የሕገ መንግሥት ለውጥ – ለኢትዮጵያዊነት የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጉዳይ   (ኪዳኔ ዓለማየሁ)

ራዕይ፤ ዓላማና እቅድ፤

ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ሕገ መንግሥት ማዘጋጀቱና ተግባራዊ የማድረጉ ራዕይ ውድ ሐገራችን ከጽንፈኛነት፤ ከዘረኛነትና ከጭቆና የተላቀቀ ኢትዮጵያዊነት፤ ሰላም፤ ጸጥታ፤ አንድነት፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ፤ ሕብረት፤ መከባበር፤ ፈጣን ልማት፤ ወዘተ. የሰፈነባት ሐገር እንድትሆን ለማረጋገጥ ነው። ይህ ራዕይ ስኬታማ እንዲሆን፤ በአጭር ጊዜ (1 ዓመት) ብቁ በሆኑ ባለሞያዎች የተሟላ ረቂቅ ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅና በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በጥልቀት እንዲመለከተው ማድረግ፤ ከዚያም፤ አስፈላጊው ማሻሻል ተከናውኖ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመላው ሕዝብና ለሚመለከታቸው ድርጅቶች ቀርቦ እንዲመረመር በመጨረሻም ተቀባይነት በሚኖረው ብሔራዊ ጉባኤ ሕገ መንግሥቱ እንዲጸድቅ ሆኖ በሚቀጥሉት ዓመታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሚመረጥ ምክር ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ማሻሻል ይቻላል።

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ሰቆቃዎች፤

እንደሚታወቀው፤ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ላይ ሰፍኖ የሚገኘው ሕገ መንግሥት ሕዝቡን በቋንቋና በጠባብ ዘረኛነት በተመሠረተ የክልል ሥርዓት ከፋፍሎ ባስከተለው የእርስ በርስ መናቆር፤ አለመተማመን፤ መከፋፈል፤ አለመተባበር እጅግ አሰቃቂ መጠነ ሰፊ ስቃይ እያስከተለ ነው። በዘረኛነት ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ብዙ ሺዎች ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል። እጅግ ብዙ ሰዎች በተለይ ሴቶችና ሕጻናት እየተሰቃዩ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከሕገር ለመሰደድና በታሪክ ያስተናግዷቸው በነበሩ በዓረብ ሐገሮች ጭምር በዝቅተኛ ደረጃ ለመኖር ተገድደዋል። በጠባብ ጎሰኛነት መለያየት ምክንያት እጅግ ብዙ ንብረት ወድሟል። የዘረኛነቱ ጠንቅ፤ ፋሺሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ዘመን ከፈጸመችው አሰቃቂ የጦር ወንጀል ብሷል።

ኤርትራ ከእናት ሐገሯ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች። በአሁኑ እኩይ የሕገ መንግሥት አወቃቀርና ሥርዓት፤ “ክልል” የተሰኙ አንዳንድ አካባቢዎችም ለመገንጠል እያኮበኮቡ ነው። ደቡብ ክልል ውስጥ ከሚገኙ አካባቢዎች ውስጥም ወደ ክልልነትና የመገንጠል አባዜ ለመዝቀጥ አቅጣጫ እያንጸባረቁ ነው።

ያሁኑን ሕገ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጫኑት ተጠያቂዎች አንደኛው ዓላማቸው፤ ሕዝቡ በዘረኛነት እርስ በርስ እንዲናቆርና እንዲጨፋጨፍ ስለ ነበር ያለሙት ሁሉ እየተሳካላቸው ነው።

ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ የሚያደርጋት፤ ሕዝቧ በኢትዮጵያዊነት አንድነት የሚተባበርና የማይደፈር መሆኑን በነአጼ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ከዚያም በአድዋ የጦርነት ድል ያስመሰከረች መሆኗ ነው። ያሁኑ ሕገ መንግሥት ግን ኢትዮጵያን በአሳፋሪና በውዳቂ ዘረኛነት ከፋፍሎ ሊያስደፍረን ነው። የባሰ ሊያጫርሰን ነው።

በዘረኛነት ሥርዓቱ ከባድ ድክመት ምክንያት ኢትዮጵያ በድህነትና በሙስና ታዋቂ ሆናለች። በተጨማሪም፤ በብዙ ዓለም-አቀፋዊ መስፈርቶች ኢትዮጵያ የዓለም ጭራ ሆናለች። ተመጽዋች ሆናለች። http://hdr.undp.org/sites/all/themes/hdr_theme/country-notes/ETH.pdf

ለበለጠ ዝርዝር ከዚህ በታች ያሉትን መመልከት ይጠቅማል፤

https://ecadforum.com/Amharic/archives/19630/

https://www.nytimes.com/2019/01/03/opinion/ethiopia-abiy-ahmed-reforms-ethnic-conflict-ethnic-federalism.html

