ወንጀል የሆነው አማራነት ብቻ ነው! -ጌታቸው ሽፈራው

vአማራ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ከማንም በላይ ለፍቷል። ከማንም በላይ። ይህ ልፋቱ አድናቆትን ያግኝ አላለም። ግዴታው እንደሆነ ያውቃል። ልፋቱ ግን እንደ ክፋት ታየበት። ያልተለጠፈበት ወንጀል አልነበረም። ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እየታገለ ቆስሏል፣ ደምቷል። የደማው ኢትዮጵያውያን እንዲጠቀሙ እንጅ ሊጠቀምባት አልነበረም።

አማራው ለኢትዮጵያ በመቆሙ በማንነቱ እየታደነ መከራ ደረሰበት። የኢትዮጵያ አንድነትን ሳይጎዳ ለማንነቱ ሲታገል፣ አማራን ማደራጀትም ወንጀል ሆነበት። ሌሎች እንገነጠላለን እያሉ ምንም ሳይባሉ “ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ከኢትዮጵያ አንሸሽም፣ አይበለው እንጅ ብትፈርስ እንኳ ትክሻችን ላይ ነው የምትፈርሰው” የሚለውን አማራ ተጠቂ ሆኗል።

የሌላው ፅንፈኛ ሀገር ገደል ትግባ እያለ፣ የህልውና ትግል ላይ ያለው አማራ “ፅንፈኛ” ተብሎ ይሳደዳል።

አማራው ለአማራም ሲታገል፣ ለኢትዮጵያም ሲታገል ወንጀል ይሆናል።

አማራው ሲደማለት ያስወገዘው ኢትዮጵያዊነት፣ ሌሎች ሲይዙት ሽልማት ይሆናል። ያውም የሚሞገሱበት ለይስሙላህ ብቻ ይዘውት ነው። አማራው ሲደራጅ ወንጀል የሆነው ለሌሎቹ ግን የሚደገፍ ነው።

ሌላው በማንነቱ ሲደራጅ “ህገ መንግስታዊ መብት” ይሆናል። አማራ ሲደራጅ ሽብር ይሆናል። ሌላው ኢትዮጵያ ሲል ምርቃት፣ አማራው ስለ ኢትዮጵያ ሲለፋ እርግማን ሲወርድበት አይተናል።

በማንነት መደራጀት ወንጀል አለመሆኑን ሌሎች ሲደራጁ ወንጀል እንዳልሆነ አይተናል። በማንነት መደራጀት ወንጀል የሆነው ለአማራ ብቻ ነው። ስለ ኢትዮጵያ መዘመር ወንጀል አይደለም። ኢትዮጵያዊነትን ሌሎች ዘመርነው ሲሉ፣ ያውም ለይስሙላህ ምርቃት ወርዶላቸዋል። አማራውም ይዞት የኖረው ነውና መርቋቸዋል። አማራው ኢትዮጵያ ሲል ግን ሲረገም ኖሯል። ኢትዮጵያዊነት ወንጀል የሚሆነው አማራ ሲዘምረው ብቻ ነው።

በማንነት መደራጀት ወንጀል አይደለም። ወንጀል የሚሆነው አማራ በማንነቱ ሲደራጅ ነው። ስለ ኢትዮጵያ መዘመር ወንጀል አይደለም። ወንጀል የሆነው አማራ ስለ ኢትዮጵያዊነት ሲለፋና ሲዘምር ነው። ወንጀል የሆነው በማንነት መደራጀት አይደለም፣ ወንጀል የሆነው ኢትዮጵያዊነት አይደለም። ወንጀል የሆነው አማራነት ነው!

