ ነገር ግን እርሳቸውን ጫፋቸውን ሰትነካ ነው ከነመጽሃፋቸው የለቀቀቻቸው፡፡ አሁንም ያን ሁሉ ግፍ በአማራ ላይ ሲያሴሩ ከርመው አልበቃ ቢላቸው አዜማ ኢዜአ እያሉ ዕድሜ እና ስህተት አላቆም ብሏቸው አማራውን ለማጥፋት ላይ እና ታች ይባዝናሉ፡፡ በመጨረሻ የምመክራቸው ቢኖር ለህሊናዎ ተገዥ ይሁኑ፡፡ ባንዳ እና እራስ ወዳድ አይሁኑ፡፡ ሰው ያልፋል፤ ለፈረንጅ ፍርፋሪ ሀገርዎን አይበጥብጡ፡፡ ሌላው በመጨረሻ አማራ ላይመለስ ቆርጧል እንኳን የእርስዎ የባንደዎች ፓርቲና ሌላ ምድራዊ ሃይል አይመልሰውም፡፡ እግዚአብሄር ልቦና ይስጥዎ፡፡

 4. The anti-Amhara political ideology started with the launching of the Marxist thesis of Walelign Mekonen in the late 1960s. This thesis highlights among others the oppression of the what it calls the nations and nations by the Amhara mation. It clearly demonizes the Amharas as the oppressors of the others in Ethiopia. The disciples of this Stalinist teaching are the EPLF,TPLF,EPRP and OLF all of which waged direct and indirect anti-Amhara campaigns. The EPRP was able to garner widespread among the Amhara elites and students. But the party was under the leadership of the Tigrean elites and incited violence that led to the deaths of tens of thousands of Amharas in the whole country. The Tigream elites whether they are in the TPLF or EPRP, they hated the Amharas and used their own evil ways to destroy the Amharas.

 5. የአማራየህልውና ትግሉ ላይ መለስ መቀጣ መቀጣጠሉ ያስደነገጣቸው ለአማራህዝብ ስር የሰ የሰየሰደደ ጥላቻ በደማቸው የሚሯሯጥ
  እንዳርናጋቸው እና የግ7ቅሪቶች ከኢሳት ቲቪ እና ከኦዴፓ/ኦነግ (ሁለም ለአማራ ህዝብ ያላቸው ጥላቻ ከትነግ ጋር በአንድ ስትራቴጅካል ስልት ያሰልፋቸዋል) በመቀናጀት ካለፈው ለውጥ ብሎ ከተባለ ግዜ ጀምሮ በኢሳት ቲቪ በሲሳይ አጌና የቀረበ አማራ የለም የሚል ትርክት አሁንሞ በግ7 ስም በተለመነ ዶላር እየተምነሸነሸ እንደልቡ አማራ የለም በሚለው ክልል. ጎንደር ባህርዳር ጎጃም እየተመላለስ በሽምግልና ዘመኑ በክፍት አፉ ለአማራ ህዝብ ያለውን ንቀት ከኦዴፓ/ኦነግ የተሰጠውን ስውር ተልኮ ለአማራ ህዝብ የሚታገሉትን በሴራ እንዲገደሉ እንዲታሰሩ እጃቸውን ከማስረዘማቸውም በተጨማሪ የፈጠራ ታሪክ በአማራ ማንነት ባህል ቋንቋ ለማጥፋት ከጣልያን በከፋ መልኩ በአማራ ላይ በቅጡ ፊደል ባልቆጠረበት የታሩክ ትምህርት ክፍት አፏን ሲከፍት በየትኛውም የአለም ክፍል ያለ መላው አማራ ዝም ብለን ለሰከንድ ልንታገሰው አይገባም።

 6. Amhara is the nucleus, the centre of ethiopia. without amhara there is no ethiopia. ethno fascist groups tplf and olf have worked for decades to destroy amhara, because amhara always stands to defend ethiopia. . Amhara is now getting stronger and this is a nightmare for the fascists because amhara strength means a threat to their strategy to dismantle ethiopia. that is what the fight is about.
  Andargachew tsgie has joined the chorus for his own political agenda. it is such a shame that this person who was seen by many as the voice for the many has turned into this level.

 7. this man was saying i am both amhara and oromo by birth. now he is saying there is no amhara. what a lunatic. he is so confused woyane have poisoned him when he was in prison

 8. የሥልጣን ጥም የማያስብለው የለም።ከድርጅቶች ከህወሓት ፣እነኦነግ ከግለሰቦች በአብይነት እነ አንዳርጋቸው፣ፕሮፍ መስፍን በጥቂቱ ብንወስድ የአማራን አለመኖር ዘብዝበዋል። እንግዲህ ከሌለ እንዴት በሌለ ነገር ይፅፋሉ፣ወይስ የለም ብለው እንዲኖር ምኞት ነው። ድርጅቶች ተሰብስበው ክልል ሲቀይሱ አማራው ከሌለ እንዴት ክልል ሰጡት።ወይም በክልል የሌለውን አካተው የዘር ማጥፋት እርምጃ ለመውሰድ ነው። የለም ተብሏልና።
  ከሐዲዎች ወረበሎች፣ አይሳካላችሁም።

 9. “የአማራ ህዝብ ሰላም እና እረፍት እስካላገኘ ድረስም የአማራ ወጣቶች እንደ አማራ ብሄረተኛ ወይም እንደ ኢትዮጵያ ብሄረተኛ ወይም በሌላ መልክ ሆነዉ ትግል ከማድረግ አይቆሙም::ስለዚህ መፍትሄዉ የችግሩን ስር ማድረቅ እንጅ ሀሰተኛ ትርክ መፍጠር አልነበረም::”