ሥልት፤

ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ሕገ መንግሥት ለማርቀቅ የመጀመሪያ እርምጃ መሆን የሚገባው፤ ለተግባሩ ብቁ የሆኑ የሕግ፤ የኢኮኖሚ፤ የማሕበራዊ፤ ወዘተ. ባለሞያዎች በመምረጥ አንድ ግብረ ኃይል ማቋቋም ነው። ግብረ ኃይሉም በተቻለ ፍጥነት፤ ከተቻለ በ6 ወሮች ውስጥ ተግባሩን አከናውኖ በሚለጥቁት 6 ወሮች ውስጥ በሚከናወን አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በጥልቀት እንዲመረመር ማድረግ ነው።

ከዚያም ሌላ ተገቢ የሆነ ግብረ ኃይል በማቋቋም፤ በሚለጥቀው አንድ ዓመት ውስጥ፤ በኢትዮጵያ እስከ ወረዳ ድረስ በሚከናወን ምክክር፤ የሚመለከታቸውን ድርጅቶች በሙሉ በማሳተፍ ስለ ረቂቁ ሕገ መንግሥት የሚገኘውን ሀሳብ ማከማቸትና በሐገር ለሚከናወነው 2ኛ ጉባኤ በማቅረብ ጥልቀት ያለው ውይይት እንዲከናወንበትና እንዲወሰንበት ማድረግ ነው።

የአዲሱ ሕገ መንግሥት ባለቤት፤

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለራሱ የሚበጀውን ሕገ መንግሥት በጥልቀት መርምሮ የሚያጸድቀውና በሚያስፈልግበት ጊዜም እንደ አስፈላጊነቱ የሚሻሻልበትን ሥርዓት ይወስናል።

5 COMMENTS

 1. ውድ አቶ ኪዳኔ፣
  “ኤርትራ ከእናት ሐገሯ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች” ስትል ምን ለማለት ነው?
  ወደ “እናት አገሯ” ትመለስ ነው? ምን ዓይነት አስተሳሰብ ነው?
  ኤርትራውያን ሌላ (ጎረቤት) አገር ነን ብለዋል እኮ! የኢትዮጵያ ቅኝ ነበርን፣ በትግላችን ነጻ ወጥተናል ነው የሚሉት፤
  አሁን “አንድ ሕዝብ ነን” “እናታችን ኢትዮጵያ” ያሉት ከገቡበት አረንቋ ኢትዮጵያ እንድታላቅቃቸው እንጂ
  የምር መስሎህ ከሆነ ገና ምኑንም አላወቅህም ማለት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጤፍና በርበሬ፣ ቡናና ቅቤ
  ትንሽ ያመላልስና ሁኔታው ሲለወጥ ታያለህ! እና አትቸኲል።

 2. ሳይቀደሙ መቅደም!

  የብዙዎች ስጋት በአንቀጽ 39 አገሪቱ ትበታተናለች የሚል ነው። ነገር ግን አንቀጹ መብት የሚሰጠው ለክልሎች (Federal states) ሳይሆን ለብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ወይም ሕዝብ ነው። ይህን በአንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1 እንዲህ እናነበዋለን፦
  ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው፡፡

  የብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብን ምንነት በተመለከተ ሕገመንግስታዊ ድንጋጌው በንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የሠፈረው እንደሚከተለው ነው፦
  በዚህ ሕገ መንግሥት ውስጥ “ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ” ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸውን ባህርይ የሚያሳይ ማኀብረሰብ ነው። ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባሕል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው፡፡

  በዚህ መሠረት የብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ወይም ሕዝብነት መስፈርቶች 5 ናቸው። የጋራ ባሕል/ልምድ፣ ቋንቋ፣ ሕልውና/ማንነት፣ ሥነ ልቦና፣ እና መልክዓ ምድር ናቸው። መልካም! አንድ ጥያቄ ይከተላል፦ ታዲያ ክልሎች(Federal States) ከዚህ ድንጋጌ ይለያሉ ወይ? የክልል መንግስታት ሲመሠረቱ በምን መስፈርት እንደሆነ ባስቀመጠው አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ መልስ አለ፦
  ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመሥረት ነው፡፡ ስለዚህ ክልል ለመመስረት 4 መስፈርቶች ተለይተዋል። እነርሱም አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት፣ እና የሕዝብ ፈቃድ ናቸው። ከብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ መለያ መስፈርቶች የጋራ ባሕል እና ስነልቦናን ሲያጎድል የሕዝብ ፈቃድን ጨምሯል። አንግዲህ ወሳኙ ጥያቄ የአንቀጽ 47 ክልሎች(States) 9 ሲሆኑ የተመሠረቱት በአንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 2 መስፈርቶች ነው ወይ የሚል ነው።