ዛሬ የትግራይ ብሔርተኞች ለመገንጠል እየፎከሩ ነው። አብዛኛዎቹ ቤተ መንግስት ውስጥ ከገዥዎች ጋር የሚውሉ ናቸው። ወንጀል አልሆነባቸውም። የኦሮሞ ብሔርተኞች የሚያደርጉትን በየቀኑ እያየን ነው። ከሌላ ክልል ገብተው ሕዝብ ለመበተን እየሰሩ ነው። ምንም አልተባሉም። ከኢትዮጵያ አንድነት የማይርቀው የአማራ ኃይል ግን እንዲጠፋ ተወስኖበታል። ለገዥዎቹ እንገነጠላለን ከሚሉት ይልቅ ከኢትዮጵያ የማይሸሸው የአማራ ኃይል “ፅንፈኛ” ተብሎ ተፈርጇል። ይጥፋ ተብሎ ተፈርዶበታል። ወንጀል የሆነው ስለ አማራ መቆም ነው። ወንጀል የሆነው አማራነት ብቻ ነው!

3 COMMENTS

 1. ጌታቸው ሽፈራው ሁሌ ለቅሶ ሁሌ ክስ ሁሌ ውሸት ሁል ጊዜ እኝኝኝኝ!

  እውነት አይዋጥልህም እንጂ እውነቱን ታውቀዋለህ ግን በውሸት ድሪቶ የተጀቦነ ኮተት ታሪክን አምነህ ለማሳመን አበሳህን ስለምታይ ከውሸት ጋር ላትፋታ ተጋምደሃል ።

  ከትላልቁ ውሸቶችህ አንዱ ስለ ኢትዮጵያ ሕልውና ከማንም በላይ የለፋው አማራ ነው ማለትህ ነው፤ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል የሚለውን ጮማ ብሂል በደምብ እየቆረጥከው ነውና ማወራረጃውን ደግሞ እኔ ላስጎንጭህ ።

  ሲጀመር ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ እንድትቆይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ውድ ዋጋ ከፍለዋል ፤ ይህን ያለማመን አባዜ ዛሬ ላይ ነገር እያበላሸ ሀገርን ወደኋላ እየሳባት ይገኛል ፤ ምክንያቱም የሚደጋገምን ውሸት እንደ እውነት የማይቆጥር እና ታሪኩን እየፈለፈለ እውነቱጋ የደረሰ ትውልድ ተፈጥሯልና ፤ ውሸትን ወርቅ ቀብተህ ብታሽሞነሙናት እውነት አትሆንምና በትናንት በሬ ለማረስ አትድከም ትናንት ላይመለስ ሄዷል ዛሬ እንኮንስ ውሸትን እውነት አስመስለህ ለማሳመን መጣር ይቅርና እውነቱንም እውነትነቱን ለማሳመን መረጃና የተደራጀ ማስረጃ ማቅረብ ግድ ብሏል ፤

  በመሆኑም ወዳጄ የዘፈንህም ቅኝት ቀይር ለኢትዮጵያ የደከመው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው እንጂ አንተ አማራ የምትለው ወገንህ (ወንዜህ) ብቻ አይደለም ፤ (በሽክና ጠላ እያሰከርክ ውሸት የምታስተፋቸውን እና እነርሱ በሚተፉልህ ውሸት በደስታ በሚያሰክሩህ በጢናኒጥ ምሁራን በነ ታዲዮስ ታንቱ ዓይነት ቀልዳ ቀልዶች ታምነህ አትዘላብድ )

  ምን አልባት አማራ ተጠላ ተብጠለጠለ ካልክም በሁሉም ዘንድ ቢጠላና ቢብጠለጠል በእናንተ በልጆቹ ተንኮል እና ውንብድና ነው፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያዊው ለሀገሩ የከፈለውን መሥዋዕትነት ሸምጥጣችሁ በመካድ ምርጥ ምርጡንና ያልዋላችሁበትን ታሪክ ሁሉ የራሳችሁ የማድረግ የቀበኝነት አባዜ እና ከሀገሪቱ ምድር ውጭ የሰው ፍቅር ብሎ ነገር የነጠፈባችሁ በመሆኑ ጭምር በመሆኑ ብትጠሉ ምን ይገርማል ???

