በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረና የ2.7 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የ3 ሀገራት ገንዘብ ተያዘ

በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረና ዛሬ በዋለው የምንዛሬ ተመን የ2.7 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው 11,900 ዲርሀም 76,230 የአሜሪካን ዶላር እና 66,900 የሳውዲ ሪያል በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የብር ኖቶቹን ከሀገር ለማስወጣት የተሞከረው በባለአምስት ሊትር ጀሪካን ውስጥ በመደበቅ ሲሆን በቶጎጫሌ ሚሊሻና የጉምሩክ አባላት የተቀናጀ ጥረት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ህብረሰተቡ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለማስቆም ከዳር እስከ ዳር እንዲረባረብ የገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪውን አቅርቧል፡፡

EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.