ምርመራው ውስጥ ተሳታፉ መባላችን ለታሪካችንም አሳፋሪ ስለሆነ አንቀጥልም – የነጀነራል ተፈራ ጉዳይ መርማሪዎች

(አያሌው መንበር)

በእነ ጀነራል ተፈራ ማሞና ኮሎኔል አለበል ያለ ምንም ማስረጃና ወንጀል መታሰራቸውን የተቃወሙ፣ ተጠርጣሪዎች አሁንም አልታሰሩም ይታሰሩ ያለወንጀል የታሰሩት ይፈቱ ባሉት እና

“እነዚህን የታሰሩትን ብቻ ወንጀለኛ ለማስባል እንስራ” በሚሉ በባለስልጣናት የሚታዘዙ መርመሪዎች መካከል አለመግባባት በመከሰቱ ጥቂት መርማሪዎች የሰኔ 15ቱን ምርመራ አቋርጠዋል።

በዚህ መልኩ ምርመራው ውስጥ ተሳተፉ መባላችን ለታሪካችንም አሳፋሪ ስለሆነ አንቀጥልም ብለዋል።

የታሰሩትን ብቻ ወንጀለኛ እናድርጋቸው የሚለው ቡድን (ፖሊስና ጥቂት ፖለቲከኞች) እነ ጀነራል ተፈራ፣ እነ ኮሎኔል አለበል፣እነ ኮሎኔል ባምላኩን ጨምሮ 12 የፀጥታ አመራሮች እንዲፈቱ ትዕዛዝ የተፃፈበትን ደብዳቤ ስልክ በመደወል ነጥለው እንዲያቆዩት በማድረግ ድጋሚ ያለምንም መነሻ ይግባኝ ጠይቆባቸዋል።

በእነዚህ ወንጀለኞች ቦታ እስከሚይዙ በሚል ያልወንጀላቸው የታሰሩ ሰዎች መታሰርና በእነ ዶ/ር አምባቸውና ሌሎች አመራሮች ግድያ የተከፋህ ወገን ሆይ ለሌሎች የትግል ስልቶች ተዘጋጅ።ስንታገሳቸው ካልታገሱ ምርጫው የራሳቸው ነው።

(ይግባኝ ባይ
የክልሉ ዐ/ህግና ፖሊስ ኮሚሽን
1ኛ ታረቀኝአረጋ
2ኛ እዮብ ጌታቸው
3ኛ ሁሉሹም አለሙ
4ኛ አብዮት አለሙ
5ኛ ም/ኢ/ር ሠጠኝ ወንዴ

ምርመራ ቡድኑ
1ኛ ም/ኢር ሠጠኝ ወንዴ
2ኛ ም/ኢር አሊ ገበየሁ
3ኛ ሳጅን ፋንታሁን ደሞዝ
4ኛ ሳጅን ሀይሌ ይግዛው
5ኛ ኮ/ር አትንኩት
6ኛ ም/ኢር ተስፋሁን ታምሩ
7ኛ ም/ኢር አምሳሉ
8ኛ እዮብ ጌታቸው
9ኛ ሁሉሹም አደላ
10ኛ ታረቀኝ አረጋ
11ኛ አብዮት አለሙ ናቸው እንግዲህ መርማሪዎቹ እና ለይግባኙ የተፈራረሙት እነዚህ ናቸው)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.