  ይሄ የራስን ለሌሎች ነፍጎና ሙጭጭ ብሎ የሌሎች ላይ ግን አርቆ ማማተር (መቀላወጥ) ስር በመስደዱና ዘመን እንኳ ተቀይሮ የማይለወጥ የገነተረ ስብዕናችሁ ዛሬም ሁሉን እንድትጠሉና በአንጻሩም በሌሎች እንድትጠሉ አብቅቷችኋል ፤ እንጂማ ያ ታገልንልህ እያላችሁ የምትታገሉትና ከወገኖቹ እንዲገለል ተግታችሁ የምትሰሩበት ምሥኪን እና ሃይማኖተኛ ሕዝብ ከሰው መኖር ተስኖት ከወገኖቹ ይጠላላል???

  እስቲ እንታገልልህ ብላችሁ ከተሰባሰባችሁ በኋላ ከማን ጋር ታገላችሁለት? ጠላቱስ ማን ነበር ? ሕዝብ ለሕዝብ ጠላት ሆኖ ያውቃል እንዴ? እናንተ ግን ትግሬ በዚህ ሊወጋህ ነው ፣ ኦሮሞው ሊወርህ ነው ፣ ጉራጌው(ዶ/ር ብርሃኑን መሆኑ ነው) አንተን ለኦሮሞ ሊሸጥህ ነው ወዘተ … በሚል ዓይን ያወጣ ዘረኝነትን እያራገባችሁና ጉምዙን እንዳሻችሁ በጥይት አረር እየቆላችሁ (በናንተ ግምት ጉምዝ አናሳ ነው የሚበቀልለት የለም) ጉራጌ ያላችሁትም ዶ/ር ብርሃኑን ክልላችን ካላችሁት ባህር ዳር አባራችሁ የትግሬ የምትሉትንም ንብረት በጉን እህሉን ሳይቀር ስትዘርፉ ምንም እንኳ ጥሩ የመልስ ምት ቢሰጣችሁም ኦሮሞንም ለመተንኮስ አጣዬና ከሚሴ አካባቢ ስትራወጡ እንዳልነበራችሁና ዛሬም አለብላቢት ምላሳችሁ ባላረፈችበት ሁኔታ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቢጠላችሁ ምን ይገርማል?

  ልብ ያላቸው ሰዎች ወደ ፊት መጥተው በፍጥነት መፍትሄ ካላበጁስ በዚህ ብቻ ይቆም ይሆን ? ለህዝቡ ዋጋ የከፈለው አዴፓ እንደሁ በእናንተ ዘንድ እንደ ርኩስ በድን ነው ፤ ውለታው ተዘንግቶ አባላቱ ላይ እለት እለት ሞት ታውጃላችሁ ፤ በስራችሁ መሞት የሚገባችሁ እናንተ ሆናችሁ ሳላችሁ ንጹሃን ላይ ሞት ታውጃላችሁ ፤ ይሄ እስከመቼ ይቀጥል ይሆን?

  መጪውን ለማየት ያብቃን!!!

 2. ውድ አማራው ጌታቸው ሺፈራው፣
  “አማራ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ከማንም በላይ ለፍቷል። ከማንም በላይ። ይህ ልፋቱ አድናቆትን ያግኝ አላለም። ግዴታው እንደሆነ ያውቃል። ልፋቱ ግን እንደ ክፋት ታየበት። ያልተለጠፈበት ወንጀል አልነበረም። ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እየታገለ ቆስሏል፣ ደምቷል። የደማው ኢትዮጵያውያን እንዲጠቀሙ እንጅ ሊጠቀምባት አልነበረም።”

  ጎጃም ተወልደህ፣ እዚያው አድገህ፣ እዚያው ተምረህ፣ ተድረህ፣ ሥራ ይዘህ መሆን አለበት። ወይም በአካል አዲስ አበባ፣ ካርቱም፣ አሜሪካ ሄደህ፣ በአስተሳሰብ እዚያው ጎጃም ቀርተህ ሊሆን ይችላል። የአእምሮ ለውጥ ጊዜ ይወስዳል። በርታ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.