“እኛ ማንንም አንፈራም” የቤተክርስቲያን አባቶች 

ክርስቲያኖችን በሜንጫ በሏቸው ያለው ሰው በመንግስት እሽሩሩ እየተባለ፣ ቤተክርስቲያን እየተቃጣለች እና ክርስቲያኑ እየታረደ መንግስት እስካሁን አንድም ወንጀለኛ ለህግ አላቀረበም። በጀት ተመድቦለት በአይዲዮሎጂ የሚደገፍ ቡድን ቤተክርስቲያንን እያጠፋ ነው። በባሌ፣ኢሊባቡር፣ጅማ፣ቤንሻንጉል፣ ወለጋ፣ሐረር፣ሰሜን ሸዋእና ከሚሴ ላይ በእስልምና እምነት ተከታዮች ጥቃት እየደረሰብን ነው። የተዋህዶ ልጆች እየታረዱ ነው።

የእስልምና እምነት ተከታዮች የነብዩን ቃል ተላልፈዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ተቋማት ጉባኤም ይህ ነገር እስልምናን አይወክልም ብሎ በይፋ ሊናገር፣ሊያስተምር እና ሊያወግዝ ይገባል። መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ለወደሙት ቤተክርስቲያኖች ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን። እያረደኝ በደሜ መቻቻልን የሚሰብክ መንግስት አንፈልግም። የእስልምና ተቋማት ጉባኤ ይህን ጉዳይ በአስቸኳይ ቢመክርበት ይሻላል። አሁን መፍትሄ ካልተገኘለት ኋላ ታሪክ ይበላሻል። እኛ ሞተን ልጆቻችንን ከሃይማኖት ባርነት ነጻ እናወጣለን። እኛ ማንንም አንፈራም። እንኳን ዛሬ ለነዚህ ጥቂት ፖለቲከኞች እና ቡድኖች አይደለም የኛ አባቶች የተነሱ ጊዜ ምን እንደሚፈጠር ጣሊያን ምስክር አለን። ያኔ መንግስትም ሆነ ቤተክርስቲያን የሚሆነውን መቆጣጠር አይችሉም። እሳቱ ከተቀጣጠለ በኋላ ግን ማንም ማብረድ አይችልም። እየለመንናችሁ ሳይሆን እያስጠነቀቅናችሁ ነው። አልደረስንባችሁም፤ ስለ እግዚአብሄር አትድረሱብን። አልነካናችሁም፤ ስለ እግዚአብሄር አትንኩን።

1 COMMENT

  1. በዚህ ዘመን ለዛውም በሰለጠነ አገር ተማርን የሚሉ አገሪቷን ለማፈራረስና ለሃይማኖት እልቂት ሲገፋፉ ዝምብሎ ማየት የሁሉም ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ ዓላማቸው ምን እንደሆነ መቼም ለመንግስት አይሰወረውም፡፡ በጣሊያን ጊዜም እኮ የውስጥ ባንዳዎች ነበሩ ወንድማቸውን ሲያገድሉ የነበሩት ግን ለነሱም አልበጀም እንጂ፡፡ ማፈሪያ ይሆናል፡፡

    ክረስቲያን ሙስሊም እኮ የቆየና የጠለቀ መዋደድ ብሎም በፍቅር የሚኖር ህዝብ ነው፡፡ ስንቱስ አልተጋባም አልተዋለደም? ስለዚህ ይህን ውህደት አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡ ለአክራሪ አመለካከት ቦታ መስጠት አያስፈልግም፡፡ ለነሱም አይበጅም፡፡ በታሪክ ለግራኝ መሐመድ እና ዮዲት ጉዲትም አልበጀ፡፡

    በተለይ በእስልመና እና ክሪስቲያን ሓይማኖት በበላይ አመራር ላይ ያሉ በአንዱ የሃይማኖት ተቋምና ህዝብ ላይ ችግር እንዳይፈጠር በጋራ ቀድመው መስራት አለባቸው ከዛ ህዝብ ራሱን ይጠብቃል፡፡ አንዱን አስመልክቶ ለሚሰራ ስራ ሌላኛው ቀድሞ ማውገዝ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በቤተክረስቲያ፣ ሰላማዊ ህዝብና ቄሶች ላይ ጉዳት ሲደርስ የዕስልምና አመራሮች ቀድመው ሲያወግዙ ብዙም ስላልታየ፡፡

    አምላክ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.