የኢህአዴግ የሰሞኑ ስብሰባ ማግስት በአቶ ደመቀ መኮንን ላይ በዲጂታል ወያኔ ዘመቻ ተከፍቱዋል

የአዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያለው ይፋ ገጽ ነኝ የሚል በጉባዔው ለሰማናቸው መረጃዎች የሰሞኑ ዘመቻ ምክንያት መሆናቸውን እንድንጠረጥር የሚያደርግ ነው።በአቶ ዮሃንስ ስም በርከት ያሉ የፌስ ቡክ ገጾች አሉ።እሳቸው በይፋ ይህ ገጽ የኔ አይደለም ሲሉ የሰጡት ማብራሪያም አልደረሰንም።የሳቸው አይደለም የሚሉም ትክክለኛ ያሉትን ገጽ አላጋሩም።ሁለት ነገር ግን እውነት ነው።በኢህአዴግ ስብሰባ ዲጂታል ወያኔ ምን የተለየ ነገር አቶ ደመቀ ተናግረው ዘመቻ ተከፈተባቸው?

ሕዝብ በይፋ የሚያውቀው ሰሞኑን የተናገሩት የለም። ነገር ግን እዚያ ስብሰባ ላይ ምን ነበር በቅርብ በስፋት እንመለስበታለን። በአቶ ዮሃንስ ቧያለው ስም የወጣው ጽሑፍ ግን የዲጂታል ወያኔን ዘመቻ ይቃወማል። ኢህአዴግ ቤት የውስጥ ሽኩቻን መሰረት አድርጎ ሰሞኑን የተጀመረው የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ አስከትሎ ምን ያመጣ ይሆን? ወደፊት የምናየው ይሆናል። ለሁሉም ለውይይት ቢሆን ጽሁፉን እነሆ ያንብቡት ሼር ያድርጉት አስተያየት ይስጡበት ስንል በድጋሚ አቅርበነዋል።

“ትህነግን ለማጀገን ደመቀ መኮንን በዲጂታል ወንበዴዎችና አዳዲስ ተስፈኞች ስለምን ጥርስ ተነከሰባቸው”
. ምክንያት:-

1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን ማለት ሲጥልህ እንጂ ሲታገልህ አታየውም ወይም ሲታገልህም ሲጥልህም በግልፅ ታየዋለህ። ስለዚህ አዳዲስ ተስፈኞች ታግሎ ከጣላቸው ወንበዴ አስረጂዎቻቸው በመማራቸው ነው።
2ኛ. አዴፓን መግታት የምንችለው ከፊት ያሉ መሪዎችን በቁሞ ቀር ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በማጠልሸት የሚመስላቸውና ወፍዘራሽ የሳይበር ህዝበኛ ዕሳቤ ያፈራቸው የለውጥ አረሞች በመሆናቸው።
3ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን የትኛውንም የተንኮል ፖለቲካዊ አሰላለፍም ይሁን ጨካኝ የሴረኝነት ጆከር በፎርፌ ማጋየት የሚችል መሪ እንጂ ፓርቲያችን አዴፓም ሆነ የአዴፓ አመራር ማንንም ይቅርታ ለመጠየቅ እስከ ወዲያኛው አይሰራም።
4ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን ስራቸውን ሲሰሩ ልታይ ልታይን የማይፈልጉ ከልብ በመነጨ ለሀገር አንድነትና ፍቅር እንጂ ለስቲዲዮ ክምችትና ዘገባ ባለመሆኑ ልብ በሉ።

ሕብር ሬዲዮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.