  የአማራ መደራጀት ለአማራ ጠል ፖለቲካ ደላላዎችን ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል:: አማራም ተመልሶ ላይተኛ ባኗል:: ይህቺን የፈጠራ ኦሮሚያ መኖር ያለመኖር ከወዲሁ ያሸበራቸው ፅንፈኞች የአማራ መድራጀት እንቅልፍ ነስቷቸዋል::አንዳርጋቸውም መሰረት የሌለው ቢቀባጥር መሬት ላይ ያፈጠጠውን ሀቅ ሊለውጠው አይችልም:: እሱ ማንነቱ ሊያጠራጥረው ይችል ይሆናል ሆኖም እጅግ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ እስርግጦ አማራነቱን ያውቀዋልና የእሱ ቧልት እውነትም ቧልት ውሀ አይቋጥርም::

 10. አማኑል ዘአምቦ
  ስለአማራ ምን አገባህና ትቀባጥራለህ:: ህዝብ አማራ ነኝ ካለ ወደድክም ጠላህም መቀበል ትገደዳለህ:: የአንተን ማንነት የጠየቀህ የለም:: የአማራ ህዝብ በአንተ ቢጤዎች ትናንሾች የሚለካ ህዝብ አይደለም::ሁሉም የበላበትን ወጪት ሰባሪ ሆነ እንጂ አማራ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ከድንቁርና ወደእውቀት ያሸጋገረ ህዝብ ነው:: ህሊና ቢፈጥርብህ ይህን ህዝብ ታመሰግን ነበር::

 11. ወይ ዕድሜ ደጉ ይሄ “ሥምንተኛ ሽህ”ሥንቱን ያሰማንና ያሣየን ይዟል ጃል? ይች አንዲት እንጀራና ያች አንዲት ወልጋዳ ወንበር ሰውን እንዲህ እንደ’ሥሥት እየለዋወጡ ቁም ስቅል ያሣያሉ ማለት ነው? “አጃኢብ!”አለ ያ የወንዜ ልጅ። የአራት ኪሎዋ ወንበር አንዲት መሆኗ ከፋ እንጂ እኔንም፣አንተንም፣እሱንም…አንዳርግንም፣ብሬንም፣ ጃዋርንም፣ፕሮ. በየነንም፣ ጃል መሮንም፣ዳውድ ኢብሣንም፣ሌንጮንም፣ዓለምንም፣ አማኑኤል ዘአምቦንም፣አባ ጫላንም፣ገመዳንም፣ሕዝቅኤልንም፣ ጸጋየ አራርሣንም፣ ደብሪፅንም፣ ኡጁሉንም፣ ዳሞቴንም… ባንድ ጊዜ ምኒልክ ቤ.መንግሥት ውሥጥ ጥዶ ወይ ጎልቶ ኢትዮጵያን ሥትንተከተክ ማየት ነበር። “የ’ብድ ቀን አይመሽም” አሉ። ነገር አታዙር።

 12. ሀገር ወዳድ እና የኮምፒተር እውቀት ያለው ይህን ህዝብን ገድሎ ትርፍ የማግኛ አካሄድን ለማስቆም ይህን መጻፍ በኢንተርኔት የፈለገ እንዲያነበው ቢለቀው ግለሰቡ ወደ ብሪታንያ ተመልሶ ቅጥፈቱን አቁሞ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት በማመላለስ እንዲፈታ በእጅጉ የደከመችለትን እሱ ግን ስላደረገችለት ውለታ አንድም ቀን ላላመሰገናት ባለቤቱ ጥቅም ይኖረው ነበር።
  የሚገርመው የአማራ ታሪክ ካልጠፋ ታሪክ መስራት እንደማይቻል ሁሉ ለምን የአማራ ታሪክ መጥፋት እንዳለበት ግልጽ አይደለም ። አሮጌ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ እንደሚያበላሽ ሁሉ አንዳርጋቸው/
  ብርሀኑ/
  ሌንጮ/
  አረጋዊ
  ዲማ ነገዎ/
  ህዝቅኤል /
  በቀለ ገርባ
  የተባሉ እቅጣጫ የጠፋባቸው ግለሰቦች ሀይ ካልተባሉ በስተቀር እንዲሁ መጨቃጨቂያ መስጠታቸው የማይቀር ነው።
  አንዳርጋቸው ጽጌ በምርምር ስራዎች ያልተቃኘ የህይወት ዘምኑን ሁሉ በካድሬነት የኖረ መሆኑን የምናውቅ እናውቃለን እንዲህ በዘመኑ ሁሉ እየተገለባበጠ የሚኖረውን ኑሮ ግን አንድ ቦታ ላይ ሊገታ ይገባል ። ባለፈው አንዱ መጽሀፉን የተቸውን ሳነብ ለእሱ ተሸማቀቅሁ። በተንኮልና ጥልፍልፍ የተቃኙ በመሆናቸው የታሰሩና የተገረፉ የህዝብ ወገኖችን ፈንቅለው ኢዜማ የተባለውን የግንቦት ፯ ተቀጥያን መስርተው በቁጥጥር ስር አዋሉት። መቼም ያማራ ወጣት ሙቶ ካልሆነ ወደዛ ግድም ድርስ ይላሉ ብዬ አልገምትም።

 13. ወንደሰን ተክሉ ብለህ ስምህን ቀይረህ በአማራ ስም የሚትነግድ የህወሀት ካድሬ መሆንህ ያስታውቃል አነዳርጋቸው የፃፈው እንኳን በደንቡም ሳይገባህ ለመተቸት ትሞክራለህ z game is over . Wake up

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.