የአንድ ተጫዋች ወርሃዊ የደመወዝ ጣሪያ ከ50 ሺህ ብር እንዳይበልጥ ተወሰነ

የኢፌዴሪ የስፖርት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያዘጋጁትና በተጫዋች ወርሃዊ ደመወዝ ጣሪያ ላይ የሚመክር መድረክ በቢሾፍቱ ዛሬ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮችና ስራ አስኪያጆች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ኮሚሽነሮች እና የክልል ፌዴሬሽን አመራሮች እና የተጫዋች ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ የተጨዋቾች የደመወዝ አከፋፈልን በተመለከተ ከሌሎች ሀገራት ጋር በማነፃፀር ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል።

ጥናታዊ ፅሑፉን መሠረት በማድረግም የመድረኩ ተሳታፊዎች የተጫዋቾችን ደመወዝ ጣሪያ ማስቀመጥ ከሀገር ውስጥ ተጫዋች እና ከክለብ አንፃር ያለው ጠቀሜታ፣ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል።

በውውይቱም የተጫዋች ደመወዝ ጣሪያ መቀመጡ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማፍራት፣ የገንዘብ ብክነትን ለመቀነስ እና ተመጣጣኝ ክለቦች እንዲኖሩ ያግዛል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ብቁ እና ተፎካካሪ ተጫዋችን ለማፍራት እንደሚያግዝም የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ውይይቱን መሠረት በማድረግም የአንድ ተጫዋች የደመወዝ ጣሪያ 50 ሺህ ብር እንዲሆን ተወስኗል።

ውሳኔውንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ወር ጀምሮ በመመሪያ በማስደገፍ እንዲያስፈፅም አቅጣጫ ተቀምጧል።

ኤፍ ቢ ሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.