ፌስታልህን ስጠኝ… “/ሜሮን ጌትነት/”

ከጠቆረው ገፅህ ከቆዳህ ላይ ውይብ
ከከሳው ሰውነት ከግንባርህ ሽብሽብ
በፅናት ውሃልክ ይታያል ተሰምሮ
ለቃል የመታመን፣ ላመኑት
የመኖር የአላማ ቋጠሮ።

እኔማ…
ከአንተ ጨለማ ውስጥ
በወሰድኩት መብራት
ከአንተ ሰንሰለት ስር ካገኘሁት ፍ’ታት
በአንተ አለመበገር ባገኘሁት ብርታት
ወግ ደርሶኝ ጀግኜ ጬኸቴን ብለቀው
ደርሶ የፈሪ ዱላ
እንደ እያሪኮ ግንብ ተናደ ጭቆና።

እናም ታዲያ ዛሬ…
ወልዶ ላሳደገ ምጥ እንደመካሪ
ቀን የሰጠኝ ቅል ሆንኩ ዞሮ
አንተን ሰባሪ
እርግጥ ገብቶኝ ቢሆን የአላማህ ውጤቱ
መች ያስፈራኝ ነበር ያንተ ብዕር
በልጦ ብረት ካነገቱ
ፍርሃት ባይሆን ኖሮ ስጋት
የሆነብኝ ‘ካፍረቴ እያላጋ
መቼ እዘነጋለሁ የከፈልክልኝን
መራር ትግልና የነፃነት ዋጋ።
አንተ ማለት… ፅናት! መንገድህ አላማ!
ለሌሎች ደህንነት ራስን የመስጠት-
የድምፅ የለሽ አርማ።
ያልከው ዲሞክራሲ …ያለምከው ነፃነት
እስኪመጣ ድረስ…የታገልክለት ቀን
የታሰርክለት ዕለት
በከፍታህ መጠን የሞራል
ልዕልናን እንዳስታውስበት
ፌስታልህን ስጠኝ ሙዚየም
ሰቅዬ ራሴን ልውቀስበት!
ታሪክ ልንገርበት!
ፅናት ልስበክበት!

Image may contain: 2 people

1 COMMENT

 1. አይ እንዲህ ያለሽ አር ቲስት ሰውየውን አቀሳስረሽ እሳት ልታስጨብጪው ነውን?

  እንዳንቺ ያሉ ወስዋሾች ብዙ ጊዜ ይህን ልምድ የሚቀስሙት ከሰይጣን ነው ፤ ሰይጣንም ሰዎይ ሃጢአት እንዲሰሩ አጣፍጦ እያሳየ ያበረታታና ቅጣቷ ስትመጣ እርሱ ከቦታው አይገኝም ፤

  ሜሮንም ይህን ውዳሴ እና የማይክ ድርድር እንደ ነፍሱ የሚወደውን ምሥኪን ሰው አቀሳስረሽ እሳት ልታስጨብጪው መጣርሽ ደግ አይደለም በደምባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዲሉ እንኳንስ ተወድሶ እንዲሁም ይጨብጠው ያጣውን ባለፌስታል መሸንገሉን ብትተይው ደግ ነበር ፤ ያው አንቺም ስለ ኮንዶሚኒየም ገጥመሽ አርበኛ የሆንሽ የሱ ቢጤ ነሽና ምንም እንኳ እስር ባያገኝሽም ለቢጤሽ ውለታ መዋልሽ አግባብ ነው

  17ጊዜ ታስሬአለሁ እያለ በዚያ የሚመጻደቅና ከእስረኞች በላይ ታሳሪ በመሆን እየተኩራራ አሁንም እንደ ምንም ብሎ ለመታሰር ደጅ የሚጠናና ድንበር የሚዘል ምሥኪን ሰው ከዚህ በላይ ነፍሱ ምን ያረካታል?

  አወይ ግን የመንሥት ጭካኔ ! ምናለ ይሄን ፍላጎቱን ቢሞላለት? መታሰር እንደናፈቀ 17 ላይ ባያቆመውስ? ምናለ 18 እና 20 ቢያደርሰውና የራሱም ሪከርድ ራሱ ቢሰብር? መንግሥት የዜጎችን ፍላጎት ለመሙላት ይተጋል እየተባለ እስክንድር ላይ መጨከኑስ አግባብ ነው? ዳቦ ለሚፈልገው ዳቦ ቤት እየገነባ መታሰር ለፈለገው እስክንድር እስር መንፈጉ ፍትሃዊ አያደርገውም ፤

  ሜሮን የጠየቀችህን ፌስታልህን ስጣትና አስገርመን ከፌስታልህ ስር ያለችውንና ያልተዘመረላትንና ማንገቻ የሰራህላትን የሲሚንቶ ወረቀት እንዴት እንደሰፋሃት ለትውልድህ በማስተላለፍ ሀገራዊ ውለታ እንድትውል እንጠይቅሃለን ፤

  አሁንማ ጥሩ ሳምሶናይት አዘጋጅተህ ስትፈታ እየጎተትክ ልትወጣ እና ኤርፖርት የሚታየውን ድባብ በከርቸሌ ለማሳየት መናፈቅህ ተሰምቷል፤ ፌስታልህንም በጨረታ ልትሸጣት እንደምትችል ይጠበቃል፤ ሜሮን ብልጧ ደግሞ ፌስታልህን ስጠኝ ስትል ታላዝናለች፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.