  መልሱ በፍፁም አይደለም የሚል ነው። ቢሆን ኖሮ 9 ክልሎች ከ80 በላይ ብሔረሰቦች በሚኖሩበት አገር እንዴት? 9 ፌደራል መንግሥታት ብቻ? ይህንን ስለሚያውቅ አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 2 ገና ከ70 በላይ ክልላዊ መንግሥታት ከነዚህ 9 ክልሎች ውስጥ መወለድ እንደሚቀራቸው እንደሚከተለው ይጠቁመናል፦
  በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከቱት ክልሎች ውስጥ የተካተቱት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ የየራሳቸውን ክልል የማቋቋም መብት አላቸው፡፡

  ስለዚህ የኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥታት የመፈልፈል የእድገት ደረጃቸውን(Metamorphosis) ገና አልጨረሱም። ሲጨርሱ ከ80 በላይ ፌደራል መንግሥታት ይኖሩናል።

  ያኔ የፌደራል አወቃቀራችን በእርግጠኛነት በአንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ነውና የአንቀጽ 39 የመገንጠል ጥያቄንም ማስተናገድ ይቻላል። ሂደቱም ቀላል የሚሆነው ብሔረሰቦች ሁሉ በወሰን ማለትም በአሠፋፈር፣ በማንነት፣ በቋንቋቸው እና በፈቃዳቸው ላይ የተመሠረተ ክልል ባለቤቶች ሆነዋል። አንቀጽ 39 መብትን የሚሰጠው ለብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ እንጂ አሁን ላሉት እና የብሔረሰቦች የጋራ መኖሪያ ለሆኑ የክልል መንግሥታት አይደለም።

  ለነጠላ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ እንጂ ለብሔረሰቦች ሕብረት እንኳን አንቀጽ 39 አይሠራም። ስለዚህ የትግራይ ክልል ስለፈለገ ብቻ ሀገር የመሆን መብት አይሰጠውም አንቀጽ 39። ይልቁንም መብቱ በውስጡ ለሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች ነው። ለትግሬ፣ ለኢሮብ፣ ለኩናማ፣ ለራያ። የአማራ ማንነትና የአፋር ማንነት ጥያቄ እና ፈቃድ ባለበት ሁኔታ አንቀጽ 46 ንዑስ አንቀጽ 2 ተጨፍልቆ የሚመሠረት አገር አይፈቅድም ሕገመንግሥቱ። ገና የአገሪቱ ክልሎች ምሥረታ ዑደት አላለቀም። 80 ክልሎች እስከሚኖሩ መጠበቅ ባያስፈልግም ትግራይ ውስጥ ያሉ ብሔረሰቦች ሁሉ ክልል እስከሚኖራቸውና የማንነት ጥያቄዎች ሁሉ እስኪፈቱ መጠበቅ ግድ ነው። ከዚያ እያንዳንዱ የትግራይ ብሔረሰብ በአንቀጽ 39 ተገንጥሎ በኋላ በመዋሐድ ትግራይን እንደ ሀገር ማቆም ይችላል። ከፈለገ።

  ደቡብ፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ አማራም ልክ እንደ ትግራይ ነው። ኦሮምያም ፌደራል መንግሥት እንጂ ብሔረሰባዊ ክልል አይደለም። ብዙ ሚሊዮን የራሳቸው ቋንቋ፣ ማንነት፣ ሥነልቦና፣ እና ፈቃድ እንዲሁም አሠፋፈር ያላቸው ብሔረሰቦችን መብት ጨፍልቆ ሀገር የሚሆንበት ሕገመንግስታዊ መሠረት የለውም። ሐረሪም ያው ነው። በአንፃራዊነት ተመሳሳይ(homogeneous) ማንነት እና አሠፋፈር ያላቸው ሶማሌና አፋር አንኳ ከሌሎች ጋር ያላቸው የወሠን ጥያቄም ሆነ በውስጣቸው የሚኖሩ ሌሎች ብሔረሰቦች እጣፈንታ ሳይለይ አንቀጽ 39 ላይ መንቀሳቀስ አይችሉም። እናም ሕገመንግሥቱ አንዱን በትኖ ሌላውን የሚምር አይደለም። በተለይ ደግሞ ፈጣሪዎቹንም ነው በመጨረሻ የሚበታትነው። ስለዚህ እልሁን ትተን ሀገራዊነትን በሚያጠናክር መንገድ ብናሻሽለው አይሻልም ወገኖች?

  Biblical Ethiopia @Facebook.com

 3. ለትግራይ ክልልም ሆነ ለሌሎች አንቀጽ 39 የመገንጠል መብት አይሰጣቸውም!

  አንድነት ይልቃል

 4. ውድ ወገኔ ዓለም፤
  ኤርትራ ከኢትዮጵያ የመገንጠሏ ነገር በቅርቡ የተከሰተ ሀቅ ነው፡፡ በኔ በኩል ያለው የወደፊቱ ራእይ ግን ከዚህ በታች ባለው እየተነበበ ነው፤
  h

  ኪዳኔ

 5. Wud Ato Alem,
  Please see my paper: “Horn of Africa: From Glory to Misery and Hope?” which is posted on Ethiopiazare.

  Kidane.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.