ደቡብ ግሎባል ባንክ ተዘረፈ!

ትላንት ለሊቱን የደቡብ ግሎባል ባንክ “ጀሞ ቅርንጫፍ” ተዘርፎ ማደሩን ከባንኩ ሰራተኛ ለመስማት ችለናል። ይህንን መረጃም ባንኩ አረጋግጦልናል። ከባንኩ ባገኘነው መረጃ መሰረትም ዝርፊያውን ፈፅመዋል ተብለው ከተጠረጠሩ የባንኩ ጥበቃዎች መካከል አንደኛው ሲይዝ የተቀሩት እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋሉም።

የተዘረፈው የብር መጠን ስንት ይሆን? ብለን ጥያቄ ያቀረብንለት የባንኩ ሰራተኛ ትላንት ከ300,000 ብር በላይ መግባቱን ነግሮን የተዘረፈውን አጠቃላይ ገንዘብ ግን አጣርቶ እንደሚነግረን ገልፆልናል። ተመሳሳይ ጥያቄ ለሚመለከትው ክፍል አቅርበን ይህን ብለውናል: “የሚያሳየው Balance 4.8 ሚሊየን ብር ነው። ከዛ ውስጥ ትንንሽ ቁጥር ያለው ገንዘብ ነው የቀረው።” ዝርፊያው ካዝና በመስበር የተፈፀመ እንደሆነ ነው የሰማነው!

በቅርቡ የኦሮሚያ ኮኦፕሬቲቭ ባንክ ለቡ ቅርንጫፍ መዘረፉም ይታወቃል።/TIKVAH-ETH

1 COMMENT

  1. መንግስት አለ ለማለት ይቻላል ወይ? የአቢይ ኦና የግብር~አበቹ ወይነም አዛዦቹ ወያኔዎች መንግስት፣ የለየላቸው ወንበዲዎች ድርጅት ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። በፍራቻ ብቻ አማራን ሲያሳድዱ፣ ይህን የመሰለ ወንጀል በዋናዋ ከተማ ይፈጸአማል። እስኪያልፍ ያለፋል።

    እንግዲህ፣ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀሰስ ስለማይለቅ፣ የቀን ጉዳይ ነው፣፣ በሰይፍ ፣ ለዚህ ግፍ የበቃ፣ በሰይፍ ይዳኛልና። ወይ ስደት፣ ወይ ጥይት ነው እጣ ፈናቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.